40.51 F
Washington DC
April 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ወደ ግንባታ እንዲገቡ የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 27/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በግለሰቦች ብቻ ሳይሆን በመንግሥት እና በተቋማት ጭምር ለልማት ተብለው
ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች በከተማዋ እድገት ላይ እንቅፋት መሆናቸውን ያነጋገርናቸው የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች
ነግረውናል። ነዋሪዎቹ ለቤተ መጽሐፍት ማዕከል ግንባታ ተብሎ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠውን ቦታ እንደ
ማሳያ አንስተዋል። ቦታው ለቤተ መጽሐፍት ግንባታ ከመጠየቁ በፊትም ለኳስ ሜዳ ተብሉ ያለምንም አገልግሎት ለ10 ዓመታት
ተከልሎ መቀመጡን ገልጸዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ቦታው ለቤተ መጽሐፍት ማዕከል ግንባታ ተብሎ በ2007 ዓ.ም የመሠረተ ድንጋይ ሲቀመጥ ይሠራል የሚል
ዕምነት ቢያድርባቸውም ዩኒቨርሲቲው በወቅቱ ወደ ሥራ ባለመግባቱ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል። መንግሥት በክልሉ የሚሠራቸውን
መሠረተ ልማቶች ጥራታቸውን በጠበቀ መንገድ በአጭር ጊዜ የመገንባት ኀላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል።
የደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ጎበዙ ማረው የባሕርዳር
ዩኒቨርሲቲ በ2007 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ለቤተ መጽሐፍት ማዕከል ግንባታ ቦታ የመሠረተ ድንጋይ አስቀምጦ እንደነበር
ነግረውናል፡፡ በ2012 ዓ.ም ቦታው የካሬ ሜትር ስፋት ማስተካከያ ተደርጎ እንደገና የቦታ ርክክብ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡ አቶ
ጎበዙ በዚህ ወቅት ከአጥር ግንባታ ውጭ የተሠራ ነገር የለም ብለዋል።
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቸሬ መስፍን (ዶክተር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲዎች አቅማቸው በፈቀደ
ልክ ለማሕበረሰቡ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተቋማትን የመገንባት ኀላፊነት ነበረባቸው፡፡ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲም
በደብረታቦር ከተማ አስተዳደር ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ሊሰጥ የሚችል የንባብ ማዕከል ለመገንባት በ2007 ዓ.ም የመሠረተ
ድንጋይ አስቀምጦ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ ዩኒቨርሲቲው የማዕከሉን የመሠረተ ድንጋይ ካስቀመጠ በኋላ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች
አነስተኛ ጥገናዎችን ካልሆነ በስተቀር ትልልቅ ግንባታዎችን ማከናወን እንዳይችሉ የሚከለክል መመሪያ በማውጣቱ ወደ ግንባታ
መግባት አልቻለም ብለዋል፡፡
አሁንም ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያው ዲዛይን ባይሆንም መመሪያውን ባልጣሰ መንገድ ባልተጋነነ ዋጋ ግንባታውን ለመገንባት
መፍትሔ አስቀምጧል ነው ያሉት፡፡ እንደ አልማ ያሉ የልማት ድርጅቶችን ለማሳተፍም እየሠሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
በመጀመሪያው ፕላንና ዲዛይን ለማጠናቀቅ ደግሞ ባለሀብቶች የተጠየቀውን የሥራ እና የዋጋ ዝርዝር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብላቸው
ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ዕቅዱም ተዘጋጅቶ ለዩኒቨርሲቲው የሥራ ኀላፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ብለዋል፡፡
ማዕከሉ 80 ሚሊዮን ብር ይጨርሳል ተብሎ ነበር፤ የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠው፡፡ ማዕከሉ የማኅበረሠቡን የንባብ ባሕል
ማዳበር ዓላማ ያደረገ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው ጥናት እና ምርምር የሚያደርግበት ማዕከል፣ ጥናትና ምርምር የሚያካሂዱ ባለሙያዎች
የሚያርፉበት፣ አዛውንቶች በአካባቢያቸው ጉዳዮች ላይ የሚመክሩበት፣ የልጆች የተረት መንገሪያ፣ የተለያዩ መሰብሰቢያ
አዳራሾችና ሱቆችን ያካተተ ማዕከል ለመገንባት ታስቦ ነበር የመሠረተ ድንጋይ የተቀመጠው፡፡
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleለ2013/2014 የመኸር እርሻ ወቅት 271 ሺህ ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

Source link

Related posts

በባሕር ዳር ከተማ በግማሽ ዓመቱ ከቱሪዝም ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።

admin

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ እስካሁን ድረስ 45 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክታቸውን እንዳስገቡ ተገለፀ፡፡

admin

ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር እሑድ ሊካሄድ ነው

admin