56.68 F
Washington DC
April 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

‹‹በቤተ ጊዮርጊስ የሚሠራው መጠለያ ሲያስፈልግ እንደ ድንኳን ሆኖ የሚሸበለል ሲያስፈልግ ደግሞ የሚዘረጋ እንዲሆን እየተጠናበት ነው፡፡›› የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን

‹‹በቤተ ጊዮርጊስ የሚሠራው መጠለያ ሲያስፈልግ እንደ ድንኳን ሆኖ የሚሸበለል ሲያስፈልግ ደግሞ የሚዘረጋ እንዲሆን እየተጠናበት ነው፡፡›› የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን

ባሕር ዳር: የካቲት 26/2013 ዓ.ም (አብመድ) የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ለአብመድ እንደተናገሩት ላልይበላ በቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱ መንግሥትም በልዩ ትኩረት የሚያዬው ነው፡፡ ቅርሶቹን ለመንከባበከብ እየተሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በቅርሶቹ ላይ የተለያዩ አማራጮችን ለመተግባር ጥናት እየተደረገ መሆኑን የተናገሩት ምክትል ዳይሬክተሩ የመጀመሪያው መጠለያ መሥራት መሆኑን አመላክተዋል፡፡ መጠላያው አብያተክርስቲየናትን የሚታደግ ነውም ተብሏል፡፡

መጠለያው ምን አይነት ይሁን የሚለውን የፈረንሳይና የኢትዮጵያ የጥናት ቡድን ሲያጠናው መቆየቱንም አስታውቀዋል፡፡ የመጠለያው አይነት፣ሥፋቱና ችካልን በተመለከተ ጥናት ሲደረግ መቆየቱንም አስታውቀዋል፡፡ ከማኅበረሰቡ ጋር ውይይት መደረጉንም አስታውሰዋል፡፡

በአብያተ ክርስቲያናቱ ውስጥ ላይ ቋሚ ከመስራት ከቋጥኙ በውጭ በኩል መሥራት አስፈላጊ መሆኑንም መመላከቱን ነው የተናገሩት፡፡ አሁን ላይ ያለው መጠለያ ከቤተክርስቲያኑ በውጭ በኩል ቋሚ ሊሠራ የነበረው ተቀይሮ ከውስጥ በኩል ተሰርቶ መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡ ከቤተክርስቲያኑ በውጭ በኩል የሚኖረው መወጠሪያ ችካል የሚኖረውን ክብደት እንደሚቀንሰውም ታምኖበታል፡፡

በቤተ ጊዮርጊስ ላይ በድንኳን መልክ ለመሥራት መታሰቡንም ተናግረዋል፡፡ የቤተ ጊዮርጊስ እይታ ልዩ በመሆኑ ውበቱን በመጠለያ መሸፈን የለብንም በሚል ጥናት እየተጠና መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ በቤተ ጊዮርጊስ የሚሠራውን ሲያስፈልግ እንደ ድንኳን ሆኖ የሚሸበለል ሲያስፈልግ ደግሞ የሚዘረጋ እንዲሆን እየተጠናበት መሆኑን ነው ያስታወቁት፡፡

አምሳለ ምድራዊት ኢየሩሳሌምን በአንድ ላይ የሚያለብስ፣ አምሳለ ሰማያዊት ኢየሩሳሌምንም በአንድ ላይ የሚያለብስ መጠለያ መሥራት ሌላኛው የጥናት አማራጭ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ አማራጮቹ በሚያዚያ መጨረሻ ወይም ግንቦት መጀመሪያ የይሆናል አይሆንም፣ እያንዳንዱ አማራጭ ምን አይነት በጎና መጥፎ ጎን አለው የሚለው እንደሚታይም ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ውሳኔ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ በተመረጠው አማራጭ በመሄድ የዲዛይን ሥራ ይጀመራልም ነው ያሉት፡፡

በአብያተ ክርስቲያናቱ አስቸኳይ ጥገና የሚያስፈልጋቸው ሥራዎች በመጪው ዓመት መጀመሪያ የመጠገን ሥራ እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡ ላል ይበላን በመከታተል የመደገፍና የመጠገን ሥራዎች (ሰስተኔብል ላል ይበላ) የሚል ፕሮጄክት መኖሩንም ተናግረዋል፡፡

ሰው የማሰልጠን ሥራ ሌላኘው ሥራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ አብያተ ክርስቲያናቱን መጠለያ ማልበስ ላይ ጥቂት ቋሚዎች ኖረው ላዩ በቀርቀሃ እንዲሆን የማድረግ ጥናቶች እየተሰሩ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ሰውን በማሰልጠን ቀርቀሃውን በራሱ የሚቀይርበት እድል እንዲፈጠር ወደ ሚያስችል ሂደት እየሔዱ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡ ቀርቀሃው ከብደቱ ቀለል ያለ በመሆኑ ቅርሱን እንደማይጎዳውም ታምኖበታል፡፡

በላልይበላ የመረጃ ስርጭት ማዕከል (ዲጅታል ዳታ ሴንተር) መፍጠርና ከሚታዩት የላል ይበላ አብያተክርስቲያናት በተጨማሪ ለቱሪዝም መዳረሻ ሊሆኑ የሚችሉ የአርኪዮሎጂ ሥራዎች መጀመራቸውንም ተናግረዋል፡፡ በአርኪዮሎጂ ሥራዎቹ አዳዲስ ግኝቶች እየተገኙ መሆናቸውንም አመላክተዋል፡፡

ጣሪያ የማልበሱ ሥራ ሲሰራ የአብያተክርስቲያናቱን ውበት እንዳይቀንስና ሀይማኖታዊ ክዋኔዎችን በማያደብዝዝ መልኩ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

በላል ይበላ የሀይማታዊ ስርዓቱም ቅርስ ነው ያሉት ምክትል ዳይሬክተሩ መጠለያው ሲሰራ ምን ያክል ከፍ ብሎ አድማስ ማሳየት አለበት የሚለው ታሳቢ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡ በአብያተ ክርስያናቱ የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ስርዓቶቹን ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች እንደሚሰሩም አስታውቀዋል፡፡ በጥናት በሚደረሱ ውጤቶችና ሂደቶች ላይ ከሕዝቡ ጋር ውይይት እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡ የሕዝቡን አስተያዬት፣ የቅርሶቹ ጠባይና የሃይማኖታዊ ስርዓቱን ታሳቢ በማድረግ ውይይት ከተደረገ በኋላ በሚመረጠው የጥናት አማራጭ ውሳኔ ወደ ትግበራ ለመሄድ ሥራዎች ይሰራሉ፡፡

የፈረንሳይ መንግሥት በገባው ቃል መሠረት በቁርጠኝት እያገዘ መሆኑንም ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው አስታውቀዋል፡፡ በላልይበላ ትልቅ ሥራ እንደሚሰራና ሥራው በጥንቃቄ እንደሚከወንም አረጋግጠዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ታርቆ ክንዴ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት አለፈ

admin

ኢትዮጵያውያን በጋራ በመቆም ለሀገራቸው የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት እንዲወጡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢፌድሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡

admin

ብርቅዬ የዝሆን ዝርያዎችን ጠብቆ ለማቆየት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል – የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

admin