45.01 F
Washington DC
February 28, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በአማራ ክልል ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ለመምራት፣ ሕገወጥነትን ለመከላከልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ኤጄንሲው አስታወቀ፡፡

በአማራ ክልል ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ለመምራት፣ ሕገወጥነትን ለመከላከልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራ መሆኑን ኤጄንሲው አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 19/2013 ዓ.ም (አብመድ) በመረጃ አያያዝ ችግር የሚፈጠሩ ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ማስቀረት የሚያስችል አዲስ አሠራር ወደ ተግባር እያስገባ መሆኑን የአማራ ክልል የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ አስታውቋል፡፡ አሰራሩ እያንዳንዱን የከተማ መሬት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመለካት ከወረቀት ሥራ ነጻ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ያስችላል፡፡

በመረጃ አያያዝ ችግር የሚፈጠሩ ውስብስብ መሬት ነክ ችግሮችን በቀላሉ ለመምራትና ለማስተዳደር፣ ሕገወጥነትን ለመከላከልና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችልም የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር ሽቤ ክንዴ ተናግረዋል፡፡ ከተሞች የመሬት ሀብታቸውን በአግባቡ ቆጥረው መረጃን ወደ ሥርዓቱ በማስገባት ለባለይዞታዎች የንብረት ዋስትናን እንዲያረጋግጡም ይረዳል፡፡

ዳይሬክተሩ በሰጡት ማብራሪያ መሠረት ዘመናዊ አሠራሩ በየከተሞች ያሉ ሁሉንም የመሠረተልማቶች ዝርጋታ ከማሳወቅ ጀምሮ መሬት በማን እጅ እንዳለ በቀላሉ ማወቅ የሚያስችል ነው፡፡ የክልሉ መንግሥትም አሠራሩን ለመተግበር የሚያስችል የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስልጠና ለመስጠት፣ ያልተሟሉ መረጃዎችን ለማጣራት፣ ሕገወጥ ግንባታዎችን ለመለየትና ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ ወደ 7 መቶ የሚጠጉ ከተሞች መኖራቸውን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ 14 ከተሞችን ወደ ሥርዓቱ ለማስገባት እየተሠራ ሲሆን ስምንቱ ሥራ ተጀምሮባቸዋል፡፡ ቀሪዎቹን ለማስጀመርም እየተሠራ መሆኑን አስታውቀዋል፤ በሂደት ሌሎች ከተሞች እንደሚካተቱም አመላክተዋል፡፡ ለአሠራሩ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በሥድስት ከተሞች የተሟላ መሬት ነክ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ባለ አራት ወለል ሕንጻዎች ተገብተዋል፡፡ በፌዴራል መንግሥት የለማ የመረጃ ስርዓት መኖሩን በመጥቀስም በተገነቡት ህንጻዎች ሥርዓቱ እንደሚዘረጋ አመላክተዋል፡፡

የክልሉን አቅም ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሌሎች ከተሞችም ቀጣይነት እንዲኖረው ይደረጋልም ብለዋል፡፡ ክልሉ ህንጻ ገንብቶ በመሬት ልማት ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ወደ አንድ በማጠቃለል የተሟላ አገልግሎት መስጠት ከጀመረባቸው ከተሞች መካከል ደብረ ብርሃን ከተማ አንዷ ናት፡፡ ቀድሞ የነበሩ ችሮችን በመፍታት ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠሩን የከተማ አስተዳደሩ ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የተገልጋዮች መረጃ በአስተማማኝ መልኩ እንዲደራጅ በማድረግና በቀላሉ እንዲስተናገዱ ጥሩ ዕድል መፍጠሩንም የጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ዘውዱ ታደሰ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ግንባታው የአካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑና ባለጉዳይ በሚበዛባቸው ጽሕፈት ቤቶች የሠራተኞች እጥረት መኖሩን አንስተዋል፡፡ በተለይ የሠራተኛ እጥረት ችግሩን ከክልሉ ጋር በመነጋገር ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

አቶ ሽቤ እንደተናገሩት ደግሞ ጅምር ሥራው ብዙ ችግሮች የታዩበት ነው፤ ችግሮቹ እንደሚስተካከሉና ለቀጣይ ሥራ ትምህርት እንደሚሆኑም ነው የተናገሩት፡፡ ለዘመናዊ አሠራሩ በ2006 ዓ.ም አዋጅ ተዘጋጅቷል፡፡ አዋጁን ተከትሎም ማስፈጸሚያ ደንቦችና መመሪያዎች መዘጋጀታቸውንም አቶ ሽቤ አስታውቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የኢትዮጵያ መንግስት ርሃብን እንደመሳሪያ ተጠቅሟል” በሚል ዘ ኢኮኖሚስት ያወጣውን ዘገባ መንግስት እንደሚያወግዝ አስታወቀ

admin

በአልጀሪያ  የኢትዮጵያ  ኤምባሲ በሁለት የንግድ ከተሞች  የኢንቨስትመንት፣ ንግድና ቱሪዝም ማስተዋወቂያ ሥራዎች አካሄደ

admin

በገቢዎች ሚኒስቴር የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሰጣቸው ስልጠና በታክስ አስተዳደሩ እየተፈጠሩ ያሉትን የወንጀል ድርጊቶች ለመከላከል እንደሚረዳቸው ሕግ አስከባሪዎች ተናገሩ።

admin