70.81 F
Washington DC
April 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

አገር አቀፍ የማኅበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

አገር አቀፍ የማኅበረሰብ ተኮር የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2013 ዓ.ም (አብመድ) በስላም ሚኒስቴር አዘጋጅነት አገር አቀፍ የማኅበረሰብ ተኮር ምክክር በባሕርዳር እየተካሄደ ነው። በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ ዳይሬክተር ጄኔራል ወይዘሮ አስማ ረዲ የአማራ ክልል በርካታ ክልላዊና ሀገራዊ ተልዕኮዎችን በኃላፊነት እየተወጣ ያለ ክልል ነው ብለዋል። መንግሥት መሪ ብቻ ሳይሆን አገልጋይ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሯ ከአውቅልሃለሁ አመራር መውጣት ይገባል ብለዋል።

ሕዝብን የምናዳምጥበት የማኅበረሰብ ተኮር ምክክር ያስፈልጋልም ነው ያሉት። ሕዝብን የመፍትሔ አካል ማድረግ እንደሚገባም ተናግረዋል። ለሕዝብ ጀሮ ሰጥቶ ማዳመጥ አለመለመዱንም ተናግረዋል።

የሕዝብን ድምፅ ለመስማት እና የመፍትሔ አካል ለማድረግ የማኅበረሰብ ምክክር እንደሚያስለግ ነው የገለጹት፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ የምክክር መድረኩ የትህነግ ኃይል በጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ተደምስሶ ላይመለስ ባከተመበት ማግስት የሚካሄድ መሆኑ ትርጉሙ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከውስጥና ከውጭ በሚነሱ የሰላም ችግር እየተፈተነች እንደምትገኝም አቶ ሲሳይ ተናግረዋል። የችግሮቹ ማጠንጠኛ ባለፉት ዓመታት የነበረው የፖለቲካ ስርዓት የፈጠረው መለያየት እና መጠራጠር ነው ብለዋል። በነበረው ፖለቲካ ስርዓት የኢትዮጵያዊነት እሴት ተሸርሽሮ፣ ዜጎች እንዲገደሉ፣ እንዲፈናቀሉ ሀብትና ንብረታቸው እንዲወድም መደረጉን አንስተዋል።

የማያግባቡ ነገሮችን በውይይት መፍታት እንደሚገባ ¦ነሱት አቶ ሲሳይ በምክክር መድረኩ የተሳተፉ አካላትም ከምክክር መድረኩ የሚያገኙትን መልካም ነገር በአግባቡ እንዲተገበሩ ጠይቀዋል። ሕግና ስርዓትን በማስከበር የሰላም አምባሳደር መሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

የምክክር መድረኩ እስከ ጥር 8/2013 ዓ.ም የሚቀጥል ይሆናል።

ዘጋቢ፡- ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በሲዳማና ኦሮሚያ አጎራባች አካባቢዎች ዘላቂ ሠላምና ልማትን ለማጠናከር የሚያግዝ የጋራ ምክክር ተካሄደ

admin

በክልሉ የከተራና ጥምቀት በዓል ያለ የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታወቀ

admin

የአዲስ አበባ ከተማ ከ29 ሺህ በላይ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎችን አስመረቀ

admin