60.78 F
Washington DC
May 16, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ኢትዮጵያዊነት የማይደበዝዝ ይልቁንም በይበልጥ የሚደምቅና የሚፈካ የጋራ ማንነታችን ሊሆን ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

“ኢትዮጵያዊነት የማይደበዝዝ ይልቁንም በይበልጥ የሚደምቅና የሚፈካ የጋራ ማንነታችን ሊሆን ይገባል” ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

ባሕር ዳር፡ የካቲት 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር የአማራ አመራር አካዳሚ ለመጀመሪያ ጊዜ ባስመረቃቸው ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው አካዳሚው ለዚህ የበቃው በሠራተኞች የዕሌት ከቀን ድካም በርካታ ፈተናዎችን አልፎ ነው ብለዋል፡፡

ወቅቱ በአንድ በኩል ትልልቅ እና አስደሳች ውጤቶች የተመዘገቡበት፤ በሌላ በኩል ደግሞ ፈተናዎች የበዙበት ሀገራዊና ክልላዊ ነባራዊ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነውም ብለዋል፡፡ ሀገሪቱ በቀጣይ የምትፈልገውን ከችግር መውጫ መንገድ መቀየስ ወሳኝ ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው፡፡

እየገጠሙ ላሉ መሠረታዊ ችግሮች እንደ አንድ መነሻ ሊወሰድ የሚችለው እንደ ኢትዮጵያ በሕብረ ብሔራዊነት የተገነባ መንግሥት፣ ዲሞክራሲን ለመትከልና ለማፅናት ፈተናዎች አሉ ነው ያሉት፡፡ የተራራቁ ርዕዮች፣ ሊታረቁ የማይችሉ ትርክቶች፣ የሲቪክ ባሕል አለመዳበር፣ ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን አጣጥሞ የመሄድ ችግር እና ሌሎችም ችግሮች መኖራቸውንም አንስተዋል፡፡

ማንነት ተፈጥሮዓዊ እውነታ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ እኩልነትና ወንድማማችነት በመሆኑ ሁሉንም በጥበብና በተሟላ ሁኔታ ልንይዝ ይገባል ብለዋል፡፡

“ኢትዮጵያዊነት የማይደበዝዝ ይልቁንም በይበልጥ የሚደምቅና የሚፈካ የጋራ ማንነታችን ሊሆን ይገባል” ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡

የአማራን ሕዝብ ከማንነቱና ከኢትዮጵያዊነቱ የሚነጥለው ምንም ኃይል አይኖርም ብለዋል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር፡፡ በርካታ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ክብሩንና ጥቅሙን በማስከበር ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በእኩልነት ለመኖር ችግሮችን በትዕግስት በማለፍ ችግሮቹ የሚታረሙበትንና እስከወዲያኛው እንዳይደገሙ እንታገላለንም ብለዋል፡፡

አሁን ላይ በማንነታችን ተነጥለን የሚደርሱብን ፈተናዎች የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ታግለን እናርማቸዋለን፤ ገዳዮቻችንን ለፍትህ እናቀርባቸዋለን ነው ያሉት፡፡

ለውጡን የሚመራ ጠንካራ ተቋም፣ የስበት ማዕከሉ እንደ ብረት የጠነከረ የአንድነት አካሄዳችንን የሚጎዳውን በማረምና ከፊታችን የሚገጥሙንን የልማት፣ የማኅበራዊና የፖለቲካ ችግሮችን እየፈታን የሀገር ካስማነታችንን፣ የሕልውና መሰረት መሆናችን አሁንም አጠናክረን መቀጠል ይገባናል ብለዋል፡፡

‹‹ እኛ የአማራ ክልል ሕዝቦች አንሰው ከሚያሳንሱን ጋር ጊዜያችንን አንፈጅም›› ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡ ተመራቂዎች ጊዜያችሁን ለሀገር ጥቅም አውሉት እንጂ በከንቱ ተግባር በመጠመድ እንዳታባክኑት ሲሉም አሳስበዋል፡፡

በትምህርት ራሱን ያነፀ ሰው የስሜት ብልህነት የሚታይበትና በአዎንታዊና በከፍታ የተለወጠ ልብ ባለቤት መሆኑን ልብ ማለት ይገባልም ብለዋል፡፡ የተቀበላችሁት ዲግሪ በሀገራችን ለውጥ ለማምጣት የመግቢያ ትኬት አድርጋችሁ እንድትቆጥሩትም ብለዋቸዋል ተመራቂዎቹን፡፡ እስካሁን ጥበብን ስትሹ መቆዬታችሁ መልካም ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የዚህ ጥበብ ፍሬያማነት የሚለካው ለሕዝብ በምትሰጡት አገልግሎትና በምታስመዘግቡት ውጤት ነው ብለዋል፡፡

ተመራቂዎቹ በሚሰጣቸው ኃላፊነት ክልሉን ወደፊት ለማራመድ በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

አካዳሚው የያዛቸውን እቅዶች ለማሳካትና ተልዕኮዎቹን ለመወጣት በሚያደርገው ሂደት ውስጥ የክልሉ መንግሥት የተለመደውን ድጋፍ ይሰጣልም ብለዋል፡፡

ሀገሪቱ ለምታደርገው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና የሰለጠነ ውድድደር የሚካሄድበት፣ እኔን ብቻ ስሙኝ የማይባልበት፣ ሕዝቡ የፈለገውን የሚመርጥበት እንዲሆን ተመራቂዎች የበኩላቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡ የክልሉን ሰላም በንቃት መጠበቅ እንደሚገባም ርእሰ መሥተዳድሩ አስገንዝበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በዚህ ወቅት ከገጠመው ችግር ለመውጣት የሰከነ ውይይት እና በሥነ ምግባር የተገራ የሥነ ተግባቦት አውድ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡

admin

በአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የፌደራል መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ፡፡

admin

የትግራይ ገበሬና የከተማ ነዋሪ በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሰም – ሪር አድሚራል ክንዱ

admin