51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ችግሮችን ለማለፍ ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡ችግሮችን ለማለፍ ጥንቃቄ የተሞላበት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 04/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በተለያዩ ችግሮች በተወጠረችበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ በሀገሪቱ ላይ
የተጋረጡት ፈተናዎች በአመዛኙ ሰው ሠራሽ ናቸው፡፡ የችግሮቹ ጠንሳሾችም ኢትዮጵያን ለማተራመስ የሚሹ የውጪ ጠላቶችና
የሀገራቸውን ሕልውና ለጥቅም አሳልፈው የሰጡ ጥቅመኞች ናቸው፡፡
በየክልሎችና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተዘረጋው የአጥፊዎች ቡድን በየጊዜው ጥፋት እየፈጸመ ይገኛል፡፡ እነዚህን ችግሮች
መከላከል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድርሻ ነው፣ በተለይ ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች በጥንቃቄ በመሥራት ሀገርን
የማዳን ኀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው ይታመናል፡፡ ሆቴሎችና የእንግዶች ማረፊያዎች እንግዶችን ሲያስተናግዱ ከፍተኛ
ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኀላፊ አበበ ባዬ (ዶክተር) ገልጸዋል፡፡
ባለቤቶችም ሠራተኞቻቸውን በትጋት እንዲሠሩ ማድረግ፣ አዲስ ተቀጣሪ ከሆኑም ማንነታቸውን በሚገባ ማወቅ ይጠበቅባቸዋል
ብለዋል፡፡
ምክትል ቢሮ ኀላፊው እንዳሉት እንግዶች ማንኛውንም አገልግሎት በሚጠይቁበት ጊዜ በተለይ አልጋ ሲይዙ አገልግሎት ሰጪው
አካል ማንነታቸውን ማወቅ ግድ ይለዋል፡፡ ለዚህም መታወቂያቸውን ማየት፣ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ እና ቅጂውን መያዝ
ያስፈልጋል፡፡ ይህም የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች ወንጀል ቢሠሩ ለመከታተል ይረዳል ነው ያሉት፡፡ ተገልጋዮች መሳሪያ፣ ሕገወጥ
ገንዘብ፣ የተለያዩ ሶፍት ኮፒዎችን እና የጥፋት መሣሪያዎችን ይዘው ሊገቡ ስለሚችሉ የሚያጠራጥር ሆኖ በተገኘ ጊዜ መፈተሽ
ይገባል ነው ያሉት፡፡ ከዚያም አልፎ ለፖሊስ ጥቆማ የማድረግ ኀላፊነት ተጥሎባቸዋል ነው ያሉት ምክትል ቢሮ ኀላፊው፡፡
ኢትዮጵያ ያለችበት ነባራዊ ሁኔታም ይሕንን ለማድረግ ያስገድዳል፡፡ ይህ ሀገርን የማዳን ሞራላዊ ግዴታ የማኀበራዊ አገልግሎት
ሰጭ ተቋማትንም ከጥቃት ይታደጋል ተብሎ በመርህ ደረጃ ቢታመንም ተግባራዊነቱ ጉራማይሌ ነው፡፡ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
የጋዜጠኞች ቡድን ከሰሞኑ ለሥራ በወልዲያ፣ ደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በተንቀሳቀሰበት ጊዜ አገልግሎት ሰጭዎች
የሚያሳድሯቸውን ሰዎች ማንነት የማያረጋግጡ፣ መታወቂያ የማይቀበሉ፣ ለዚሁ ተግባር ፎርም አዘጋጅተው ተግባራዊ የማያደርጉ
ማረፊያ ቤቶች መኖራቸውን ታዝቧል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት ተግባራዊ ያደርጉት እንደነበርም የሆቴል ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡ ምንም እንኳን የጥንቃቄ ምክሮቹን መተግበር
ተገቢ መሆኑን ቢገነዘቡም አሠራራቸው ወጥነት የጎደለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ግን አሳማኝ ምክንያት አላቀረቡም፡፡
በቀጣይም ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ እንደሚተገብሩም አስታውቀዋል፡፡
ምንም እንኳን ለእያንዳንዱ ነገር ደንብ ባይዘጋጅም አገልግሎት ሰጭዎች የመተግበር ግዴታ እንዳለባቸው የባሕልና ቱሪዝም ቢሮ
ምክትል ኀላፊው ተናግረዋል፡፡ የጥንቃቄ ተግባራቱን የሚያከናውኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መኖራቸውንም አመላክተዋል፡፡
ምንም እንኳን በተቋም ደረጃ ባይገመገምም በክልሉ በስፋት ያለመተግበር ችግሮች እንዳሉ አንስተዋል፡፡ ይሕም በግንዛቤ
እጥረት ሳይሆን ትኩረት ካለመስጠት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ይህንን ማስተግበር የቢሮው ተግባር በመሆኑ በሁሉም የከተማ
አስተዳደሮችና በዞኖች እንዲተገበር ይሠራል ነው ያሉት፡፡
እያንዳንዱ ግለሰብ እንቅስቃሴው በጥንቃቄ ሊሆን እንደሚገባ በአማራ ፖሊስ ኮሚሽን የማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል
መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ጀማል መኮንን አሳስበዋል፡፡ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተጨማሪ በተለይ አከራዮች ነዋሪዎችን
በሚከራዩ ጊዜ የተከራዮቻቸውን ማንነት በሚገባ ማወቅ እና የመታወቂያቸውን ቅጅ የመያዝ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡ ፖሊስም
ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የመስክ ምልከታ በሚደረግበት ጊዜ ወጥነት የሌለው አተገባበር
መኖሩን ጠቁመዋል፡፡
በዚህ መነሻነት የጥንቃቄ ርምጃዎች እንዲተገበሩ ከማድረግ ጀምሮ ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ይሠራልም ብለዋል
ኮማንደር ጀማል፡፡ ጉዳዩ ለጸጥታ አካሉ ብቻ የሚተው ከሆነ የጸጥታ ችግሮችን መከላከል እንደማይቻል በመጥቀስም
ለውጤታማነቱ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ በክልሉ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ የማኅበረሰብ አቀፍ የወንጀል
መከላከል ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡ ይሕም የፖሊስና የኀብረተሰቡን ግንኙነት በማጠናከር ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
ይሁን እንጂ በተለያዩ ምክንያቶች ተግባሩ በሚፈለገው ደረጃ አለማደጉን ነው ያስታወቁት፡፡ በቅርቡ በፌዴራል መንግሥት ደረጃ
የማኅበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል በገለልተኛ አማካሪ ቡድን እና በማኅበረሰብ የደኅንነት ፓትሮል እንዲደራጅ እየተሠራ
ነው፡፡ ይሕም በፖሊስና በማኅበረሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ውጤታማ የወንጀል መከላከል ሥራ እንዲኖር
ያስችላል ተብሏል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን የሚጠብቀው ተስፈኛው ወጣት፡፡

Source link

Related posts

በሳንፍራንሲስኮ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ያካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና የህዳሴ ግድብን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ

admin

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የባሕርዳር ሀገረ ስብከት ለመተከል ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ።

admin

መንግስት ለነዳጅ 24 ቢሊየን ብር ባለፉት ሁለት ዓመታት ድጎማ ማድረጉ ተገለፀ

admin