71.98 F
Washington DC
May 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ትህነግና የጥፋት የበኩር ልጁ ኦነግ-ሸኔ በሽብርተኝነት ለመፈረጅ የውሳኔ ሃሳብ መቅረቡ የሕዝብ ትግል እያሸነፈ ስለመሆኑ ምልክት ነው” የአማራ ብልጽግና ፓርቲ“ትህነግና የጥፋት የበኩር ልጁ ኦነግ-ሸኔ በሽብርተኝነት ለመፈረጅ የውሳኔ ሃሳብ መቅረቡ የሕዝብ ትግል እያሸነፈ ስለመሆኑ
ምልክት ነው” የአማራ ብልጽግና ፓርቲ
ፓርቲው በጉዳዩ ላይ ያወጣው ሙሉ መግለጫ ቀጥሎ ይቀርባል።
ትሕነግ ከፍጥረቱ ጀምሮ አማራን በጠላትነት የፈረጀ፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን የበታቹ ለማድረግ አልሞ የተነሳ በአያሌ
የንጹሃን ደም የሰከረ ድርጅት ነው፡፡ ከአፈጣጠሩ ጀምሮ በሥልጣን ጥመኝነቱም ሆነ አፍቅሮተ ንዋዩ ጸረ-ኢትዮጵያ እና ጸረ-ሕዝብ
ስለመሆኑ በወንጀል የከረፋው የድርጅቱ ታሪክ ህያው ምስክር ነው።
በተለይም የአማራን ህዝብ እንደ ቀዳሚ ጠላት ፈርጆ መነሳቱ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው፡፡ ሴረኝነት፤ ተስፋፊነትና
ተገንጣይነት የዚህ ድርጅት መገለጫ ባህሪያት ናቸው፡፡ ይሄን እውነታ ከትህነግ ማንፌስቶ ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ካለፉት ሃያ
ሰባት ዓመታት የአገአዛዝ ባህሪውና የተጠኑ ሴራዎቹ፤ ከሁለት ዓመት ተኩል ወዲህ ደግሞ እጁን የሰደደባቸው የሽብር ድርጊቶቹ
መረዳት ይቻላል፡፡ በሕዝብ ትግልና በፓርቲ የውስጥ መተጋገል ከማዕከላዊ ሥልጣኑ ከተነቀለ በኋላ 113 ግጭቶችንና የሽብር
ጥቃቶችን አድርሷል። በክልላችንም ሃያ ሦስት ያህል ግጭቶች ሲፈጠሩ በአሸባሪው ትህነግ የተቀነባበሩ ናቸው። የአገሪቱ ምሰሶ
የሆኑትን አማራን እና ኦሮሞን ለማጋጨት፣ በሐሰት ትርክት ቅራኔን በማፋፋም ሳያስበው ያጣውን ሥልጣኑን ማስመለስ ይመኝ
የነበረ መሰሪ ድርጅት ነው፡፡
ትሕነግ ከፖለቲካ ታሪኩ መረዳት እንደሚቻለው፣ ቅድመም ሆነ ድኀረ-1983 የሁለት ሀገረ-መንግሥት ዕይታ ያለው ድርጅት ነው፡፡
ይሄ ዕይታው የፖለቲካ መገለጫው ሆኖ ኑሯል፡፡ ከዚህ አመለካከቱ የሚመነጨው የፖለቲካ እንቅስቃሴው ‹ጸረ-ኢትዮጵያ› ባህሪ
እንዲኖረው አድርጎታል። ድርጅቱ የበላይ ሆኖ እስከኖረ ድረስ በሀገረ-ኢትዮጵያ ጥላ ስር ለመቆየት፣ ይህ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያ
ትፍረስ የሚል እኩይ ባህሪ ያለው ስለመሆኑ ባለፉት ሁለት ዓመታት ተኩል የተጓዘባቸው የሽብር ፖለቲካ መንገዶቹ ምስክር
ናቸው፡፡ ጥቅምት 24/2013 ምሽት ላይ በሀገረ-መንግሥቱ ዘብ ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው ክህደት በመፈጸሙ ዛሬ ለደረሰበት
አሳፋሪ ሽንፈት ምክንያት ሆኗል።
ባለመንታ ልቡ ትሕነግ እኩልነትን ለመቀበል የሚቸገር እብሪተኛ ድርጅት በመሆኑ ዛሬ አጋር የለሽ የተጠላና የተተፋ አሸባሪ ቡድን
ሆኖ ከሕዝብ ሊነጠል ችሏል፡፡
የትህነግ አመራሮች የፈሩትንና የጠሉትን የዳር አገርነት ፖለቲካ መቋቋም አቅቷቸው፣ ወደ መሀል ፖለቲካው ለመመለስ የቀውስ
አከፋፋይነትና የሽብር ስምሪት መንገድን ምርጫቸው ከማድረጋቸው አልፎ የማይነካውን ነኩ፤ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ እና
