52.39 F
Washington DC
February 25, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በአማራ ክልል 7 ከተሞች ወደ ከተማ አስተዳደርነት አደጉ፡፡

በአማራ ክልል 7 ከተሞች ወደ ከተማ አስተዳደርነት አደጉ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 20/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል መሥተዳደር ምክር ቤት የ7 ከተሞችን ደረጃ ሽግግር አፅድቋል።

ምክር ቤቱ በአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ተጠንተው የደረጃ ሽግግር እንዲደረግላቸው የቀረቡ 7 ከተሞችን ደረጃ ሽግግር አፅድቋል። ወደ ከተማነት ካደጉት ውስጥ ቲሊሊ፣ ወገልጤና፣ ሃራ፣ አምደወርቅ፣ ቱለፋ፣ ጨፋሮቢት እና ሰንበቴ ከተሞች ናቸው፤ ሁሉም ከተሞች ከመሪ ማዘጋጃ ወደ ከተማ አስተዳደር ደረጃ ተሸጋግረዋል።

የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በሰላም ይመኑ እንደተናገሩት አንድ ከተማ ወደ ከተማ አስተዳደርነት እንዲያድግ በከተማው የሚኖረው የሕዝብ ብዛት 25 ሽህ እና በላይ ከሆነ፣ በከተማው የሚሰበሰበው አማካይ ዓመታዊ ገቢ በተለይም ከመሬት ሊዝ ሸያጭ ውጭ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና በላይ ከሆነ፣ የነዋሪዎች መተዳደሪያ በከተማው ውስጥ ከሚኖረው ጠቅላላ ሕዝብ 60 በመቶ እና በላይ የሆነው ከግብርና ውጭ በሆኑ የሥራ መስኮች የተሠማራ ከሆነ፣ ከተማው ለኢንቨስትመንት ያለው ምቹነት፣ አመች የትራንስፖርት ያለው፣ በተመረጡ የልማት ኮሪደሮች ለልማት ማዕከልነት የተመረጡ እና ለቱሪስት ሃብት አመች የሆኑ መስፈርቶችን የሚያካትት ከሆነ ነው፡፡

ከተሞቹ ወደ ከተማ አስተዳድርነት አደረጃጀት መዋቀራቸው ለነዋሪዎች ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም ለመቀነስ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ባካሄደው ጥናት ቲሊሊ፣ ወገልጤና፣ ሃራ፣ አምደወርቅ፣ ቱለፋ፣ ጨፋሮቢት እና ሰንበቴ ከተሞች ወደ ከተማ አስተዳድርነት እንዲያድጉ መወሰኑን ነው አቶ በሰላም ያስረዱት፡፡

አንድ መሪ ማዘጋጃ ቤት ወደ ከተማ አስተዳድርነት ሲያድግ ለቢሮ መሰረተ ልማት፣ የሰው ኃይልና በጀት ያስፈልጋል፤ እነዚህን ወጭዎች በመንግሥት አቅም ብቻ ማሟላት ስለማይቻል ህብረተሰቡ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበትም አስገንዝበዋል፡፡

በአማራ ክልል ከከተማ አስተዳድርነት ጥያቄ በተጨማሪ 5 ከተሞች ወደ የሪጂኦፖሊታንትነት የማደግ ጥያቄ በማቅረባቸው የክልሉ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጥናት አካሂዷል፤ ጥያቄውን ያቀረቡት ደብረ ታቦር፣ ወልድያ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረ ብርሃን እና ኮምቦልቻ መስፈርቱን ሲያሟሉ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ እንደሚፀድቅም የሕዝብ ግንኑነት ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

ቢሮው ከተሞች ጥያቄ ስላቀረቡ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ቁጥራቸውን፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴቸውን እና ሌሎች መስፈርቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት እንደሚሠራም ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሸምስያ በሪሁን

ፎቶ፡- ከአማራ ክልል ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የፓርላማ አባላት የአየር ኃይል አባላትን እና ሠራተኞችን አወያዩ

admin

የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች ገለልተኛ የመንግሥት ተቋማት በሚፈጠርበት ሁኔታ በጅግጅጋ ከተማ እየመከሩ ነው

admin

አብይ፣ ለማና የጃዋር ካልኩሌተር (አበበ ገላው)

admin