76.03 F
Washington DC
June 18, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በየመን በእስር ቤት ከሞቱት 43 ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ለመለየት መቸገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።በየመን በእስር ቤት ከሞቱት 43 ሰዎች ውስጥ ኢትዮጵያውያንን ለመለየት መቸገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ባሕር ዳር: መጋቢት 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) በየመን ሰንአ በእስር ቤት ከሞቱት 43 ሰዎች ውስጥ ምን ያክሉ ኢትዮጵያውያን
መሆናቸውን መለየት አለመቻሉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሳምንታዊ መግለጫው አሳውቋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ አንዳሉት በየመን ሰንአ አስርቤት ውስጥ በተነሳ
አለመግባባት ወደ እስርቤቱ አስለቃሽ ጭስ በመወርወሩ ቃጠሎ ለመነሳቱ ምክንያት ሆኗል። በዚህም 43 ሰዎች የሞቱ ሲሆን
ሰንአን የሚቆጣጠሩት የሁቱ አማጺያን በመሆናቸው የሟቾችን ማንነት መለየት አንደከበደ እና ቤተሰቦቻቸው አንዲለዩ ለማድረግ
ሙከራ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።
ቃል አቀባዩ በሳምንቱ የመሥሪያ ቤታቸውን አንቅስቃሴ ሲያብራሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ
መኮንን ከፊንላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሀቪስቶ ጋር በስልክ የሰሜን ኢትዮጵያ ጉዳይን በሚመለከት ውጤታማ ውይይት
አድርገዋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአውስትራሊያ፣ ሳውዲና ጋና
አምባሳደሮች መሾማቸውን እና የሥራ እንቅስቃሴዎቻቸውን በ100 ቀናት አቅደው እየተገበሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን ወደ መቀሌ ይዞ አንደሄደ የተናገሩት አምባሳደር ዲና በትግራይ ወቅታዊ
ሁኔታ በቂ እና ስኬታማ የሚባል ማብራሪያ መሰጠቱን ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የተደረጉ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰልፎች ውጤታማ እና ዜጎች
ምን ያክል የሀገራቸው ጉዳይ አንደሚያስጨንቃቸው ማሳያ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ተጽኖአቸውም መልካም እንደነበር አንስተዋል።
በትግራይ ክልል በሳምንቱ ለ4 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ማድረግ መቻሉን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ እንደገለጹት የህዳሴ ግድብን በሚመለከት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኀብረት እና
አሜሪካ ያደራድሩ የሚለው ሃሳብ በግብጽ እና ሱዳን እየተነሳ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከሦስት ወራት በፊት ድርድሩ የተቋረጠው
ሱዳን የታዛቢዎቹ ሚና ከፍ ይበል በማለቷ እና ግብጽ ባለመቀበሏ እንደነበርም አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የመርሆች ስምምነትን እና
የአፍሪካዊነት የውሳኔ አቅምን ብቻ አክብራ እንደምትንቀሳቀስ ገልጸዋል፡፡
አምዳደር ዲና በአየርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር መጠራታቸውን ተናግረዋል፡፡ ከአየር ላንድ መንግሥት እና ሕዝብ ጋር የቆየ
ግንኙነት እደነበር እና አሁን ጥሩ ምልክቶች እየታዩ አለመሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘም “አየር ላንድ ባለፈው የጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በተመለከተ ሲያነሳ የሀገሪቱ አንቅስቃሴ መልካም
ባለመሆኑ ይህንን አንቅስቃሴ ለማብራራት እና ለመጠየቅ ኢትዮጵያ አምባሳደሯን ወደ ሀገሯ ጠርታለች” ብለዋል አምባሳደር ዲና።
ዘጋቢ፡- አንዱዓለም መናን-ከአዲስ አበባ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበበጀት ዓመቱ ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠሩን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡
Next article“ሱማሌ ክልል አሁን ለደረሰበት ሰላም፣ልማትና እድገት መከላከያ ሰራዊታችን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል” የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

Source link

Related posts

በኢትዮጵያ የሂሳብ ሙያ ልማትን ይደግፋል የተባለ የ450 ሺህ ፓውንድ ፕሮጀክት እየተተገበረ ነው

admin

ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ምርጫ ያስፈልጋታል?

admin

የአማራ ሕዝብ የተጋረጡበትን ችግሮች ከሕዝብ ጋር በመተባበር ለመፍታት እንደሚሠራ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገለጸ፡፡

admin