87.71 F
Washington DC
June 15, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጋዮች ጠየቁ፡፡በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጋዮች
ጠየቁ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የተቀላጠፈ አገልግሎት አሰጣጥ ችግር እና በቂ መድኃኒት አቅርቦት አለመኖር
ለወጭ እና ለእንግልት እያጋለጣቸው መሆኑን በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች
ገልጸዋል፡፡ በተለይም ደግሞ አንዳንድ ባለሙያዎች ሙያዊ ሥነ ምግባርን ባልተላበሰ መንገድ ደንበኛን አለማስተናገድ ችግር
እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡
በሆስፒታሉ በቂ የመድኃኒት አቅርቦት ባለመኖሩ በግል መድሃኒት ቤቶች እንደሚታዘዙ እና በዚህም ለከፍተኛ ወጭ መዳረጋቸውን
በሆስፒታሉ ተገኝተን ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች ገልጸውልናል፡፡ በተለይም ከውጭ መድኃኒት ቤቶች የገዙትን መድኃኒት በጤና
መድህን ለማወራረድ የሚያስችል ማረጋገጫ ከሆስፒታሉ ለማግኘት ችግር እንደሆነባቸው ነው ያነሱት፡፡
የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዐብይ ፍስኃ ከባለሙያዎች ሥነ ምግባር ጋር ለተነሳው
ጥያቄ ሆስፒታሉ ካለው ከፍተኛ የህሙማን ፍሰት እና የባለሙያ ቁጥር አለመጣጣም ጋር ተያይዞ በሚፈጠር የሥራ ጫና ያልተገባ
ባህሪ የሚያሳዩ እና እንግልት የሚፈጥሩ ባለሙያዎች እንደሚስተዋሉ አንስተዋል፡፡ በተደጋጋሚ ምክር ባላስተካከሉ ሦስት
ባለሙያዎች ላይ በሩብ ዓመቱ ርምጃ መወሰዱን ነግረውናል፡፡
ሌላኛው በሆስፒታሉ የተነሳው ችግር በቂ የመድኃኒት አቅርቦት አለመኖር ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁ እንዳሉት ሆስፒታሉ ለኢትዮጵያ
መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ያልከፈለው 28 ሚሊዮን ብር እዳ ምክንያት ኤጀንሲው የሚፈለገውን መድኃኒት እያቀረበ ባለመሆኑ
የአቅርቦት ችግር አጋጥሞታል፡፡ በዚህም ምክንያት ታካሚዎች ከግል መድኃኒት አቅራቢዎች በመግዛት ለከፍተኛ ወጭ እየተዳረጉ
እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡ በተለይም ደግሞ የጤና መድህን ተጠቃሚዎች የጤና መድህን ደብተራቸውን ብቻ ይዘው ወደ ህክምና
ስለሚሄዱ እንግልት እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነግረውናል፡፡ የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት ኤጀንሲም የማኅበረሰቡን ችግር
ተገንዝቦ የሚፈለገውን መድኃኒት ማቅረብ እንደሚገባ ነው የተናገሩት፡፡
በሆስፒታሉ የሚገለገሉ የጤና መድህን ተጠቃሚ ወረዳዎች የሚጠበቅባቸውን 15 ሚሊየን ብር በወቅቱ አለመክፈላቸው
ሆስፒታሉ ያለበትን እዳ እንዳይከፍል ፈተና እንደሆነበትም ሥራ አስኪያጁ አንስተዋል፡፡
ሆስፒታሉ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አለመሆኑ አገልግሎቱን ለማግኘት መቸገራቸውንም ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች አንስተዋል፡፡
አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ማኅበረሰብ እኩል አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ መተላለፊያ ቦታዎችን ምቹ የማድረግ
ሥራ እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አካል ጉዳተኞች ታሳቢ ያደረጉ ‹‹ሊፍቶች›› እና መወጣጫዎች እየተገነቡ መሆኑን አቶ ዐብይ
ገልጸዋል፡፡
ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሥነ ልቦና ጫና ሳይደርስባቸው እንዲገለገሉ የ‹‹ሴቶች አንድ ማዕከል›› በማቋቋም በሰለጠኑ
ባለሙያዎች አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንመ ገልጸውልናል፡፡ መስማት የተሳናቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችንም ከክልል ውጭ
በመላክ የተለያዩ ስልጠናዎች እያገኙ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሆስፒታሉን ችግሮች በራሱ ለመቅረፍ የሃብት አፈላላጊ ቡድን በማዋቀር ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ዘጠኝ
ኮንቴይነር የህክምና ግብዓቶችን አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በእርዳታ የማሟላት ሥራ እየተሠራ
ይገኛል ብለዋል፡፡
በሆስፒታሉ የማይሠጡ የህክምና አይነቶችን ደግሞ ከህንድ፣ ቻይና እና አሜሪካ ሀገራት የሚገኙ ሀኪሞች ወደ ሆስፒታሉ
በማምጣት በዘመቻ አገልግሎት እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
የክልሉ መንግሥት ሆስፒታሉ በሚያስተናግደው ህሙማን መጠን በጀት ሊመድብለት ይገባል ብለዋል፡፡ ሆስፒታሉ ለአራት
ዓመታት በነፃ ለታከሙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያወጣውን 96 ሚሊዮን ብር ወጭም በመመሪያው መሰረት የክልሉ መንግሥት
እንዲሸፍን ጠይቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleየአማራ ምሁራን መማክርት ያወጣው መግለጫ ፡፡
Next articleበአማራ ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የፌደራል መንግሥት አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር አሳሰቡ፡፡

Source link

Related posts

ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው

admin

በኒዮርክና አካባቢው ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ

admin

በአዲስ ዘመን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ።

admin