55.89 F
Washington DC
April 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ760 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት በመስኖ ለምቶ ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ከ760 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት በመስኖ ለምቶ ለገበያ መቅረቡን የዞኑ ግብርና መምሪያ ገለጸ፡፡

ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2013 ዓ.ም (አብመድ) በሰሜን ሸዋ ዞን በመጀመሪያው ዙር በለማው የመስኖ እርሻ ከ91 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። በመኸር እርሻ ልማቱ የጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተት፣ ከፍተኛ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ፣ በረዶ እና የበርሃ አንበጣ የምርት መቀነስ እዲፈጠር አድርገው ነበር፡፡

በዞኑ ግብርና መምሪያ የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም የሥራ ሂደት ተወካይ ድፌ ወንድማገኝ እንደተናገሩት በተፈጥሮ አደጋዎቹ የተፈጠረውን የምርት ቅናሽ ለማካካስ የተጠናከረ የመስኖ እርሻ ልማት እየተከናወነ ነው።

በመስኖ ወደ 28 ሺህ 250 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል። ለዚህም ወደ 36 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ እና 5 ሺህ 718 ኩንታል የምርጥ ዘር ግብዓት እየቀረበ መሆኑን አመላክተዋል። በመጀመሪያው ዙር የመስኖ ልማትም 23 ሺህ 187 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን የአትክልትና ፍራፍሬ መስኖ አጠቃቀም የሥራ ሂደት ተወካዩ ተናግረዋል። ይህም ወደ 82 በመቶ አፈጻጸም እንዳለው ታውቋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 760 ሺህ 508 ኩንታል ምርት ከለማው መስኖ ለገበያ ቀርቧል። አቶ ድፌ እንዳሉት በዞኑ በመስኖ በስፋት የሚለማው የአትክልትና ፍራፍሬ አይነቶች ናቸው። እንደ ሽንኩርት፣ጥቅል ጎመን፣ ካሮት፣ ቀይሥር፣ ነጭ ሽንኩርት፣ ቡና፣ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ ብርቱካን፣ ፓፓያ፣ ሙዝ እና የመሳሰሉት የግብርና ምርቶች በስፋት ይመረታሉ። ገብስና ሥንዴ በመስኖ ከሚለሙት አዝዕርት መካከል ሲሆኑ ኢትዮጵያ ከውጪ ሀገራት የምታስገባውን የስንዴ ምርት ለመተካት ተስፋ የተጣለበት የቆላ ስንዴ የመስኖ ልማትም በዞኑ ተጀምሯል።

በሁለተኛው ዙር የመስኖ ልማት ወደ 13 ሺህ ሄክታር ለማልማት ታቅዷል። እስካሁንም 2 ሺህ 200 ሄክታር ለምቷል ብለዋል አቶ ድፌ። በመስኖ ልማቱ 3 ሚሊዮን 396 ሺህ 512 ኩንታል ምርት ነው ለማግኘት የታቀደው። በዚህም 111 ሺህ 382 አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

ቀደም ብሎ በአርሶ አደሮች ዘንድ የመስኖ አጠቃቀም እንዲሁም የግብርና ግብዓት የመጠቀም ልምድ አናሳ እንደነበር አስታውቀዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ በመሠራቱና የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እየጨመረ በመምጣቱ የመስኖ ልማቱም ሆነ የግብዓት አጠቃቀሙ እያደገ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ውኃ መገኛ ነው። ከዚህ በፊት በተሠራ የዳሰሳ ጥናት ወደ 90 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ እንደሚለማ ተገልጿል።

የመስኖ ልማቱን ለማሳደግ ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመነጋገር ጥናት ለመሥራት እንቅስቃሴ ተጀምሯል ብለዋል። በጥናቱ ውጤት ላይ በመመስረትም በዞኑ የተሻለ የመስኖ እርሻ ለደማት እንዲኖር በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ- ከደብረብርሃን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በወጣቱ ላይ የተሰራውን የጥላቻ ትርክት በትምህርት ስርዓት ማስተካከል ይገባል – ብሔራዊ የወጣቶች ምክክር

admin

“አንድነት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በዋሽንግተን ዲሲና በኒውዮርክ ግዛቶች ሰላማዊ ሰልፍ ሊካሄድ ነው፡፡

admin

በድባጤ ወረዳ ሳስ ማንደን ቀበሌ የእርቅ ስነ-ስርዓት ተፈፀመ

admin