72 F
Washington DC
June 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ባለፉት ሦስት ዓመታት 56 ሽህ 790 የከተማና የገጠር ውኃ ተቋማት ግንባታ በማጠናቀቅ ከ15 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት 56 ሽህ 790 የከተማና የገጠር ውኃ ተቋማት ግንባታ በማጠናቀቅ ከ15 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ያለፉት ሦስት ዓመታት የውኃ፣ የመስኖ እና የኢነርጂ ዘርፍ ተግባራትን አመላክተዋል፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በውኃ፣ በመስኖ እና በኢነርጂ ዘርፍ

•ባለፉት ሦስት ዓመታት 56 ሽህ 790 የከተማና የገጠር ውኃ ተቋማት ግንባታ

በማጠናቀቅ 15 ሚሊየን 287 ሽህ 148 ነዋሪዎችን የንጹሕ መጠጥ ውኃ አቅርቦት

ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

•ባለፉት ሦስት ዓመታት ለከተሞች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት የሚውል 16 ቢሊየን ብር የብድር ፋይናንስ ከተለያዩ አበዳሪ ተቋማት በማሰባሰብ ለ72 ከተሞች የመጠጥ ውኃ አቅርቦት የሚውል የብድር ፋይናንስ ማቅረብ ተችሏል፡፡

•ጊቤ 3 የውኃ ማመንጫ (1 ሽህ 870 ሜጋ ዋት)፤ የገናሌ ዳዋ 3 የውኃ ማመንጫ (254 ሜጋ ዋት) እና የረጲ የደረቅ ቆሻሻ ማመምጫ (25 ሜጋ ዋት) ማጠናቀቅና ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጠቅላላ የማመንጨት አቅም 4 ሽህ 466 ሜጋ ዋት እንዲሁም 19 ሽህ 746 ኪሎ ሜትር ጠቅላላ ርዝመት ያላቸው የማስላለፊያ መስመሮች በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡

•የታላቁ ሕዳሴ ግድብ (79 ነጥብ 3 በመቶ)፤ የኮይሻ የውኃ ማመንጫ ግድብ (45 ነጥብ 8 በመቶ)፤ የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ (73.9 በመቶ)፤ የአሉቶ ላንጋኖ ጂኦተርማል (28 ነጥብ 3 በመቶ) የደረሱ ሲሆን፤ ለጎረቤት ሀገሮች የኃይል ሽያጭ ያሳልጣል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮ – ኬኒያ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር 97 ነጥብ 8 በመቶ ደርሰዋል፡፡

•ከ875 ሽህ በላይ ዜጎች የግሪድ አገልግሎት ሲያገኙ ከ1 ሽህ 100 በላይ የገጠር ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡

•የመንግሥት ወጭ ቅነሳ ጋር ተያይዞ ችግሮች የነበሩባቸውን ፕሮጀክቶች መፍትሔ በመስጠት 4 የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶች (የርብ፣ የጊዲቦ፣ የመቂዝዋይ እና የመገጭ ሰራባ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች) በማጠናቀቅ 32 ሽህ 400 ሄክታር በማልማት 56 ሽህ 946 አርሶአደሮች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

•ከለውጡ በኋላ ግንባታቸው እየተካሄደ የሚገኙ እና ለግንባታ በጨረታ ሂደት ላይ የሚገኙ 8 አዳዲስ (ካሊድዲጆ፣ የላይኛው ጉደር፣ ጨለጨል፣ ወልመል፣ የአጅማ ጫጫ፣ ወይቦ፣ አንገር ፣ ኬጦ) የመስኖ ግድብና የመስኖ አውታሮች ሲጠናቀቁ 52 ሽህ 192 ሄክታር በማልማት 104 ሽህ 384 አርሶአደሮች ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል፡፡

•እንቦጭን ከጣና ሐይቅ የማስወገድ ዘመቻ ከ 4ሽህ 302 ነጥብ 94 ሄክታር ውስጥ 3 ሽህ 656 ነጥብ 7 ሄክታር መሬት ማስወገድ ተችሏል፡፡ ይህም ከአጠቃላይ 85 በመቶ ማሳካት አስችሏል (የተሳተፈ የሰው ኃይል 396 ሽህ 943 (73 ነጥብ 4 በመቶ ሴቶች)

Source link

Related posts

“በቀጣይ አምስት ዓመታት የሚያስተዳድረኝን ፓርቲ ለመምረጥ ካርድ አውጥቻለሁ፤ሁሉም ዜጋ በቀሪው ሰዓት ካርድ በማውጣት መሪውን በካርድ ሊወስን ይገባል” 80 ዓመት አዛውንት

admin

የትግራይ ሕዝብ ከገጠመው ችግር እንዲወጣ የአፋር ሕዝብ ከጎናችን አልተለየም – ዶክተር ሙሉ ነጋ

admin

በያቤሎ ከተማ ከ172 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ለአግልግሎት በቅተዋል

admin