69.82 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“በሞታችን የሚያተርፉ እና በቁስላችን የሚነግዱ ሕሊና ቢሶች በዝተዋል፤ ሕዝቡ ነቅቶ ኢትዮጵያን ሊያድንና ወደ ቀደመዉ ክብሯ ሊመልስ ይገባል” የባሕር ዳር የሰላም ልዑክ

“በሞታችን የሚያተርፉ እና በቁስላችን የሚነግዱ ሕሊና ቢሶች በዝተዋል፤ ሕዝቡ ነቅቶ ኢትዮጵያን ሊያድንና ወደ ቀደመዉ ክብሯ ሊመልስ ይገባል” የባሕር ዳር የሰላም ልዑክ

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 19/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም አምባሳደር ቤንጃሚን ወንዴ የሞጣ ከተማ ክርስትና እና እስልምና ሃይማኖት ተከታይ ሕዝብ ለተንኮለኛ እጅ አንሰጥም፤ ለሴረኛ አንበረከክም ማለታችሁን ስንሰማ እና እንዲህ በአካል ተገኝተን ሕብር የሆነውን ፍቅራችሁን እና አንድነታችሁን ስናይ በእጥፍ ተደስተናል ነው ያሉት በሰላም አምባሳደር ቤንጃሚን ወንዴ የተመራው የባሕር ዳር የሰላም ልዑክ በሞጣ።

በሞጣ ከተማ አስተዳደር ታሕሣሥ 10/2012 ዓ.ም ተፈጥሮ የነበረውን የቤተ እምነቶች እና የንግድ ድርጅቶች ቃጠሎ ስንሰማ ከልብ አዝነን ነበር ያሉት የሰላም መልክተኞቹ ዛሬ ያንን የችግር ጊዜ በትዕግስት አሳልፈችሁ “ሕብር እና ፍቅር በሰባቱ ዋርካ” በሚል መሪ ሃሳብ የፍቅር፣ የአንድነት እና የሰላም መሠረት የሆነውን ሕዝባዊ ውይይት ስታካሂዱ በመታደማችን ደስታችን ወደር የለውም ብለዋል።

ለሞጣ ከተማ ሕዝብ ሰላም እና ፍቅር ባህላችሁ፤ መተባበር እና መከባበር የኖረ እሴታችሁ መገለጫችን ነው ብለዋል የወጣቶች የሰላም ልዑክ፡፡

በዚህ ዘመን የሚያሳዝነው በሞታችን የሚያተርፉ እና በቁስላችን የሚነግዱ ሕሊና ቢሶች በዝተዋል ያሉት ወጣቶቹ ሕዝቡ ነቅቶ ኢትዮጵያን ሊያድንና ወደ ቀደመዉ እሴቷና ክብሯ ሊመልስ ይገባል ነው ያሉት።

የውጭ ኃይሎች እና የውስጥ ባንዳዎች ኢትዮጵያን ለመበተን አሰፍስፈው በየቀኑ አዳዲስ ሴራ እየፈበረኩ በሚገኝበት ጊዜ በሞጣ ከተማ የሰላም፣ የእርቅ፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት ውይይት መካሄዱ በጎ አርዓያ ነው ብለዋል።

አሁን ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የሚያስፈልገን አንድነት፣ ፍቅር እና ወንድማማችነት ነው ያሉት ወጣቶቹ “በአንድነት ዓለም የግል ክብር እና የግል ሀዘን የለም” ነው ያሉት። ክብሩም ሆነ ሀዘኑ የጋራ ነው፤ በአንድነት ዓለም ግለኝነት የለምና ይህች ዓለም የሕብረት ዓለም ናት ብለዋል።

ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው -ከሞጣ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

Source link

Related posts

የኦሮሚያ ክልል በማንነት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በማስቆም በክልሉ ለሚኖረው ሕዝብ ደኅንነት በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ

admin

ብሔራዊ የአየር ጠባይ አገልግሎት ማዕቀፍ ስምምነት ተፈረመ

admin

“የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የቱንም ያህል ቢበረቱ አሸናፊ መሆን ግን አይችሉም።” አቶ አብርሃም አለኸኝ

admin