71.89 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በዕኛ አገር ለአገር ኖረ ፣በስራ የተከበረ ኖሮ ያወዉቃል – ማላጂ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

ለመነሻየ መንደርደያ የሆነኝ  …ፀሃፊዉ ስለ ኪን ሠወች ሽልማት ያዩትን እና የታዘቡትን እንደነበር የተረዳሁ መሰለኝ፡፡

የቅድመ ሽልማት መመዘኛዎችን ዘርዝረዋል ፡፡ ይችን አስተያየቴን ለመሞነጫጨር አስከተነሳሁበት ጊዜ ድረስ ምንም መረጃ አልነበረኝም ፡፡ ግን ደግሞ ስለ እኛ አገር ሽልማት ከ18ኛዉ ክ/ዘ አስካሁን ስላለዉ ብርቱ እና ብሄራዊ ፈርጥ የሆኑ ዘመን ተሸጋሪ የአገር እና የኣለም ባለዉለታ ኢትዮጵያዉያን  ዕዉቅና እና ሽልማት መስጠት አይደለም አትበል የተባለዉን ዝም ፤ይሁን / በል የተባለዉን እንደወረደ አሜን በሚል በይሉኝታ እና በአድር ባይነት ተቀፍድደን ባለን ማህበረሰብ ባህል ዉስጥ መኖራችንን መርሳት ሳይሆን በዕቢተኝነት ለነጻነት መኖርን መከተል አለብን፡፡

ለብሄራዊ አንድነት ፣ሉዓላዊነት  እና ዕኩልነት የህይዎት መስዋዕት የከፈሉትን እና ለዛሬ የጋራ አገራችን ነጻ ምድር እና ዜጎች ላበቁን ዕንቁ ታላላቅ ቀደምቶችን መታሰቢያ በስማቸዉ ለማድረግ ብርክ የሚይዘን ዕኮ ነን ፡፡

በየትኛዉ ቀደምት የኢትዮጵያ ነገስታት፣ መሪዎቻችን፣ ጀግኖቻችን ትንሹን መታሰቢ ለማድረግ ተስማማን ሳይሆን ዕዉነት ለምን ብለን እናዉቃለን ?

እንደ አሸን  ከፈሉት ከፍተኛ ት/ት ተቋማት እንኳን ከዋኖቻችን በአንዱ ሰይመናል፣ የምርምር ማዕከል ሰይመናል፣ የታሪክ መማሪያ እና የማንነት መግለጫ ሀዉለት  መዲናችን ላይ አቁመናል ?

የኋለኞችን እና የአገር ባለዉለታወችን በርግጥ በአደባባይ ስለሰሩት ተጋድሎ እና ብሄራዊ ኩራት በልበ ሙሉነት ለመናገር የሚችል ስብዕና አለን ?

የእኛ /ኢትዮጵያዉያን መሪዎች እና የቁርጥ ቀን ሰዎች እንኮ ለአካባቢ እና ለብሄር አልኖሩም አልሞቱም ፤ብሄርም ቤተሰብም አልነበራቸዉም ለነሱ ህዝብ ፣ወገን እኛ የህዝብ ልጅ ሆነዉ የህዝብ እና የአገር ቤተሰብ ቤዛ የሆኑ ነበሩ ፡፡

ዛሬ እነርሱ የህይዎት ዋጋ ለከፈሉልን የነሱን በጎ ስራ ለማዉሳት የእኛን ቤተሰብ ፣ ጓደኛ እና ሲለጥቅ ብሄር ላለማስከፋት ዕዉነትን ለመመስከር አንፈልግም ፡፡ እኮ እንዴት ፣መቸ እና የት ነዉ የሰራ እና ለአገር ኖሮ በአገሩ ለሞተ ምስክርነት የሰጠንዉ ፡፡

