51.91 F
Washington DC
May 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ሴቶች፣ ሕጻናትና
ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ሴቶች፣ ሕጻናትና
ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም (አብመድ) የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከኢፌዴሪ ሴቶች፣
ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በፍትሕ ስርዓቱ ውስጥ በሚያልፉ ሕጻናትና ሴቶች አያያዝ ዙሪያ ከባለ ድርሻ
አካላት ጋር በባሕር ዳር ውይይት እያካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል የሴቶችና ሕጻናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ወይዘሮ ሠላማዊት ዓለማየሁ በፍትሕ
ስርዓቱ ውስጥ በሚያልፉ ሕጻናትና ሴቶች አያያዝ ዙሪያ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ጠቅሰዋል፡፡ ምንም እንኳን ቁራቸው
አነስተኛ ቢሆንም በአማራ ክልል ሁለት ማቆያ ማዕከላት ተቋቁመው አገልግሎት እየሠጡ ነው ብለዋል፡፡ ማዕከላቱ ጥቃት
የደረሰባቸው ሴቶች እና ሕጻናት ፍትሕ እንዲያገኙ የጎላ አስተዋጽኦ አያበረከቱ ነው ብለዋል፡፡ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ
የሚደርሰውን ጥቃት ለመከላከል ከባለ ድርሻ አካላት ጋር እየሠሩ መሆናቸውንም ወይዘሮ ሠላማዊት ተናግረዋል፡፡
የኢፌዴሪ የሴቶችና ሕጻናት ወጣቶች ጉዳይ ሚንስቴር የሕጻናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ወይዘሮ ዘቢደር ቦጋለ
እንደጠቀሱት በሀገራችን ከተከሰቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ ሴቶችና ሕጻናት በሰፊው የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ነው፤ ይሄን ችግር
ለማስቆም በርካታ ሥራዎች ቢሠሩም ችግሩን ከምንጩ ማድረቅ አልተቻለም፡፡
ወይዘሮ ዘቢደር እንዳሉት ወቅታዊ ችግሮች ባሉባቸው አካባቢዎች ችግር የደረሰባቸውን ሴቶች እና ሕጻናትን ለማገዝ ከአጋር
አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው፡፡ ሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ሲከሰቱ ቅድሚያ የችግሩ ተጠቂዎች ሴቶች መሆናቸውን
አማካሪዋ ገልጸዋል፡፡ አማካሪዋ ችግር በደረሰባቸው አካባቢዎች ለአደጋ የተጋለጡ ሴቶች ተገቢውን የህክምናና የንጽህና
መጠበቂያ ቁሳቁስ የሚያገኙበት ሁኔታ መመቻቸቱንም ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ዘቢደር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወደ ሀገሪቱ መግባቱን ተከትሎ ሴቶችና ሕጻናት በቤት ውስጥ እንዲውሉ መደረጉ
በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት ቁጥሩ እንዲያሻቅብ ምክንያት መሆኑንም አንስተዋል፡፡ ሴቶችና ሕጻናት ችግሮች ሲያጋጥማቸው
የፍትሕ አካላት እየወሰዷቸው ያሉ እርምጃዎች ውጤት ሲያመጡ አይታዩም ብለዋል፡፡ በዚህ ዙሪያ የሚከሰቱ ችግሮችን
ለመፍታት በርካታ ደንቦችና መመሪያዎች ቢወጡም የአፈጻጸም ችግሮች በመኖራቸው ጥፋተኞች ከጥፋታቸው ከመቆጠብ ይልቅ
ደግመው ደጋግመው ሲፈጽሙት እንደሚስተዋልም አንስተዋል፡፡
የፍትሕ አካላት ለእነዚህና ለሌሎች ችግሮች መፍትሔ በመስጠት በኩል ምን እየሠሩ እንደሆነ እና ወደፊትስ ምን መሥራት
እንዳለባቸው ለማመላከት ውይይቱ አስተዋጽኦው ከፍ ያለ ነው ተብሏል፡፡ ወይዘሮ ዘቢደር እንዳሉት የፍትሕ ስርዓትን ከማስተካከል
ጎን ለጎን ማኅበረሰቡ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ አለበት፡፡ ማኅበረሰቡ ችግሮች ሲያጋጥሙ ከመጠቆም ጀምሮ ማስረጃ ሆኖ
እስከመቅረብ ድረስ ድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በ2017 ዓ.ም ያለእድሜ ጋብቻን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም እና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን
መፈረሟን ወይዘሮ ዘቢደር አንስተዋል፡፡ እነዚህን ስምምነቶች ከሀገሪቱ ሕጎች ጋር አስተሳስሮ ተግባራዊ ለማድረግም እየሠራን
ነው ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleበአማራ ክልል የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 8 ሺህ ሲጠጋ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ200 ሺህ አልፏል፡፡
Next articleየነዳጅ እጥረትን ለመፍታት የነዳጅ አቅርቦትን መጨመርና ሕገ ወጥነትን መቆጣጠር እንደሚገባ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ገለጹ፡፡

Source link

Related posts

“ሱዳን በሶስተኛ ወገን የተደገሰላትን የጦርነት ወጥመድ በመተው ችግሩን በድርድር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆን አለባት” ጀነራል ብርሃኑ ጁላ

admin

በአጣዬና ዙሪያዋ የሆነው ይህ ነው | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት አምባሳደሮችና ከሀገራቱ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

admin