45.68 F
Washington DC
February 27, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በአማራ ክልል የቆላ ስንዴን ለማልማት ከታቀደው 24 በመቶው በዘር መሸፈኑን ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡

በአማራ ክልል የቆላ ስንዴን ለማልማት ከታቀደው 24 በመቶው በዘር መሸፈኑን ግብርና ቢሮ ገለጸ፡፡

የዘር እጥረት ለዕቅዱ አለመሳካት እንደ አንድ ምክንያት ተቀምጧል፡፡

ባሕር ዳር፡ የካቲት 09/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአማራ ክልል የቆላ ስንዴን በአንደኛ ዙር መስኖ ለማልማት ከታቀደው 50 ሺህ 200 ሄክታር መሬት በአሁኑ ወቅት ከ17 ሺህ 500 ሄክታር በላይ መሬት መታረሱን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ተስፋሁን መንግስቴ ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ ደግሞ 12 ሺህ 99 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል፡፡ ይህም የቆላ ስንዴን ለማልማት በክልሉ ከተያዘው ዕቅድ አፈጻጸሙ 24 በመቶ ነው፡፡ በዚህም 29 ሺህ 435 አርሶ አደሮች እያለሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ቆጋ፣ ጃዊ እና ቆቦ ጊራና ደግሞ የተሻለ የልማት እንቅስቃሴ እየተከናወነባቸው ይገኛሉ ብለዋል ምክትል ቢሮ ኃላፊ፡፡

ይሁን እንጅ የዘር አቅርቦት ችግር ለዕቅዱ አለመሳካት በምክንያትነት ተቀምጧል፡፡ በክልሉ የሚያጋጥመውን የዘር እጥረት ለመቅረፍም የክልሉ መንግሥት 23 ሺህ ሄክታር መሬት ለዘር ብዜት መሥጠቱን ኃላፊው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል የቆላ ስንዴን ለማምረት የሚያስችል ሰፊ፣ ለም መሬት እና ከፍተኛ የውኃ አቅም አለው። ምዕራብ ጎንደር፣ ጃዊ፣ ቆቦ ጊራና፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም እንዲሁም ማዕከላዊ ጎንደር የቆላ ስንዴን ለማምረት እምቅ አቅም ያላቸው አካባቢዎች መሆናቸውን ምክትል ቢሮ ኃላፊው ለአብነት አንስተዋል።

ኢትዮጵያ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ በዓመት ከውጭ እንደምታስገባ ግብርና ሚኒስቴር በዚህ ዓመት መጀመሪያ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በዚህም ሀገሪቱ በዓመት 1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጭ ታደርጋለች፡፡ ከውጭ የሚገባን ስንዴ ከ50 በመቶ በላይ ለመቀነስም በ2013 ዓ.ም በሀገሪቱ 300 ሺህ ሄክታር መሬት ስንዴ በመስኖ ለማልማት መታቀዱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል ደግሞ 50 ሺህ 200 ሄክታር መሬት የቆላ ስንዴን በመስኖ በማልማት 2 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት እየተሠራ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሰራ

ፎቶ፡- ከድረ ገጽ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ዝክረ ዓድዋ ዝግጅት የሁሉም አፍሪካውያን መሆን እንዳለበት በዩጋንዳ ማኬሬሬ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ምሁር አስገነዘቡ፡፡

admin

የኢትዮጵያን የአለም አቀፍ ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት ደረጃን ለማሻሻል የዩኒቨርሲቲዎችን ሙሉ አቅም መጠቀም እንደሚገባ ተገለፀ

admin

የባቡር ሀዲድ ሲዘርፉ የነበሩ ዘጠኝ ግለሰቦች ተያዙ

admin