70 F
Washington DC
April 10, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአጼ ፋሲል እና የፈለገ አብዮት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማስፋፊያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የአጼ ፋሲል እና የፈለገ አብዮት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማስፋፊያ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 14/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአጼ ፋሲል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ እና ገጽታን የማሻሻል ሥራ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሙሉ ወጭ የሚሠራ ሲሆን ፈለግ አብዮት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ በትምህርት ቤቱ የቀድሞ ተማሪዎችና በአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) የሚሠራ ነው ተብሏል።

ሁለቱም ትምህርት ቤቶች ከተገነቡ ዘመናትን ያስቆጠሩና በጭቃ የተገነቡ በመሆናቸው ደረጃቸውን ለማሻሻል ፈርሰው በብሎኬት እንደሚገነቡ የአልማ የጎንደር ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡ የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ቄስ ልዑል አበበ እንዳሉት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወጪ የሚሰራው የአጼ ፋሲል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲዛይን ሁለት ህንጻዎች ያሉት ሲሆን ባጠቃላይ 12 መማሪያ ክፍሎች፣ ሁለት ቤተ ሙከራዎችና ቤተ መጽሐፍት ያካተተ ነው።

ግንባታውን ለማጠናቀቅ 13 ሚሊዮን ብር ወጭ ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል። እንደ ከተማ አስተዳደሩ መረጃ በጎንደር ከተማ አስተዳደር ካሉት አጠቃላይ ትምህርት ቤቶች 3 ነጥብ 6 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ደረጃቸውን ያሟሉ ናቸው። ከደረጃ በታች የሚገኙትን የትምህርት ተቋማትን በአልማ፣ በበጎ ፍቃደኛ ባለሀብቶችና በሕዝብ ተሳትፎ ወደ 50 በመቶ ደረጃቸውን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው።

በጎንደር ከተማ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል በዚህ ዓመት 77 ሚሊዮን ብር ማኅበረሰቡን በማስተባበር ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው። በዚህም የከፋ ጉዳት ውስጥ የሚገኙ 42 የትምህርት ተቋማትን ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ከከተማ አስተዳደሩ አልማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የአማራ ልማት ማኅበር (አልማ) ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታና የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሞላ መልካሙ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶክተር) እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኀላፊዎች በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡-ኃይሉ ማሞ- ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በምዕራብ ጉጂ ዞን የሠላም አማራጭ የተቀበሉ 436 የኦነግ ሸኔ አባላት ከህዝብ ጋር እንዲቀላቀሉ ተደረገ

admin

በባሕር ዳር ከተማ በግማሽ ዓመቱ ከቱሪዝም ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።

admin

በሳንፍራንሲስኮ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መንግስት ያካሄደውን የህግ ማስከበር ዘመቻ እና የህዳሴ ግድብን የሚደግፍ ሰልፍ አካሄዱ

admin