27.09 F
Washington DC
March 8, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ኅብረተሰቡ የአማራ ክልል የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አደረጃጀትና አሠራርን በመረዳት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀረበ፡፡

ኅብረተሰቡ የአማራ ክልል የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አደረጃጀትና አሠራርን በመረዳት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ ቀረበ፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 05/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክልሉ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ምንነትና አደረጃጀት አስመልክቶ ለማኅበረሰቡ ግልጽ በማድረግ ኅብረተሰቡ አደረጃጀቱን በመገንዘብ የሕገ-መንግሥቱ አጣሪ ጉባዔ ተጠቃሚ እንዲሆን ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

የአማራ ክልል የሕገ-መንግሥታዊ ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በብሔራዊ ክልሉ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 71 (1) መሠረት የተቋቋመ ነው፡፡ የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ 11 አባላት ያሉት ሲሆን የራሱ ሰብሳቢና ምክትል ሰብሳቢ እንዳለው የአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና የክልሉ ሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ አብዬ ካሳሁን በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ሰብሳቢው በሰጡት መግለጫም የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔዉ የአሠራር ሥርዓቱን ለመወሰን አዋጅ ቁጥር 225/2007 ዓ.ም ታውጇል፡፡ ለዚሁ አዋጅ ማስፈፀሚያ የሚሆን ልዩ ልዩ መመሪያዎችን በማዘጋጀት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ሥራዉን ለመጀመር የተሰጠዉን ተግባር እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡

የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ከአጣሪ ጉባኤ አባላት በተጨማሪ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ጥያቄዎችን የሚቀበል አንድ ሬጅስትራር እና አቤቱታዎቹን መርምረው የመነሻ አስተያየት ለአጣሪ ጉባኤው የሚያቀርቡ ሁለት መርማሪ የሕግ ባለሙያዎች አሉት ብለዋል፡፡

የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሥልጣንና ኃላፊነት፣ የክልሉ ሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በክልሉ ሕግ አዉጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ ወይም ሕግ ተርጓሚ አካላት ሂደቱን ጠብቆ የመጨረሻ ዉሳኔ፣ ፍርድ ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ ከተሰጠ በኋላ ከማንኛዉም ሰዉ የሚቀርብለትን የሕገ-መንግሥት ትርጉም ጥያቄዎችን ተቀብሎ ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ያስፈልገዋል ወይም አያስፈልገውም? በሚል የውሳኔ ሀሳብ ለኮሚስዮን የሚቀርብ የባለሙያዎች ስብስብ መሆኑን መግለጫው አትቷል፡፡

የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ በቀረበለት ጉዳይ በሚያደርገው ማጣራት የክልሉን ሕገ-መንግሥት መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የራሱን የውሳኔ ሀሳብ አዘጋጅቶ ለሕገ መንግሥት ተርጓሚ ኮሚስዮን ያቀርባል፡፡ ጉዳዩ የሕገ መንግሥት ትርጉም የማያስፈልገው ከሆነ ይህንን ወስኖ ለባለጉዳዩ ያሳውቃል፡፡ ባለ ጉዳዩም ይግባኝ ለኮሚስዩኑ የማቅረብ መብት አለው ይላል መግለጫው፡፡

የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ያከናወናቸው ተግባራት፣ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የተቋቋመው በሕገ መንግሥቱ ነው፡፡ ዝርዝር ሕግ የወጣው በ2007 ዓ.ም ነው፡፡ የክልሉ ሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሥራውን የጀመረው ደግሞ በ2008 ዓ.ም ነው፡፡ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ 14 የተለያዩ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ጥያቄዎች ቀርበውለት መመልከቱን የጉባዔው ሰብሳቢ ገልጸዋል፡፡ ከቀረቡለት ጥያቄዎች አራት አቤቱታዎች የሕገ-መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል የውሳኔ ሀሳብ በማስደገፍ ለመጨረሻ ዉሳኔ ለክልሉ ሕገ-መንግሥት ተርጓሚ ኮሚሲዮን እንደተላለፈ ፕሬዝዳንት አብዬ አስረድተዋል፡፡

በእነዚሁ አራት ጉዳዮች ኮሚሊየኑም ጉዳዩን በጥልቀት ካየና ከመረመረ በኋላ የሕገ-መንግሥት ትርጉም ያስፈልገዋል በማለት የአጣሪ ጉባዔዉን የዉሳኔ አስተያየት አጽንቷል ብለዋል፡፡ ሌሎች 10 አቤቱታዎች ደግሞ የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የሕገ-መንግሥት ትርጉም አያስፈልግም በማለት የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበባቸው ነበሩ ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ባደረጉት ገለፃ “አጠቃላይ የሕገ-መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሥራ ከጀመረበት ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድርስ የቀረቡ የሕገ-መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎችን ስንመለከት ከክልሉ ሕዝብ ብዛት እና ካለዉ የፍትህ ፍላጎት አንፃር በጣም ዝቅተኛ የሚባል ነዉ፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በክልላችን የሚገኘዉ ማህበረሰብ በክልሉ ዉስጥ የሕገ-መንግሥት ጉዳዮችን በማጣራት ትርጉም የሚሰጡ አካላት ስለመኖራቸው በቂ መረጃ የለውም፤ ግንዛቤም አልተፈጠረለትም፡፡ ይህ ደግሞ የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ወደ ተርጓሚ አካላት ሳይቀርቡ እንዲቀሩ ያደርጋል” ብለዋል፡፡ የጉባዔዉ ሰብሳቢ እንደተናገሩት በዚህ ምክንያትም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ የሆኑ ሕጎች፣ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች፣ የፍርድ ቤት ዳኝነቶች ጭምር ተፈጻሚ የሚሆኑበት አጋጣሚ ይኖራል፤ ህብረተሰቡም መብቱን መጠቀምና ማስከበር አይችልም ማለት ነው፡፡

“ለክልላችን ህዝቦች ግንዛቤ ለመፍጠር መሥራት፣ የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እና ዘዴዎችን ሁሉ በመጠቀም በክልሉ ሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ የውሳኔ ሀሳብ የሚያቀረብ እንዲሁም የሕገ መንግሥት ትርጉም የሚሰጡ አካላት ስለመኖራቸው ማስገንዘብ መፍትሔ ይሆናል” ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለአካባቢው ማኀበረሰብ የተለያዩ ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በመስጠት አለኝታነቱን እያሳየ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ፡፡

admin

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ጋር ተወያዩ

admin

የዲፕሎማሲ ስራዎችን በማጠናከር ወዳጅነትን ማብዛት ይገባል-ቋሚ ኮሚቴው

admin
free web page hit counter