ይህስ ክፉ ልማድ እንዴት ይወገድ ዕዉነት ለመናገር በይሉኝታ እና አድርባይ ልጓም ራሳችንን አፍነን፡፡

ኮከብ አርሶ አደር……..ሳይሰራ  የሚያወራ

ኮከብ ነጋዴ /ባለሀብት……ሳይነግድ/ ሳይሰራ በመዝረፍ የሚያተርፍ፣

ምሁር ወረቀት ካለዉ…..ተቀመጥ በወንበሬ ፤ተናገር በከንፈሬ የሚባል ባለግንጥል ጌጥ ከሆነ፣

የኪን ሠዉ የሚዘፍን ፣የሚያሞግስ እንጅ ጥበብን የሚል …..ዕገሌን ያየ በሚባልባት አገር ገና የሚቀሩን ስለመኖራቸዉ ዛሬ ባንስማም ነገ በዉጤቱ አብረን ዋጋ እንጠየቅበታለን ፡፡

አስኪ ስለ ቴዲ ….ትንሽ ልበል ዕዉነት ከዓመታት በፊት የክብር ዶክተርነት ሊሰጣቸዉ ከሚገቡ የአገራችን ሠዎች  አንዱ እና ዋነኛዉ ቢሆን ምንድን ነበር የሚሆነዉ ፡፡

አገር ከሞላ የክብር ….ማዕረግ ለእንዲህ አይነት  የአገርን እና ዉልድን የቀደመ ፣የአሁን እና የመጪ ዘመን ብሩህ የኪነት ባለሙያ/ ድምጻዊ፣ አርበኛ፣ ነብይ፣ ብልህ እና በሳል ሠዉ አለማድነቅ በራሱ ከፋት እንጅ ሌላ ሊባል አይቻልም ፡፡

ሌላዉን ትተን ለብሄራዊ ለዉጥ እና ለተገኘ የነጻነት ከፍተኛዉን እና ዋናዉን ድርሻ በሙያዉ ህዝብን እና ተዉልድን በማንቃት፣ በማስተማር ፣ ታሪክን ከተዉልድ ከማስተሳሰር….ዕኮ ማን ይሆን እንደ ቴዲ …..?

በኪን ለህዝብ እና ለአገር በቅንነት ፣በብቃት፣ በድፍረት፣ በአርቆ ተመልካችነት …ከቴዲ በላይ እኮ ማን ይሆን ፡፡

ማን ነበር ዕስር ፣ዕንግልት በበጎ ስራዉ መከራ ያየዉ….እናም የበጎዎች እና የጀግኖች ሽልማት ዘመን ተሸጋሪ ስራቸዉ ፣ ለህዝብ እና ለአገር የከፈሉት እና ያበረከቱት ስራ እና የዚህ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ብቻ ናቸዉ ፡፡

እኛ አገር ኮሚቴ  ከሚሰራዉ ስራ ብዙ መጠበቅ ስህተትን በስህተት ለማስተካከል እንደመሻት ነዉ ፡፡

ሁሉም የኪነ ጥበብ ሰዎቻችን  እናከብራቸዋለን እንወዳቸዋለን እንኳን … አገር ቢሸለሙ ደስተኞች ነን ግን ከእኛ ይልቅ ላገር እና ለህዝብ የኖሩ ፣የሞቱ…..አሉን እና እነርሱን እናመስግን ፣ እንሸልም፣ እናዉሳ፣ አንርሳ እንዲሉ እና ሽልማትም ለሠራ በስራዉ ልክ ዋጋ እንደሚገባዉ ለማመስከር ነዉ ፡፡

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ታፍራ እና ተከብራ ለዘላምትኑር

ማላጂ

Source link

Related posts

በአምባሳደር ምስጋኑ አረጋ አስተባባሪነት ከ36 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

admin

ምርጫ ቦርድ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል-10 የዕጩዎችን የምዝገባ ሂደት ተመለከተ

admin

ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ኢትዮጵያ የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት አስጀመረ

admin