87.71 F
Washington DC
June 15, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
News

በአማራ ክልል ውስጥ የህወሃትን ቦታ ሸፍነው የሚሰሩ የብአዴን አመራሮች ((እነ በረከት፣ አዲሱና የመሳሰሉት)

አያሌው መንበር

በአማራ ክልል ውስጥ የህወሃትን ቦታ ሸፍነው የሚሰሩ የብአዴን አመራሮች ((እነ በረከት፣ አዲሱና የመሳሰሉት) “#መገለልና #መድሎ እየደረሰብን ነው” ማለታቸው ተሰምቷል።

እኔም ታድያ እኔስ አላማየ ምን ሆነና? በዋናነት ቅድሚያ የምሰጠው የህወሃት ፈረስን (የጎንደር አማራ ፖስተኛ ብሏቸዋል በአንድ ወቀት) #ከአማራ_ህዝብ መነጠል ነው ብያለው።

ያለ ድርጅቱ አሰራር በህወሃት ግብዣ የኢህአዴግ ስራ አስፈፀሚ ስብሰባ እለት የተገኙ ነባር አመራሮቹና አሁንም በስልጣን ላይ ያሉ አመራሮች በስራ አስፈፃሚው ስብሰባ ወቅት ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ “እኛ የተለየ ትኩረት እየተደረገብን በአመራሮች እና በህዝቡ ዘንድ #እንዳንታመን_ሁነናል የሚል ነው።”

ይህንን ያሉት የአማራን ህዝብ በህወሃት አጭር ገመድ አንገቱን አስረው እንዳይራመድ፣ እንዳይበላና እንዳይጠጣ ለጉመውና ቀፍድደው ይዘውት የኖሩና በቅርብ ግን ለህወሃት ይሰራሉ፣ ታዛዥ ናቸው እየተባለ በማስረጃ እየተደገፈ በተሰራ ስራ በከፊልም ቢሆን የተገለሉ አመራሮች ናቸው።

እነዚህ አካላት ከላይኛው እስከ ታችኛው አመራር እንዲሁም በመላው የአማራ ህዝብ ድረስ ተጽኖ እየደረሰባቸው መሆኑንና የአመራር ስራቸውን እንዳይሰሩ እንቅፋት እንደተፈጠረባቸው ታናግረዋል።ይህንን ሀሳብ አለምነውም ይጋራዋል ተብሎ ይጠበቃል።ተደጋግሞ ከሱዳን መሬት ጋር ስሙ የሚነሳው ደመቀ መኮነንም (ይህ ስም ያለ በቂ ማስረጃና ምክንያት መለጠፉ ይታወቃል) ይህንን ሀሳብ መጋራቱ አይቀርም።ህወሃት ይህንን ሀሳብ ሆን ብላ ነው የመዘዘችው።

((ባለፈው የመብራት ችግርን በተመለከተ በኢህአዴግ ዘመን የአማራ ህዝብ ምንም አይነት መብራት በአዲስ መልክ እንዳልገባለት መገለፁ ይታወሳል። እንኳንስ ከሌላው ከጣና በለስ ሀይል ማመንጫ እንኳን አንድ ሜጋ ዋት እንዳልተጠቀመ በግልፅ በሚዲያ መነገሩን ተከትሎ “አመራሩ ለህወሃት ሲታዘዝ ነው የኖረው” የሚለውን ሀሳብ ለምን በአንድ ማስረጃ ታጋልጡናላችሁ? በሚል ለዚህም የCounter attacking መልስ በመብራት ሀይል በኩል መመለሱ ይታወሳል።
አሁን ህወሃት “አዲሱ የብአዴን አመራር ለአማራ ህዝብ በደል ነባሩን አመራር ተጠያቂ እያደረገ እናንተን እንድትገለሉ እያደረገ ነው” የሚል ማሸነፊያ ስልት በመምዘዝ ጃዝ ቡች ብላለች።”አመራሩ ከህዝብ ተነጥሏል” የሚለውን ሀሳብ በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ የሆነው አለምነው መኮነንና እስከ ቅርብ ጊዜ የህወሃት የምግብ ሳህን ሆኖ የቆየው ደመቀ መኮነንም መጋራታቸው አልቀረም።በአቋም ደረጃ በግልፅ ባይታወቅም ከእነ ገዱ አስተሳሰብ ለመነጠል ግን ህወሃት ጥሩ ስልትን ነው ያመጣችላቸው።እነ ገዱና አጠቃላይ አዲሱ የብአዴን አመራርም ሊይዘው የሚገባው አቋም “አዎ አሮጌው የብአዴን አመራርማ የአማራን ህዝብ ለስቃይ የዳረገ፣ የህወሃት አገልጋይ፤ የአማራነት ስሜት የሌለው፣ ፖስተኛ ነው” የሚል #የማይናወጥ_አቋምን ነው።