በጠገዴ ቅራቅር በኩል የአማራ ሕዝብ ላይ ጥቃት ከፈቱ። እናም የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሻ
አይቀጡ ቅጣት ቀጡት። በኢትዮጵያ ሕዝብ የአብሮነት ፍላጎትና በመንግሥታችን ብርቱ ጥረት አገርን ከፍርሰት ጠርዝ መታደግ
ተችሏል፡፡
ወታደራዊው ድል በፖለቲካውም ተደገመ፤ ትህነግና በርሱ አምሳል ያደራጀው ኦነግ-ሸኔ በግብራቸው እንዲጠሩና አስፈላጊው
ሕጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ በሚንስትሮች ምክር ቤት የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል። የውሳኔ ሀሳቡ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና
ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ 1176/2012 አንቀጽ 3 ስር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰነውን ትርጓሜ ሙሉ በሙሉ
የሚያሟሉ ወንጀሎች መፈጸማቸውን መሠረት በማድረግ ነው።
የዚህ እኩይ ድርጅት አመራሮች ‹‹የሕገ-መንግስት ጠበቃ ነን›› ሲሉ ቢከርሙም በጎን የሀገር መከላከያ ጦር ሰራዊትን የሚገዳደር
ክልላዊ ጦር ከመገንባት አልፎ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እስከመውጋት ደርሰዋል። የሕግ-ማስከበር ዘመቻው ከተጀመረ በኋላ
ባላቸው የውስጥና የውጭ ግንኙነት ኔትወርክ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተሰልፈው ሀገረ-መንግሥቱን ለመናድ በብርቱ
ሰርተዋል።
የእነርሱ ‹‹ሕገ-መንግሥታዊ ጥብቅና›› ለሥልጣን የበላይነት እንጅ ለእኩልነት እንዳልሆነ ራሳቸውን አጋልጠዋል፡፡ ጦረኝነት እና
ፌዴራሊስትነት የሚታረቁ ሃሳቦች እንዳልሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከገባው ቆይቷል፡፡ ክልልና ዓለምአቀፍ ድንበር ያልገደባቸው
ቀውሶችን በመፍጠር በሽብር ተግባር፣ ያጡትን ሥልጣን ተመልሶ ማግኘት እንደማይቻል የዛሬው የሚንስትሮች ምክር ቤት
የውሳኔ ሀሳብ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል።
የብሔር ጠበቃ በመምሰል ‹እውነትና መንገድ እኔ ነኝ፤ እኔን ተከተሉኝ› ቢልም ለሥልጣን መመለሻ ይረዱኛል በሚል ራሱ
ያደራጃቸው ‹‹የፌዴራሊስት ኀይሎች›› የሚባሉት ፓርቲዎች ሳይቀር አፍራሽ ሚናውን አውቀው ራሱ ከፈጠረው ‹‹ሕብረት››
መሰናበቱ፣ የሕግ ማስከበር ዘመቻው ከጀመረ በኋላም ከምርጫ ቦርድ የፖለቲካ-ፓርቲዎች ስም ዝርዝር መሰረዙ የሚታወስ ነው።
ይህ የውርደት ጉዞው ድምር ውጤት ለዛሬው ውድቀቱ ተደማሪ ኪሳራ ሆኖበታል። የቱንም ያህል መስዋዕትነት ተከፍሎ ሂደቱን
ጠብቆ ዛሬ ይህ ድርጅትና የጥፋት የበኩር ልጁ ኦነግ-ሸኔ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡን ተከትሎ፣ በቀጣይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ታሪክ የማይዘነጋው ታላቅ ውሳኔ ይወስናል የሚል እምነት አለን።
ይህ ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ የበላይ ሆኖ ለኖረ ድርጅት በቃላት ለመግለጽ የሚከብድ ፖለቲካዊ ኪሳራ ነው፡፡ ከሞት የበረታ ውድቀት
