51.91 F
Washington DC
May 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት ለመወጣት እየሠሩ መሆናቸውን አሚኮ ያነጋገራቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅትች አስታወቁ፡፡

በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የሚጠበቅባቸውን ኀላፊነት ለመወጣት እየሠሩ መሆናቸውን አሚኮ ያነጋገራቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅትች አስታወቁ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መረጃ እንደሚያሳየው በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ትምሕርት ለመስጠት 155 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እንዲሁም በአንደኛ ዙር ምርጫን ለመታዘብ 36 ድርጅቶች ፍቃድ አግኝተዋል፡፡

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በምርጫው የፖለቲካ ፓርቲዎችን ማግባባት፣ የመራጮች ትምሕርት መስጠት እና ምርጫን ለመታዘብ ይሳተፋሉ፡፡ እናም ድርጅቶቹ ከምርጫ በፊት የመራጮች ትምሕርት ይሰጣሉ፤ በምርጫ ጊዜ ምርጫን ይታዘባሉ፤ ከምርጫ በኋላ ግጭት እንዳይከሰት ሕዝብን የማረጋጋት እና አለመግባባቶች ቢኖሩ እንኳን በሠላማዊና ሕጋዊ መንገድ ብቻ እንዲፈቱ ጥረት ያደርጋሉ፡፡

ምርጫን ለመታዘብ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመዘገባቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በዘርፉ በሚሰማሩበት ወቅት በዓላማቸው መሰረት መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውም ተጠቅሷል፡፡

በዚህ ረገድ ዝግጅታቸው ምን እንደሚመሰል አሚኮ የአማራ ክልል ወጣቶች ማኀበርን እና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የሴቶች ማኅበርን አነጋግሯል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሴቶች ማኅበር ሰብሳቢ ወይዘሮ ሐና ጆርጅ ግንቦት 28/2013 ዓ.ም በሚካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሴቶች በቂ ግንዛቤ ኖሮአቸው የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየሠሩ መሆኑን ነግረውናል፡፡ ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ሴቶች በሀገሪቱ ልማትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ያላቸው ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢዋ እንዳብራሩት በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ሥር በሚገኙ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የማኅበሩ የሥራ ኃላፊዎች ምርጫን በተመለከተ ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ ተሠርቷል፤ በቀጣይ በየክፍለ ከተማው ለሚገኙ አባላቱ ሥልጠና ይሰጣል፤ የማኅበሩ ሰባተኛ መደበኛ ጉባኤ የምርጫ ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

ወይዘሮ ሐና የማኅበሩ አባላት ከአማራ ሴቶች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 61 የምርጫ ጣቢያዎች ሁለት ሁለት አባላት እንዲመደቡና ምርጫውን እንዲታዘቡ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑንም ነግረውናል፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የአማራ ሴቶች ማኅበር ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ እንደሚሠራም ገልጸዋል፡፡

ምርጫው ሠላማዊ እንዲሆን ከመሥራት ባሻገር የማኅበሩ አባላት የምርጫ ካርድ በማውጣት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከ11 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ማኀበሩ ነጻና ፍትሐዊ ምርጫ እንዲካሄድ ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ ሰብሳቢዋ አስታውቀዋል፡፡

የአማራ ክልል ወጣቶች ማኀበር ሰብሳቢ ዓባይነህ ጌጡ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሐዊና ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማኀበሩ እየሠራ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ማኅበሩ የመራጮች ትምሕርት በመስጠት እና ምርጫን በመታዘብ እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡

ወጣት ዓባይነህ እንዳለው ስለ ምርጫ ወጣቶች በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ሚናቸውን አውቀው ለስኬታማነቱ ጥረት እንዲያደርጉ ውይይቶች እያካሄዱ ነው፡፡ እስካሁንም በደቡብ ጎንደር እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች አካሂደዋል፡፡ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በቀሪዎቹ ዞኖች ከትናንት መጋቢት 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይካሄዳል ብሏል።

የማኅበሩ አባላት በተሳሳተ መረጃ አለመደናገር እና ከምርጫ በኋላ ውጤቱን ሕጋዊ የሆነው ምርጫ ቦርድ ብቻ ይፋ እንደሚያደርግ በማወቅ ምክንያታዊ ሊሆኑ እንደሚገባ ገልጿል።

“ሀገራችን በተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ ሆና የሚደረግ ምርጫ በመሆኑ የማኅበሩ አባላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል” ብሏል የማኅበሩ ሰብሳቢ።

ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ሁከትና ብጥብጥ ሀገርን ለመበተን ከሚሠሩ ኀይሎች የሚሰነዘር በመሆኑ ወጣቶች በጥበብ ሊያልፉት እንደሚገባም ሰብሳቢው ጠቁሟል። ምርጫው ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ሠላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ የወጣቶች ሚና የጎላ መሆኑን በመረዳት መንቀሳቀስ እንደሚገባ ዓባይነህ ጌጡ መልእክት አስተላልፏል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋው ይቁም፣ጨፍጫፊዎቹም ለፍርድ ይቅረቡ! | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

አምባሳደር ዮናስ ዮሴፍ በታንዛኒያ ከሱዳን ኤምባሲ ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ጋር ተወያዩ

admin

ʺሕይወቱን የሰጠላት ሀገር ለሐውልቱ መቆሚያ ስፍራ ነፈገችው”

admin