63.7 F
Washington DC
June 17, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በምርጫ ወቅት ብዙኃን መገናኛ ተቋማት በኀላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ምሁራን ገለፁ፡፡በምርጫ ወቅት ብዙኃን መገናኛ ተቋማት በኀላፊነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ምሁራን ገለፁ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 08/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረውን ስድስተኛውን ሀገራዊ
ምርጫ በመጪው ግንቦት 28 ለማካሄድ ታስቦ እየተሠራ ነው፡፡ የሀገሪቱ ምርጫ ቦርድ እንደ አዲስ ከተደራጀበት ጊዜ አንስቶም
የምርጫ አዋጅ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡ ከዚህ ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን እና የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ የሥነ ምግባር እና
አሠራርን መመሪያን መጥቀስ ይቻላል፡፡
ማሻሻያው መገናኛ ብዙኃን በተለይ በምርጫ ወቅት በኀላፊነት ሚናቸውን መወጣት ባለባቸው ላይ ያተኩራል፡፡ በጉዳዩ ላይ
ያነጋገርናቸው የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት ምሁራን በምርጫ ወቅት ብዙኃን መገናኛ ተቋማት በኀላፊነት መንቀሳቀስ
እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ኅብረተሰቡም የመምረጥም ሆነ የመመረጥ መብቱን ተግባራዊ እንዲያደርግ መረጃ በመሥጠት
ሊያግዙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት ትምህርት ክፍል መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አስማማው አዲስ ምርጫ ዜጎች
ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚተገብሩበት አንዱ እድል በመሆኑ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛ፣ ወቅታዊ እና በቂ መረጃ በማቅረብ
ውሳኔያቸውን ሊያግዙ ይገባል ብለዋል፡፡ እንደ ምሁሩ ማብራሪያ መገናኛ ብዙኃን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ እንደመሆናቸው መጠን
መረጃ ማቀበል እና ስለምርጫ ሂደቱ በቂ ግንዛቤ መፍጠር አለባቸው፡፡
ተደራሽነታቸው ሰፊ መሆኑን በመጥቀስ በምርጫ ወቅት ስለ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦች መራጩ ኅብረተሰብ እና
ተመራጩን በማገናኘት አንዱ ከአንዱ ምን እንደሚፈለግ እና እንደሚጠበቅበት ለማሳወቅ የውይይት መድረክ ያመቻቻሉ፡፡ የሀገሪቱ
የምርጫ ቦርድ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ እና በድህረ ምርጫ ሂደቶች የሚያወጣቸው መመሪዎች፣ ደንቦች እና መረጃዎች
ማስተዋወቅ እና ተግባራዊነታቸውን መከታተል የብዙኃን መገናኛ ተቋማት አይተኬ ሚና ነው፡፡
መገናኛ ብዙኃን ከምርጫ ቦርድ ብቻ ይፋ የሚደረገውን ውጤት ለኅብረተሰቡ ይፋ የማድረግ ኀላፊነታቸውን በብቃት ሊወጡ
እንደሚገባም ረዳት ፕሮፌሰር አስማማው አስረድተዋል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ሥነ ተግባቦት መምህሩ ታደለ አምበሉ በምርጫ ወቅት በመረጃ እጥረት፣ በተሳሳተ እና
ሚዛናዊ ባልሆነ መረጃ ምክንያት ሊከሰት የሚችል ቀውስን ከወዲሁ በመከላከል ረገድ መገናኛ ብዙኃን ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡
እንደ ምሁሩ ማብራሪያ ምንም እንኳን በሀገሪቱ ያሉ ብዙኃን መገናኛዎች ቁጥር እና ተደራሽነት ውሱን ቢሆንም በምርጫ ወቅት
በተለየ መልኩ ሙያዊ ሥነ ምግባርን በተከተለ መልኩ በመንቀሳቀስ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጥረት ማድረግ
አለባቸው ብለዋል፡፡
ወቅቱ ግለሰቦች የማኅበራዊ ሚዲያ ባለቤት የመሆን እድልን የሚፈጥር መሆኑ ግላዊ አቋምን ብቻ የሚገልጽ መረጃ
በተጠቃሚዎቹ ይሠራጫል ነው ያሉት፡፡ ይህ ደግሞ አድማጭ፣ ተመልካች ወይም አንባቢው ስለ ምርጫው በቂ እና ተዓማኒነት
ያለው መረጃ ማግኘት አያስችለውም ብለዋል፡፡ በምርጫ ወቅት ትክክለኛ፣ ሚዛናዊ እና ወቅታዊ መረጃ ምንጭ የመሆን ኀላፊነት
እንደ ተቋም ከሚንቀሳቀሱ ብዙኃን መገናኛ የሚጠበቅ መሆኑን ተናግዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ያስተናገደቻቸውን ምርጫዎች እና እነሱን ተከትለው የተከሰቱ ግጭቶችን ያነሱት ረዳት ፕሮፌሰር
አስማማው አድማጭ፣ ተመልካች እና አንባቢው ከመገናኛ ብዙኀን ለሚያገኛቸው መረጃዎች የሚሠጠው ምክንያታዊ ምላሽ
ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ተደራሲው በተለይ በምርጫ ወቅት ሙያዊ የአዘጋገብ ስልት የሚከተሉ የመገናኛ ብዙኃንን ብቻ በመረጃ
ምንጭነት እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡
የጥላቻ፣ የሐሰት እና ሚዛናዊ ያልሆኑ መረጃዎችን በማሰራጨት ረገድ በተለይ በማኅበራዊ ሚዲያው ላይ ስለሚስተዋሉ በምርጫ
ወቅት ተደራሲው ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አመላክተዋል፡፡ ለሚያሰራጩት መረጃ ኀላፊነት መውሰድ የሚችሉ እና ተጠያቂነት
ያለባቸው ብዙኃን መገናኛ የትኞቹ ናቸው ብሎ መለየትም ከተደራሲው የሚጠበቅ መሆኑን መክረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- የማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous articleየታላቁ ህዳሴ ግድብ አጠቃላይ ግንባታ 79 በመቶ ደረሰ፡፡

Source link

Related posts

የሰላም ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች – ሽማግሌው ከሁስተን ቴክሳስ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች በዓል በዩኔስኮ በማይዳሰሱ ቅርሶች እንዲመዘገብ እየተሠራ መሆኑን የፌዴራል ቅርስና ጥበቃ ባልስልጣን ገለጸ።

admin

የመንግስት የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓትን ለማሻሻል የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ ስትራቴጂክ ዕቅድ ይፋ አደረገ

admin