ነው።
በሌላ በኩል፣ የማያበራ ፀረ አማራነቱ ገፍቶት ኦነግ-ሸኔን ከመሰሉ የጥፋት የበኩር ልጆቹ ጋር ሆኖ አማራን በየአቅጣጫው
ቢያስወጋውም፣ የአማራ ሕዝብ አንድነቱን አጥብቆ ከሌሎች ወንድም ሕዝቦች ጋር በመሆን የሠላም ዘብነቱን አስመስክሯል።
ታሪክ ሰሪው ሰፊው ሕዝብ ነውና የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያውያን ጋር ሆኖ መስዋዕትነት እየከፈለ ሀገር
የማስቀጠል ሚናውን በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ እንደትህነግና የጥፋት የበኩር ልጆቹ ፖለቲካዊ ዓላማ ቢሆን የታሰበው ሌላ
ነበር፡፡
ትሕነግ እንደትላንቱ ሁሉ ዛሬም የፖለቲካ አቋሙ በአማራ ቁልቁለት የሚፀና የትግራይ ታላቅነትን ማንበር ስለመሆኑ በተግባራዊ
እቅስቃሴዎቹ አሳይቶናል፡፡ ይህ መንገዱ ለተከበረው የትግራይ ሕዝብ የማይጠቅም ብቻ ሳይሆን ከትግራይ የትላንት ቅድመ አገር
ገንቢነት ሚና፣ ከነ አጼ ዩሃንስ እና ከነ ራስ አሉላ አገራዊ ድል በተቃራኒ የቆመ ስለመሆኑ የተከበረው የትግራይ ሕዝብ የሚረዳው
እውነታ ነው፡፡
ይህ የሽብር ቡድን ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለትግራይ ሕዝብም አደጋ ስለመሆኑ ከጥቅምት 24 ምሽት ጀምሮ ያለው
እውነታ ይመሰክራል። ይህ የሽብር ቡድን የሕዝብ የመከራ ምንጭ ሆኖ መቀጠል የለበትምና መላ የትግራይ ተወላጆች ተፈላጊ
ወንጀለኞችን አሳልፈው እንዲሰጡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የትህነግና መሰሉ በሽብርተኝነት የመፈረጅ የውሳኔ-ሀሳብ ሲጸድቅ፣ በሕጉ በተቀመጠው አግባብ የሽብር ወንጀል ድርጊትን በተሻለ
ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል ይችላል። ውሳኔው በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ተጠያቂነትና የሕግ የበላይነትን ለማስፈን ትርጉም
ያለው ድርሻ ይኖረዋል። ትግራይና ትግራዋያንም በሂደቱ ከሚገኘው የሠላም ትሩፋት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
በሌላ በኩል የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረት
በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም
የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም የውሳኔ ሐሳቡ ተፈጻሚ እንደሚሆን የዉሳኔ ሀሳቡ ደንግጓል።
ስለሆነም ሁሉም ወገኖች ይሄንን እዉነታ ተረድተው በማወቅምሆነ ባለለማወቅ ከነዚህ ወገኖች ጋር ማናቸዉንም አይነት ግንኙነት
ከማድረግ እንዲቆጠቡ ስንል ምክራችንን እንለግሳለን።
በመጨረሻም!
ትህነግ በአማራ ደምና ሀብት ታላቋን ትግራይ የመመስረት እቅዱን ለማሳካት ሲል፤ አማራን ገድሏል፤ አኮላሽቷል፤ ሐብቱን
ዘርፏል፤ መሬቱንም ወራሯል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው ትህነግ በወልቃይት፤ ጠገዴ፤ ጠለምትና ራያ አማራዎች ላያ ያደረሰው
ግፍና በደል ነው፡፡ ዛሬም ድረስ የቀጠለው የጅምላ መቃብሮች ግኝት ይህ ድርጅት በአማራው ላይ ከሞት የበረታ ክፋት
ስለመፈጸሙ የጅምላ መቃብሮቹ ተጨባጭ ምስክር ናቸው። ይህ ጥፋት ላይደገመ ቀልብሰነዋል። በሕዝባችን ትግል፣ በመሪ