ህወሃት በዚህ ስልት አመራሩን ከከፋፈለች በኋላ በክፍል ሁለት ይዛው የመጣችው ነገር ብአዴን ((“#የዘቀጠሀሳብ #አራማጆችን በመያዝ” ትላቸዋለች) ለተከታታይ ሁለት አመታት #ትግራይ ላይ ያነጣጠረ የማያቋርጥ #ጥቃት እየፈፀመብኝ ነው የሚል ነው።አሁን ህወሃት ባለድል ለመሆን ግማሽ መንገድ ተጉዛለች።ህወሃት አሁን ሁለት ደረቅ ሀቆች ፍንትው ብለው እንዲወጡ በማደረግ ብአዴንን በስልት ሽባ ለማድግረ ጫፍ ደርሳለች።አሁንም ይህ ጉዳይ ገና አልተቋጨም።በመሰረቱ እነዚህ ሁለት ሀሳቦች አባይን ተሻግረው የሚሄዱት በሁለት ወይም ሶስት ግለሰቦች ካልሆነ በስተቀር አይሄዱም፤ አልያም አብረው ቢሄዱም ተፈፃሚ አይሆኑም።

ሌላኛው በሶስተኛነት የቀረበው ሀሳብ “ድርጅቱ ይጥራ ቀጥተኛ መስመሩን ይያዝ” ካልን በህዝቡ ዘንድ የሚታወቁ፣ እኛም እንዳላየን እያለፍናቸው ያሉ ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ አሁን አሁን በአመራሮች ሚስት እና ቤተሰብ ስም የሚንቀሳቀሱ #የገንዘብ ዝውውሮችና #ንብረቶች ላይ እርምጃ እንውሰድ የሚል ነው።ይህ ሀሳብ በአብዛኛው ብአዴንን ባይነካም ህወሃትና ኦህዴድን በሩን ማንኳኳቱ አይቀርም።ስርዓቱ ራሱ አመራሩን ለንግድ እና ዝርፊያ የሚያበረታታ በመሆኑ የሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት በኢፈርት እና በፖለቲካ አመራሮች ቤተሰቦች እጅ የተያዘ ነው። እናም ህወሃት ለጊዚያዊ ማምለጫነት ጥቂት ግለሰቦች የእነ ሳምሶን ወንድሙ እጣፈንታ ደርሷቸው ለሳምንት ማረሚያ ቤትን ተሳልመው ይመጡ ይሆናል፤ አልያም እንደ እነ ገብረዋህድ እና መላኩ ፈንታ እስር ቤትን መኖሪያቸው ሊያደርጉ ይችላሉ።በተለይ ኦህዴዶች በሁለተኛው ሊመደቡ ይችላሉ።

የኢህአዴግ ስብሰባ አሁንም ቀጥሏል።ምንም የተለየ ዘላቂ መፍትሄ ይዞ አይመጣም።ህወሃት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግር እኔ ነኝ ብሎ የሚያምንበትና ለመፍትሄ ሊዘጋጅ የሚችልበት ማዕቀፍ የለም።ስለዚህ አጣፋንታችን አሁንም እኛ እነርሱን አጮልቀን እያየን በሙሉ አይናችን ደግሞ ትግላችን እየቃኘን ወደፊት!!!!
ሁልጊዜም አንድ አቋም አለኝ።ይህ ስርዓት የሚፈርሰው ከውስጡ በሚፈነዳ መፈረካከስና በህዝባዊ አመፅ ነው የሚል።አሁን ውስጣቸው ያለው መፈረካከስ በጥገናዊ ለውጥ ሊመለስ ይችላል።ግን ዘላቂ አይሆንም።ይህንን ተከትሎ ደግሞ ሊያገረሽ የሚችለው ህዝባዊ ማዕበል ስርዓቱን ይበላዋል።እስከዚያው የሚደርሰንን መረጃ ማደረሳችን እንቀጥላለን።የሚጠቅመው ይጠቀምበታል፤ የማይጠቅመው አይቶ ይለፈው።
የሆነው ሁኖ ስርዓቱ ግን ብልጥ ነው።ሁለቱንም (በህዝባዊ ማእበል እና በራሱ መፈረካከስ እንደሚወድቅ ያውቃል።
ስለዚህ እድሜውን ከላይ በገለፅኩትና በሌሎች ስልቶች እያራዘመ የእቅዱን ዋና ክፍል ከመውደቁ በፊት እየፈፀመ ይጓዛል።ትግራይን ያወፍራል፤ ቀሪ ገንዘንlብን ያሸሻል፤ አማራን ይበዘብዛል።ጥያቄው ግን መቸ ይበላዋል? ነው።

Related posts

Lone opposition voice in Parliament says economic goals trigger clampdown on criticism

admin

Ethiopia’s Model of Ethnic Federalism Buckles Under Internal Tensions

admin

Ethiopia: More soldiers desert the army, join opposition groups

admin