70 F
Washington DC
April 10, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

አለም ዙሪያ ለምትገኙ፣ በየሀገሩ ለተደራጃችሁ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ፡-

Social Media Campaign

አክቲቪሲቶች፣ በርካታ የፓለቲካ ስዎች፣ ምሁራንና ልዩ ልዩ ስብስቦች በጋራ ለመስራት የተቀናጁበት፣ የኢትዮጵያውያን ኔትወርክ በሰሜን አሜሪክ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ በመናበብ፣ እውቀት፣ የሰው ሃይል ፣ ሌሎችንም ግብአቶች በማሰባሰብ ፣ ለጋራ አላማ በጋራ መስራት ጀምረናል።

የኔትወርኩ አብይ ግቦችና አላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡ – ‘

• በኢትዮጵያ አንድነትና የህዝብ ደህንነት እንዲጠበቅ
• ሰላም፣ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ፣ መንግስት የሀራችንን አንድነት፣ የህዝቡን ደህንነት ፣ ሰላምና መረጋጋት እንዲያስጠብቅ
• በውጭ አለም ከሚገኘው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋር በመናበብና በመተባበር የበኩላችንን ድርሻ መወጣት።
• በውጭ የሚገኘውን የኢትዮጵያውን እንቅስቃሴ በልዩ ልዩ ተጨባጭ ተግባሮች እገዛ ማድረግ
ተጨባጭ እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን የሚከተሉትን ዋና ዋና የስራ ዘርፎችና ቡድኖች በማቆም መስራት አስፈላጊ ናቸው።

ሀ) የህግ ባለሞያዎች ኮሚቴ በማቋቋም በጽንፈኛ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ጥላቻዎች፣ የዘር ፍጅት የሚቀስቅሱትን ልሂቃን በህግ ፊት ማቅረብ

ለ) የዲፕሎማሲና ሎቢ ኮሚቴ፣ ለውጭ መንግስታት፣ በአውሮፓ፡ በአሜሪካ፣ በካናዳ ለሚገኙ የፓርላማ ተመራጮች፣ የሴኔትና የኮንግሬ አባላት፣ የመንግስትና መንግስታዊ ተቋማት የጽንፈኞቹ የጥላቻ፣ የዘር ግጭት ቅስቀሳ ለሀገር ሰላም ፣ ለአፍሪቃ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት፣ ለህዝብ ስለምና ለተጀመረው የለውጥ እርምጃ ትልቅ አደጋ መሆናቸውን ማሳያአት፣ ማናገር፣ ማስጨበጥ።

ሐ) የሚድያ ኮሜቴ፣ በአለም አቀፍ ሚዲያዎች የጽንፈኞችን ውዥንብር ማጋለጥ በሶሻል ሚዲያ የጽንፈኞቹን ትርክትና ዘመቻ ለመቋቋም አንድ ቡድን ተቋቁሞ ስራ ይጀምራል ፣ ሃሙስ የበይነ መረብ ዘመቻ ይጀመራል። በየአለማችን ክፍል ያለ ሁሉ እንዲተባበር ጥሪ ቀርቧል

የትብብር ጥሪ ፥- በጽንፈኛ ሚዲያዎች በልሂቃን እንዲሁም በግለሰቦች የሚደረጉ የጥላቻ፣ የፍለጠው ቁረጠው መልክቶች በማሰባሰብ ለተቋቋመው የባለሞያዎች ቡድን መረጃዎችን በማጠናከር፣ በማደራጀት ፣ ለህግ ባለሞያዎች የሚያቀርብ በመሆኑ መረጃዎች በመላክ እንድትተባበሩ ጥሪ እናቀርባለን፣

ወደፊት ልዩ ልዩ የአለም አቀፉ ግብረሃይል አባላት በእነዚህ ዚሪያ አየቀረቡ ዝርዝር ማብራሪያዎች ይሰጣሉ።

በአነዚህ ተጨባጭ ተግባሮችና ስራዎች ዙሪያ ለመተባበር የምትፈልጉ ፣ አሳውቁን፣

የስልክ ቁጥር — 877 477 2544

በጽንፈኛ የኦሮሞ ልሂቃንና ሌሎች ብሄሮች እንወክላለን በሚሉ የሚተላለፉ የጥላቻና- የሽብር መልእክቶች-በምስል፣በሰነድ-ለህግ ለማቅረብ የመረጃ አሰባሳቢና የህግ ቡድኖች እንዲደርስ መረጃዎች እንድትልኩልን ጥሪ እናቀርባለን –

መረጃ ለመላክ የኢሜል አድራሻ የሚከተለው ነው፡ [email protected]Source link

Related posts

የሴቶችን ችግር በንግግር እና በመፈክር ብቻ ሳይሆን በተግባር መፍታት ይገባል -ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

admin

6ኛው ሀገር አቀፍ የፓራ ኦሎምፒክ ቅርጫት ኳስ ውድድር በባሕር ዳር ተጀምሯል፡፡

admin

በድሬዳዋ ከተማ በከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮጀክት ታቅፈው የነበሩ አባወራዎች ተመረቁ

admin