67.32 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በአጣዬና አካባቢዉ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በአጣዬና አካባቢዉ የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር: ግንቦት 05/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአጣዬ ከተማ አስተዳደርና በአጎራባች አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረዉ ጥቃት ከ253 ሽህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን አስተዳደሩ አስታዉቋል፡፡ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራ እየተሠራ ነዉ ተብሏል፡፡

የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገዉ ጥረት ከእለት ደራሽ ምግብ ጀምሮ በዘላቂነት ኑሯቸዉን መምራት የሚችሉበት እርዳታና ድጋፍ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በሰሜን አሜሪካ የክርስቲያናዊ ሕብረት ድርጅት በሀገሪቱ ችግር ለደረሰባቸዉ ወገኖች እርዳታ ልኳል፡፡

ድጋፉን ይዘዉ ወደ ኢትጵያ የመጡት በሰሜን አሜሪካ የካሊፎርኒያና አሪዞና ግዛት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዱሱ አባል ብፁዕ አቡነ ቲዎፍሎስ በዜጎች ላይ የደረሰዉ መከራ ከባድ ነዉ ብለዋል፡፡

በአጣዬና አካባቢዉ ለተፈናቀሉ ወገኖች ለቤት መሥሪያ የሚሆን ከ4 ሽህ 600 በላይ ቆርቆሮም ድጋፍ አድርገዋል፡፡

ድጋፍ የተደረገዉ የቤት መሥሪያ ቆርቆሮ የ150 አባዎራዎችን መኖሪያ ቤት እንደሚገነባ ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ በርካታ አካባቢዎች በሰላም እጦት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ሕብረቱ እየሠራ ነዉ ብለዋል፡፡

በትግራይ፣ ከመተከል ዞን ተፈናቅለው ቻግኒ ለሚገኙና በሌሎችም አካባቢዎች ለተጠለሉ ወገኖች እርዳታ ማድረጋቸዉን የገለጹት ሊቀ ጳጳሱ ለአጣዬ ተፈናቃዮች የተደረገዉ ድጋፍ የመጀመሪያ በመሆኑ በቀጣይ ሌሎች ድጋፎችም ይደረጋሉ ነው ያሉት፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃድቅ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ አካባቢያቸዉ እንዲመለሱ ለማድረግ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በበኩላቸዉ በዞኑ ከ253 ሽህ በላይ ወገኖች ተፈናቅለዉ በአጎራባች አካባቢዎች ይገኛሉ ብለዋል፡፡ አሁን ላይ የመኖሪያ ቤት ጉዳይ አንገብጋቢዉ ጉዳይ ነዉ ያሉት ኃላፊዉ ለዚህም ጉዳት የደረሰባቸዉን ወገኖች የመለየትና ቤት ገንብቶ ለማቋቋም እየተሠራ መሆኑን አስገንዝዋል፡፡

ከጥቃቱ ሸሽተዉ በተለያዩ ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢዎች የሚገኙ ወገኖችም ቤት መገንባትን ጨምሮ ሌሎች ተግባራት እየተጀመሩ ስለሆነ ወደ ቀያቸዉ ተመልሰዉ አጋዥ ተግባራትን እንዲፈጽሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከአሜሪካ የመጡት የሃይማኖት አባቶች በደብረ ብርሃን ከተማ ጊዜያዊ መጠለያ ዉስጥ የሚገኙ ተፈናቃዮችን አጽናንተዋል ፤ በቀጣይም ከጎናቸዉ እንደማይለዩ አረጋግጠዉላቸዋል፡፡

ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎች በህዳሴ ግድብና በውጭ ጣልቃ ገብነት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ

admin

ዜጎች የምርጫ ካርድ ወሰደው ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን እንዲጠቀሙና ነጻ እና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ፡፡

admin

ካናዳ 132 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ለአየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ልታበረክት ነው፡፡

admin