63.7 F
Washington DC
June 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በኢትዮጵያ የጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች (ስታርትአፕስ) የሚፈጥሩት የሥራ እድል እያደገ መምጣቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በኢትዮጵያ የጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች (ስታርትአፕስ) የሚፈጥሩት የሥራ እድል እያደገ መምጣቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

ባሕር ዳር: ግንቦት 12/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የዱባይ የንግድ ምክር ቤትና ኢንደስትሪ፣ ከዱባይና ሰሜን ኢሚሬትስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ አካል የሆነው የዲጂታል ቴክኖሎጂ የበይነ መረብ ውይይት ተካሂዷል።

ውይይቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች (startups) ፣ በወጣት የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችና ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው።

የዱባይና ሰሜን ኢሚሬትስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል አምባሳደር እየሩሳሌም አምደማርያም ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ለመገንባት የሚያስችላትን መደላድል እየፈጠረች መሆኑን ተናግረዋል።

ግብርና፣ የማምረቻ ዘርፍ፣ ቱሪዝምና የአገልግሎት ዘርፍ ላይ ቅድሚያ የተሰጠው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂና ሌሎች አስቻይ ሁኔታዎች እየተፈጠሩ ነው ብለዋል።

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ 2025 ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር) በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና የዘርፉ ሥራ እድል ፈጠራ እያደገ መምጣቱን ተናገረዋል።

የዘርፉ ማነቆዎችን የሚፈቱ የትራንዛክሽን አዋጅ እንዲፅደቅ፣ የኢኖቬሽን ፈንድ አዋጅ ወደ መጠናቀቅ መቃረቡና ሌሎች አስቻይ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ልዩ ልዩ ተግባራት ተከናውነዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ሥራ ፈጠራ በፍጥነት እያደገ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

የዱባይ ንግድ ምክር ቤትና ኢንደስትሪ የዓለም አቀፍ ቢሮ ዳይሬክተር ኦማር ካህን ኢትዮጵያ ለሥራ ፈጣሪዎችና ለጀማሪ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ወሳኝ ሰዓት ላይ ትገኛለች ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ ሜሪያም ሰይድ የበይነ መረብ ግንኙነት ችግር ለመፍታት ኢትዮጵያ የቴሌኮምን ዘርፉን በከፊል ወደ ግል የማዞር ሥራ በሂደት ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

የበይነ መረብ ግንኙነት መሰረተ ልማት፣ የዲጂታል እውቀትና የዲጂታል ኢኮኖሚ አስቻይ ሁኔታዎች ላይ በመድረኩ ወይይት መደረጉን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ኢዜማ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላን አስመልክቶ ያደረገውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ

admin

ማይክሮሶፍት ለዊንዶውስ ተጠቃሚዎች ወርሃዊ የደህንነት ማዘመኛ ለቀቀ

admin

ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ስራ የተመደበ ገንዘብ ያለአግባብ ጥቅም ላይ ያዋሉ ሀላፊዎች በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

admin