51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን የአማራ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ፡፡

በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን የአማራ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወጣቶች “ይመራናል” የሚሉትን ዕጩ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመርጡ፤ ሂደቱ ሠላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን አይተኬ ሚናቸውን እንዲጫወቱ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተሠራ ነው። የአማራ ወጣቶች ማኅበር በክልሉ ዞኖችና ከተማ አሥተዳደሮች ለአባላቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶቹን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ዛሬም በባሕር ዳር ከተማ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ በተመለከተ የንቅናቄ መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት ተደርጓል፡፡

የውይይቱ ተሳታፊ ወጣት ውዴ ዘለቀ ለመራጭነት የሚያበቃትን ካርድ በማውጣት ተሳትፎዋን መጀመሯን እና የምርጫው ሂደት ሠላማዊ እንዲሆን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እንደምትሠራ ነግራናለች፡፡

እንደ ውዴ አስተያየት ወጣቶች ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ በማውጣት የመምረጥ መብታቸውን በመጠቀም መሳተፍ አለባቸው፤ መልካም ሥነ ምግባር በመላበስ ምርጫው ሠላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል፡፡

“ሀገር ሠላም እንድትሆን ምርጫ ትልቅ ዋጋ አለው” ያለችው ወጣት ውዴ ወጣቶችም መብታቸውን የሚያስከብርላቸውን የፖለቲካ ፓርቲ ካርድ በማውጣት መምረጥ አለባቸው ብላለች፡፡

ሌላው ወጣት ዳንኤል ሃይማኖት እንደገለጸው በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ማንን መምረጥ እዳለበት ወስኗል፡፡ ወጣቶችም የሚፈልጉትን ፓርቲ ካርድ በመሸለም የማይፈልጉትን ደግሞ ካርድ በመንፈግ በሠላማዊ መንገድ መብታቸውን መጠቀም እንዳለባቸው ተናግሯል፡፡

ወጣቶች ከዚህ በፊት በተካሄዱት ምርጫዎች ወቅት የተስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ እንዳይከሰቱ ለሠላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል ብሏል፡፡

“በአሁኑ ወቅት በአማራ ላይ እየደረሰ ያለው ችግር ይታወቃል፤ በቀጣዩ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ የምንመርጥበት ሂደት መፈጠር አለበት” ብሏል ዳንኤል። በምርጫ ሂደት የሚፈጠሩ ግጭቶች የሕይወት መጥፋትን፣ መፈናቀልን፣ የመሰረተ ልማት አውታሮች ውድመትን፣ የኢኮኖሚ ድቀትን፣ የማኅበራዊ አግልግሎት መስተጓጎልን እንደሚፈጥሩ ገልጿል፡፡

ይህ ደግሞ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዲበራከቱ መንገድ ስለሚከፍት ወጣቶች ምክንያታዊ ሆነው መንቀሳቀስ እንዳለባቸው መክሯል፡፡

የአማራ ወጣቶች ማኅበርም እየሠራ የሚገኘውን የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብሏል፡፡

ዳንኤል የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቀድመው “ምርጫ ይጭበረበራል” ከሚል የጥላቻ ሃሳብ በመውጣት ምርጫው ዴሞክራሲ መንገድን ተከትሎ እንደሚከናወን ማሰብ እንዳለባቸው ገልጿል፡፡

የአማራ ወጣቶች መኅበር ዋና ጸሐፊ ከፍያለው ማለፉ እንዳለው በመጪው ሀገራዊ ምርጫ ወጣቶች ሁለንተናዊና የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማኅበሩ የወጣቶችን ተነሳሽነት የማሳደግ ሥራ እየሠራ ነው፤ ወጣቶች ለፖለቲካ እና ለዴሞክራሲ ሥርዓት ያላቸው እይታ እንዲሰፋ የውይይት መድረኮችን እያዘጋጁ መሆኑን ተናግሯል፡፡

“ወጣቶች በምርጫው የነቃ ተሳትፎ የማያደርጉ ከሆነ በማይፈልጓቸው ፓርቲዎች ይተዳደራሉ፤ ባልመረጧቸውና በማይደግፏቸው የአሥተዳደር አካላት ውሳኔ ተገዢ ይሆናሉ፤ የተሻለ የዴሞክራሲ ሥርዓት ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋፆ ሳያበረክቱ ይቀራሉ” ብሏል፡፡

የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዓባይነህ ጌጡ በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ወጣቶችን በንቃት በማሳተፍ ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ እየሠሩ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ማኅበሩም በአሁኑ ወቅትም “የወጣቶች የነቃ ተሳትፎ ለሠላማዊ ምርጫ” በሚል መሪ ሃሳብ የውይይት መድረኮችን አዘጋጅቶ ምክክር እያደረገ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

“ወጣቱ ትውልድ በዓድዋ ላይ በደም ማኅተም የታተመውን አንድነት ጠብቆ ሀገርን የማሻገር ኃላፊነት ሊወጣ ይገባል” የአማራ ክልል የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ፕሬዝደንት ዳኝነት አያሌው

admin

በብሄር ሳንለያይ የአከባቢያችንን ሰላም እንጠብቃለን- የማንዱራ ወረዳ ነዋሪዎች

admin

የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ ነው – ጤና ሚኒስቴር

admin