51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች በዕውቀት ላይ ተመስርተው እንዲመርጡ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ተገለጸ።በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች በዕውቀት ላይ ተመስርተው እንዲመርጡ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኃላፊነታቸውን
እንደሚወጡ ተገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 03/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች በዕውቀት ላይ ተመስርተው ወካያቸውን
እንዲመርጡ ለማስቻል በባሕር ዳር ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባጸደቀው አዋጅ
ቁጥር 1162/2011 መሠረት መራጮች ግንዛቤ ኖሯቸው በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ
ምርጫ ቦርድ አሠራሮችን ዘርግቷል።
የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምሕርት መስጠት ለሚችሉ ሀገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና የትምሕርት ተቋማት ፈቃድ
መስጠትም አንዱ ነው። በቦርዱ የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው ፈቃድ የተሰጣቸው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ቦርዱ
ባዘጋጃቸው የማስተማሪያ ሰነዶች ላይ ተመስርተው የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት በመስጠት ሀገራዊ ምርጫው ሠላማዊ
እና በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን የማድረግ ሚናቸውን ይወጣሉ።
በምርጫ ቦርዱ ፈቃድ ከተሰጣቸው መካከል ‘ሄልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ’ የተሰኘ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት የመራጮች
ትምሕርት ለሚሰጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው የተሰጠው ከባሕር ዳር ከተማና ከባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ
ለተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሆኑን የሄልዝ ኤንድ ሆልነስ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት መሥራችና ዳይሬክተር
አለሁበል አልማው ገልጸዋል፡፡
ሰልጣኞቹ ከስልጠናው በኋላ በ10 ቀበሌዎች ከ125 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ያስተምራሉ ብለዋል። ስልጠናው ዜጎች
‘ይወክለኛል’ ያሉትን ተወካይ በሚገባ ተገንዝበው በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ምርጫ እንዲያደርጉ ማስቻልን ታሳቢ ያደረገ ነው።
ሰልጣኞች አጠቃላይ በምርጫ ዑደት ያሉ ሂደቶችን አውቀው ለኅብረተሰቡ እንዲያስገነዝቡ ማድረግ ደግሞ የስልጠናው ዓላማ
ነው።
ሰልጣኞች ምርጫና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያላቸውን ዝምድና በሚገባ በመረዳት ለሀገራዊ ምርጫው የሚጠበቅባቸውን
አስተዋዕጾ እንደሚያበረክቱ ይጠበቃል። ስለ መራጮች መብትና ግዴታ ሰፋ ያለ ግንዛቤ ወስደው ለማኅብሰቡ በቂ ዕውቀት
ያስጨብጣሉ ተብሎም ይጠበቃል። የስልጠናው ይዘትም በምርጫ አጠቃላይ ምንነት፣ ዜጎች በምርጫ ሂደቱ ሊኖራቸው በሚገባ
ተሳትፎ እና በምርጫ ጊዜ ቅድሚያ ለሠላም መስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በምርጫ ሂደቱ የኮሮናቫይረስ
መከላከያ ፕሮቶኮልን ተግባራዊ ማድረግም የስልጠናው አካል ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ።
አቶ አለሁበል እንዳሉት ሰልጣኞች ማኅበረሰቡን የሚያስተምሩበት ሰነድ እና የመረጃ መያዣ ቅፅ ተዘጋጅቷል። በዚያ መሰረት
በየቀበሌው ከሚገኙ አስተባባሪዎች፣ ሥራ አስኪያጆች፣ የጸጥታ አካላት እና ሊቀመናብርት ጋር እንዲሠሩ ይደረጋልም ብለዋል።
ለስልጠናው አስፈላጊ ወጪ መሸፈንን ጨምሮ በጎ አድራጎት ድርጅቱ በምርጫ ጉዳዮች ላይ ተከታታይነት ያላቸው ሥራዎችን
እንደሚያከናውን አቶ አለሁበል አስታውቀዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም ያገኙትን ዕውቀት ለኅብረተሰቡ በማካፈል ዜጎች በኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ ላይ የሚወስን ተወካይ
እንደሚመርጡ ለማስገንዘብ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“እውነትን የመካድ ዘመቻ”

Source link

Related posts

የአድዋ ድል አባቶቻችን እና አያቶቻችን በመደማመጥ፣ በመከባበር፣ በአንድነት እና በመዋደድ ያስመዘገቡት የድል ክብረ ወሰን ነው -ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

admin

ትግራይ እንዴት ሰነበተች? – (ክፍል 1)

admin

መንግሥት በዜጎች ላይ የሚፈጸም ሽብርተኝነትን ለመከላከል ቁርጠኛ ከሆነ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ መብት በተግባር ሊተረጉመው ይገባል” ደራሲ፣ ጠበቃና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አለልኝ ምህረቱ

admin