44.76 F
Washington DC
February 26, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት እንዲወጡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢፌድሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት እንዲወጡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢፌድሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል፡፡

ውይይቱ በትግራይ ክልል የተወሰደውን ሕግ የማስከበር እርምጃ እና የተገኘው ውጤት፣ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትና ኢትዮጵያዊያውያኑ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ቋሚ መልእክተኛው እንዳብራሩት በትህነግ የአመፅ ቡድን ላይ የተወሰደው ሕግን የማስከበርና የመከላከል ርምጃ የአመፅ የፓለቲካ መሪዎችን የዕብሪትና የአልደፈር ባይነት መንፈስ አክስሟል፤ ለዘመናት ‘እኛና እነሱ’ የሚለው የፍረጃ አስተሳሰብ እንዲሸነፍ በር ከፍቷል ብለዋል።

በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ችግሮችን ከመቅረፍ አኳያ አስተዳደራዊ መዋቅርን በማቋቋም ዕለታዊ ርዳታን በማዳረስ ላይ መሆኑን አምባሳደር ታዬ አብራርተዋል፤ ሠላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ለሚያከናውነው ሥራ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የአካባቢው ተወላጆች ድጋፋቸውን መስጠት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

አምባሳደር ታዬ እንዳስረዱት የተፈናቀሉ እና ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን ለመርዳት ከኢትዮጵያ ሕዝብና ከዓለም ማኅበረሰብ የሰብዓዊ እርዳታ የማሰባሰብ እና የማዳረስ ሥራ እየተከናወነ ነው፤ የዕርዳታው ስርጭት በአብዛኛው የሚከናወነው በመንግሥት በኩል ሆኖ የተወሰው ደግሞ በዓለም አቀፍና በረድኤት ድርጅቶች አማካኝነት መሆኑን ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ተግባራትን ለማገዝ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ ከ26 በላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በጥምረት እየተሠራ መሆኑን አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ ላመለከቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንደ የሚያከናውኑት ሥራና እንደ እንደሚያበረክቱት ፋይዳ እየታየ የሰብዓዊ ድጋፍ ሂደቱን እንዲያግዙ ፈቃድ እንደተሰጣቸውም አስታውቀዋል።

አንዳንድ ወገኖች የውጭ ዜጎችን ጭምር በመጠቀም በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የሀገርን ገፅታ በሚያበላሹ አፍራሽ ተግባራት ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ ጠቅሰዋል። እናም በሀገር ውስጥ ያለውን መልካም ሁኔታ በማስረዳት የሚቀርቡትን አፍራሽ እንቅስቃሴዎች መመከት እንደሚያስፈልም አምባሳደር ታዬ ተናግረዋል፡፡ ከምንግዜውም በላይ እንደ ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም እንደሚገባ አምባሳደሩ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ዲያስፖራው በሚኖርበት አካባቢ የሚገኙ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦችን፣ የፓርላማ አባላትንና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን አግኝቶ እውነታውን ማስረዳት ከማኅበረሰቡ ከመቸውም ጊዜ በላይ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን ግልጽ አድርገዋል፡፡

ቋሚ መልእክተኛው ኢትዮጵያን በመታደግ ሥራ ላይ ለተሰማሩ የዲያስፖራ አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በውይይቱ ላይ ለተሳተፉ የትግራይ ኮሚኒቲ አባላት በተለየ መልኩ ትግራይን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ ከግዚያዊ አስተዳደሩ ጎን መቆም እንዳለባቸው ጥሪ መቅረቡን ከለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ሲዋጉና ሲያዋጉ የነበሩ 18 ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር ዋሉ

admin

አምባሳደር አዲስዓለም ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስና ታጣቂዎችን ለመደገፍ ሲሰሩ ነበር-  መርማሪ ፖሊስ

admin

የማኀበረሰቡ የግንዛቤ እጥረትና የመሰረተ ልማት ችግሮች ነፍሰጡር እናቶች በቤታቸው ወልደው ለችግር እንዲጋለጡ ምክንያት መሆናቸውን የምስራቅ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

admin