ድርጅቱ ቆራጥ አመራር አዲሱ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ለመድረስ በቅተናል።
የትህነግ እና ኦነግ-ሸኔ የሽንፈት ጉዞ ብሎም በሽብርተኛ ድርጅት ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው፣ የግማሽ ክፍለ ዘመኑ ፀረ-አማራ
የፖለቲካ ትርክት ለመሸነፉ የድል ምልክት ነው። ከፋፍለህ ግዛ፣ የሴራ ፖለቲካው ወደ መቃብር መውረዱ ለመላ የኢትዮጵያውያ
ብሔር ብሄረሰቦች ተጭኗቸው የቆዬው ቀንበር ለመሰበሩ የድል ምልክት ነው።
ትህነግም ሆነ ኦነግ-ሸኔ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው እኩልነትንና ወንድማማችነትን የማይቀበሉ፤ በድርጊታቸው የሽብር ወንጀልን
የዓላማቸው ማስፈጸሚያ የሚያደርጉ ጸረ-አማራና ጸረ-ኢትዮጵያ፣ የጥፋት ኃይሎች በመሆናቸው በሽብርተኝነት መዝገብ ውስጥ
እንዲገቡ የውሳኔ ሀሳብ መቅረቡ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለመላ ኢትዮጵያውያን ፋይዳው የላቀ ነው።
የኢትዮጵያን ልዖላዊነትና የግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅም ሆነ ሕዝቦቿን ከቀጥተኛ የህልውና አደጋ ተጋላጭነት ነጻ ለማድረግ
በመሰል የጥፋት ኃይሎች ላይ ቀጣይነት ያለው ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል። ይህ የውሳኔ ሀሳብም የሀገረ-መንግሥቱን
ህልውና የማስጠበቅ አካል ነው። በኢትዮጵያ ላይ እሳት እየለኮሱ ያሉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ከጥፋት ኃይሎች ጋር እየሞከሩ
ያለውን ትስስር በጊዜ ለመበጣጠስ ይረዳል። እውነታው ባይጠፋቸውም ትህነግንና መሰሎቹን በፖለቲካ ጫና፣ በሚዲያ
ፕሮፖጋንዳ፣…ለመደገፍ እየሞከሩ ያሉ የውጭ ኃይሎች አሸባሪዎችን እየረዱ ስለመሆኑ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ እንዲያውቀው
ለማድረግ ዕድል ይሰጣል።
እናም ለአማራ እና ለኢትዮጵያ የማይበርድ ጥላቻ ያለው ትህነግና የጥፋት የበኩር ልጁ የሆነው ኦነግ-ሸኔ በሽብርተኝነት
እንዲፈረጅ የውሳኔ ሀሳብ መቅረቡ የሕዝብ ትግል እያሸነፈ ስለመሆኑ ምልክት ነው።
በብዝሃነት ያጌጠችው ኢትዮጵያ በእውነተኛ ፌዴራሊዝም ብልጽግናዋ እውን ይሆናል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“ሕወሓት እና ሸኔን ሽብርተኛ ብሎ መሰየም አካፋን አካፋ የማለት ትክክለኛ ውሳኔ ነው“ ዶክተር አረጋዊ በርሄ የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

Source link

Related posts

በትግራይ ክልል እስካሁን 3 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ በማድረግ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ቀርቧል

admin

ኢትዮጵያውያን ምሁራን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ለመግባት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የሚቃወም ደብዳቤ ለፀጥታው ምክር ቤት አስገቡ

admin

የኮሚሽነር አበረ አዳሙ የሕይወት ታሪክ

admin