48.63 F
Washington DC
February 27, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በባሕር ዳር ከተማ በግማሽ ዓመቱ ከቱሪዝም ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።

በባሕር ዳር ከተማ በግማሽ ዓመቱ ከቱሪዝም ከ109 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኘ።

ባሕር ዳር ፡ የካቲት 11/2013 ዓ.ም (አብመድ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር ስምንተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 21ኛ መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ እያካሄደ ነው። የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳኅሉ በ2013 በጀት ዓመት ሁለተኛው ሩብ ዓመት የተከናወኑ የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ ሥራዎችን በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል።

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ ታስቦ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን አስመልክቶ ባቀረቡት ሪፖርትም ባሕር ዳር ካላት በርካታ ተፈጥሮዊ፣ ባህላዊ ፤ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ የመስህብ ሀብቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

ለዚህም ህብረተሰቡን ያሳተፈ የሎጅ ግንባታና መስተንግዶ፣ የስጦታ እቃዎች ምርትና ሽያጭ፣ የአካባቢ አስጎብኝነት፣ የጀልባ ትራንስፖርት፣ የኪነጥበብ ሥራዎች ተያያዥ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል። በዓመቱ ለ1 ሺህ 589 ሰዎች አዲስ የቱሪዝም የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ632 ዜጎች እንደተፈጠረ በሪፖርቱ ቀርቧል።

በከተማ አስተዳደሩ የቱሪዝም ገበያ ሥርዓትንና ሁለንተናዊ ፋይዳን በማሻሻል ለሃይማኖታዊ ክብረ በዓላት፣ ለኮንፈረንስ ቱሪዝም፣ ለቢዝነስ፣ ለጤና ቱሪዝም እና ለስፖርታዊ ውድድሮች ወደከተማዋ የሚገቡ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገራት ቱሪስቶችን ቁጥር ለማሳደግ መሠራቱንም ተናግረዋል።

ከሀገር ውስጥ ጎብኝዎች 306 ሚሊዮን 280 ሺህ 159 ብር ከዉጭ ሀገር ጎብኝዎች ደግሞ 217 ሚሊዮን 623 ሺህ 900 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ እንደነበርም ተመላክቷል።

በሪፖርቱ እንደተመላከተው 176 ሺህ 943 የሀገር ዉስጥና 335 የዉጭ ሀገር ቱሪስቶች ባሕርዳርና አካባቢዋን ጎብኝተዋል። በዚህም ከሀገር ዉስጥ ጎብኝዎች 107 ሚሊዮን 324 ሺህ 519፣ ከዉጭ ሀገር ጎብኝዎች ደግሞ 1 ሚሊዮን 823 ሺህ 740 በድምሩ 109 ሚሊዮን 158 ሺህ 259 ብር ገቢ ተገኝቷል፡፡

የቅርስ ጥገና በማድረግና የመስህብ ሀብቶችን በማልማትና በማስፋፋት የቱሪስቱን ፍሰት ከመጨመር ባለፈ የባህል እሴቶችን ለትዉልድ ለማስተላለፍ የተከናወኑ ተግባራትም ቀርበዋል።

በበጀት ዓመቱ ለቋሚ ቅርሶች ጥገና ለማካሄድና ቅርሶች ጉዳትና ስርቆት እንዳይደርስባቸው የተከናወኑ ተግባራት በሪፖርቱ ተጠቅሷል። ወደ 581 ተንቀሳቃሽ ቅርሶች ለስርቆት እና ለዘረፋ እንዳይጋለጡ የቁጥጥርና የክትትል ሥራ መሠራቱን ዶክተር ድረስ ተናግረዋል።

ጎብኝዎች ያለምንም ወከባ የቱሪዝምአገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፈጠር እየተሠራ ነው፡፡

አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ የብቃት ማረጋገጫ የመስጠት እንዲሁም የድጋፍና ክትትል ሥራ መከናወናቸውንም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አንስተዋል።

በሀገሪቱ በተፈጠረው የሕግ ማስከበርና በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተለይ የውጪ ሀገራት ጎብኝዎች ቁጥር ቅናሽ ማሳየቱን ተቀዳሚ ምክት ከንቲባው ተናግረዋል። በቅርቡ ግን የሀገር ውስጥ ጎብኝዎችን ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች መኖራቸውን አመላክተዋል። ጅምር ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት።

ከክልሉ መንግሥት ጋር የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማልማትና ቅርሶችን በመጠገን ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ማሳደግ ትኩረት ይሰጠዋል ብለዋል ዶክተር ድረስ ለምክር ቤት አባላት ባቀረቡት ሪፖርት።

ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የአገሪቷን ኪነ-ሕንፃ ታሪክና አካባቢን ያገናዘበ ለማድረግ የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ

admin

“ለጎርጎራ ፕሮጀክት አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረሥላሴ የሚያስገነባውን ግዙፍ ሪዞርት ጨምሮ ከ120 በላይ ፕሮጀክቶች በእጃችን ይገኛሉ” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

admin

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ እና የፌደራል መሬት ባንክ ልማት ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

admin