70.74 F
Washington DC
May 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“በርብ ግድብ የአሳ ምርት ላይ ያለውን ህገወጥ ሥራ በማስቆም የአሳ ምርቱን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራሁ ነው፡፡” የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት“በርብ ግድብ የአሳ ምርት ላይ ያለውን ህገወጥ ሥራ በማስቆም የአሳ ምርቱን ውጤታማ ለማድረግ እየሠራሁ ነው፡፡” የደቡብ
ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 16/2013 ዓ.ም (አብመድ) ህገወጥ አሳ አስጋሪዎችን መከላከል ባለመቻሉ በአሳ ምርት ላያ ውጤታማ
መሆን አለመቻላቸውን በርብ ግድብ በአሳ ማስገር የተደራጁ ወጣቶች ገልጸዋል። የአሳ ማሥገሪያ ግብዓት አቅርቦት እና
የሥልጠና ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ወጣቶቹ ጠይቀዋል።
ወጣት ባቡ አመሼ እና ምናለ አዳነ እንደነገሩን የግድቡ ውኃ መለቀቅን ተከትሎ የአሳ ሃብቱ ከውኃው ጋር ወደ ውጭ በመውጣቱ
ዝርያው ተመናምኗል። ይህንን ተከትሎ የማስገር ሥራ እንዳይከናወን ቢከለከልም በህገወጥ መንገድ ሥራው መቀጠሉን
ገልጸዋል።
በተደራጀ መንገድ ሙያዊ ስልጠና እና የብድር አገልግሎት አለማግኘት እንዲሁም ህገወጥ መረብ መከላከል ላይ የተሰጠው
ትኩረት ዝቅተኛ መሆኑን በሥራቸው ላይ ፈተና እንደሆነባቸው ነው ወጣቶቹ የተናገሩት።
የፋርጣ ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት የአሳ ሀብት ልማት ባለሙያ ክንዴ በላይ ወጣቶች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ
ተደራጅተው በአሳ ማስገር ሥራ ቢሰማሩም በበጀት ችግር የተደራጀ ስልጠና እና የብድር አገልግሎት አለማግኘታቸውን
ገልጸዋል። የወረዳው አሳ ሀብት ልማት ባደረገው ክትትልም ከ300 በላይ በሱዳን የገባ ህገወጥ መረብ መያዙን አንስተዋል።
በግድቡ የህገ ወጥ አሳ አስጋሪዎች መበራከት በአሳ ምርቱ እና በህጋዊ አስጋሪዎች ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል። የፋርጣ እና እብናት
ወረዳዎች በትኩረት ህገወጥነትን መከላከል ካልቻሉ የአሳ ዝርያው የመጥፋት ዕድሉ ከፍተኛ እንደሆነም አንስተዋል።
የክልሉ መንግሥት ጥናት አድርጎ በሚቀጥለው ዓመት ተጨማሪ የአሳ ጫጩት በመጨመር በሥራው ላይ ተጫማሪ ወጣቶች
እንዲሳተፉ ማድረግ እንደሚገባም ነው ባለሙያው የጠቆሙት።
የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ እና የእንስሳት እርባታ ቡድን መሪ አሰፋ ጌቴ ግድቡ
ከሁለት ዓመት በፊት ሥራ ሲጀምር 10 ሺህ የሚጠጋ የአሳ ጫጩት ወደ ግድቡ ተጨምሮ እንደነበር ገልጸውልናል።
በ10 ኢንተርፕራይዞች የተደራጁ 103 ወጣቶችም ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል። ቡድን መሪው እንዳሉት በተለያዩ ምክንያቶች
የግድቡ ውኃ መለቀቅን ተከትሎ የአሳ ዝርያው በመመናመኑ ውኃው መልሶ እስኪሞላ እና አሳ ጫጩት ተጨምሮ ወደ ምርት
እስኪገባ የማስገር ሥራ እንዳይከናውን ታግዷል።
ይሁን እንጅ በእብናት እና ፋርጣ ወረዳዎች የቅንጅት ችግር ምክንያት በህገውጥ መንገድ የማስገር ሥራው አልቆመም፤ ይህም
በተደራጁ ወጣቶች የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ችግር መፍጠሩን ተናግረዋል።
ወጣቶቹ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ከሁለቱ ወረዳዎች እና ከአጋር አካላት ጋር ሥራ እንደሚጀምሩ አቶ አሰፋ ነግረውናል።
በቀጣይ ግድቡ በዘላቂነት ውኃ የመያዝ ሁኔታውን በማረጋገጥ እስከ 25 ሺህ የአሳ ጫጩት በግድቡ ብቻ እንደሚጨመርም
ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሰራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“የአማራ ልዩ ኃይል ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ደጀን መሆኑን በተግባር ያረጋገጠ ኃይል ነው” የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ

Source link

Related posts

በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተገልጋዮች ጠየቁ፡፡

admin

ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የአማራ ፖሊስ ዘመናዊ አሠራር እንዲከተልና ብቁ ተቋም እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ያደረጉ እንደነበሩ የሥራ ባልደረቦቻቸው ተናገሩ፡፡

admin

ከሞት የበለጠ አስፈሪ ነገር ምን አለ?

admin