55.89 F
Washington DC
April 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በኖርዲክ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡

በኖርዲክ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኖርዲክ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር የበይነ መረብ መድረክ ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ይካሄዳል።

መድረኩ በኖርዌይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በኖርዲክ ሀገራት ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

የኢትዮጵያ ምሁራን በኖርዲክ ሀገራት ቡድን አስተባባሪ ዶክተር ተፈሪ ደጀኔ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብሩ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሚያደርጉትን ድጋፍ ማጠናከርን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በበይነ መረብ መድረኩ ከሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ ድጋፍ እንደሚሰባሰብና ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ ዜጎችም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ እንደሚቀርብ ጠቁመዋል።

በውይይቱ የሕዳሴ ግድቡ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃና የሦስትዮሽ ድርድሩን አስመልክቶ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እንደሚከናወንም ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በግድቡ ግንባታና ድርድር ዙሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል።

የበይነ መረብ ውይይቱ በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ዜጎች በተመሳሳይ ለሕዳሴ ግድቡ የሀብት ማሰባሰቢያ መርኃግብር እንዲያዘጋጁ መነቃቃት የመፍጠር ዓላማ እንዳለው ነው ዶክተር ተፈሪ ያስረዱት።

የኢትዮጵያ ምሁራን በኖርዲክ ሀገራት ቡድን በኖርዌይ የሚገኙ የኢትዮጵያ የሃይማኖት አባቶች፣ የማኅበረሰብ መሪዎችና በአጠቃላይ በኖርዌይ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላትን ያካተተ የሕዳሴ ግድብ የሀብት አሳባሳቢ ኮሚቴ በማቋቋም ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

Related posts

አንዳንድ የውጭ ሀገር ዜጎች “ኢንቨስተር ነን” በሚል ከፍተኛ የማጭበርበር ወንጀል እንደሚፈፅሙ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

admin

“ልዩ ኀይላችን በተግባር መስዋዕትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን ከመፍረስ እና ከመበታተን የታደገ ኃይል ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኀይለማርያም

admin

በሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የተከሰተው የጸጥታ ችግር አንጻራዊ ሰላም እያሳየ መሆኑን አስተዳደሮቹ ገለጹ፡፡

admin