87.71 F
Washington DC
June 14, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

በመንግስት የተከዳ ህዝብ፣ – ከገብረ ኣማኑአል | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

በመንግስት የተከዳ ህዝብበመሰረቱ የመንግስት ስልጣን የመገልገያ ሳይሆን የማገልገያ መሳሪያ ነው። በርግጥ ስልጣንን ተመርጦ ሳይሆን መርጦና ዘርፎ ለሚይዛት ይህ ትርጉም ላይኖረው ይችላል። አያንዳንዱ የፖለቲካ ሹም ደሞዝ፣ መኖሪያ ቤት፣ መኪና ወዘተ የሚያገኝበትና የሚከፈለውና ህይወቱን የሚመራው ከህዝብ  በግብር  በሚሰበሰበው ገንዘብ ነው። ያገሪቱ የጦር ሃይል የታጠቀው መሳሪያ፣ የጦር ኣውሮፕላን፣ አና ሌሎች ዘመናዊ መሳሪያዎች ሁሉ የተገዙት በህዝብ ሃብትና በስሙ ከሚገኝ ርዳታና ነገ ህዝቡ በሚከፍለው ብድር ገንዘብ አንጂ የመንግስት የሚባል ሃብት የለም። ለጦሩም ደሞዝ የሚከፈለው ህዝቡ በሚከፍለው ግብር  ነው።    ስለዚህ መንግስትም ሆነ የጦር ሃይሉ ተቋም የህዝብ መገልገያና ህዝብና ኣገር መጠበቂያ ተቋሞች ናቸው። ስለዚህ መንግስት የጦር ሃይል የህዝብን ሰላም ማስጠበቅ ሃላፊነትና ግዴታው አንጂ የሚሰጠው ችሮታ ርዳታ ኣይደለም።

 

በዚህ በኩል ያለው መንግስት ፍጹም ሃላፊነቱን ኣልተወጣም። በርካታ ዜጎች ለሞት ስደትና መፈናቀል ህይወታቸው ለአንግልትና ለመከራ የተዳረገው ባለፉት ሶስት ኣመታት  ነው። ለዚህ መንግስት ወይም ሰራዊቱና ደህንነቱ ኣቅም ኣንሷቸው ነው ለማለት ኣይቻል፣ ይልቁንም በሚያሳፍር ሁኔታ ይህ ሃይል ኣየዋለ ያለው ኣፍራሽ ለሆነ ርካሽ ዓላማ ነው። በመሆኑም ወገኖቻችን በታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በተለይ ኣሁን ባለንበት የሰለጠነ ዘመን ሊደረግ ቀርቶ ሊታሰብ የማይችል ጭፍጨፋ በወገኖቻችን ላይ ደርሷል።  ብዙ አናውቃለን የሚሉት መሪዎቻችን ክዚህ ኣናሳ ኣስተሳሰብና ኢሰባዊነት ሊርቁ ኣልቻሉም።

 

አንዳለመታደል ሆኖ የኣገራችን ኣመራር ከጊዜ ወደ ጊዜ አያሽቆለቆለ በመሄድ ላይ ይገኛል። መንግስታችን አጅግ ከመውረዱ የተነሳ ሰልጣን ከያዘ በኋላ ሰፊውን ኣገር ባግባቡ መምራት ሲቻል፣ ያረጀና ያፈጀ ንጹሃን ህዝብን የመጨፍጭፍ ስልት በመጠቀም የመስፋፋትን ቅዠት ለማሳካት በመውተርተር ላይ ይገኛል። ቢያንስ ከህውሃት ውድቀት መማር ኣለመቻሉ ያሳዝናል።

 

ያልታደለው ህዝብ ከ1966ቱ ኣብዮት ወዲህ በተከታታይ በመጡ መንግስታት መከራ ተቀብሏል ኣሁንም በመቀበል ላይ ይገኛል። በረሃብም ይሁን በመፈናቀልም ሆነ በስደት ሆኖ ቢያንስ በሰላም ሊያኖረው የሚችል ኣመራር በማጣቱ ህዝቡ አንደገና ለሌላ ዙር ትግል ተነስቷል። ይህም ሆኖ አውነተኛ የኢትዮጵያ ህዝብ ኣሁንም ጨዋነቱንና ኣብሮ የመኖር አሴቶቹን አንደያዘ ያለ ጨዋና የሰለጠነ ህዝብ መሆኑን አያሳየ ነው። አንዳለመታደል ሆኖ ግን መሪዎቹ ህዝቡ ካለበት ደረጃ አጅግ በመውረድ አጅግ ተራና የተናቀ ፖሊቲካን በዚህ ዘመን በማካሄዳቸው ባጭር ጊዜ ውስጥ የብዙሃን ህይወት አንዲጠፋና በህይወት የመኖር ዋስትና በብዙ ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ኣሳሳቢ አንዲሆን ኣድርጎታል። በመሪዎች ህሊና የተሳለው ያረጀ የነጻ ኣውጪነት በስልጣን ላይ የመቆየት ስነልቡና በመሆኑ፣ ኣገርን ባጠቃላይ ለመምራት የሚያስችል ደረጃ ላይ ወጥተው ሳለ ዘር በማጥፋት የራስን ዘር የማንገስ በሽታ ይዟቸው የሚያበላና የሚያከብር ህዝባቸውን ለከንቱ ዓላማ ሸጠው በሞትና በረሃብና በስደት ያሰቃዩታል። አንግዲህ በሰላም ምሩን ብሎ የሰገደላቸው መሪዎች ያለፉት መልማይ ኣባቶቻቸው የተጓዙበትን መንገድ በመምረጣቸው ህዝቡ በቃን አንዲል ኣስገድደውታል።

 

ራስን መከላከልና ለነጻነት ሰላማዊ ትግል ማድረግ ተፈጥሯዊ መብት ነው። በሴራ ፖለቲካ በመጠቀም ማፈንና ማኮላሸት ኣይቻልም። ይልቁንም ማክበርና መንከባከብ ይበጃል። በቅርቡ በኣሜሪካን ኣገር ባንድ ጥቁር ሰው ላይ በተደረገ የፖሊስ ግድያ ምክንያት ኣገሪቷ ስትናጥ ቆይታለች። ብዙ ችግር ደርሷል። ሆኖም ህዝብ ሌት ከቀን ባደረግ ትግልና በፈጣሪ ርዳታ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮች ለቤተሰቡ ካሳ የተከፈለ ሲሆን ገዳዩ ፖሊስ በፍርድ መድረክ ወንጀለኛነት ተበይኖበት ፍርዱን አየተጠባበቀ ይገኛል። ኣለምን የለወጠ የተባለለት ድል ተገኝቷል። የህዝባችንም ትግል በራሳቸው ሃብት በባርነት ለሚገዙ አንደኢትዮጵያ ላሉ ኣገሮች በህዝቡ ትግልና በፈጣሪ ፈቃድ `ዓለምን የለወጠ`  የሚባልለት ለውጥ ኣንደሚመጣ ተስፋችን ጽኑ ነው።

 

ትግላችን ወሳኝ የሆነ የስርዓት ለውጥ አስኪመጣ መቀጠል ኣለበት። ጥቂት ድል በተገኘ ቁጥር ነገር ዓለሙን ሁሉ ትተን ወደኑሮኣችን መመለስ ሳይሆን የኑሮኣችን ኣንድ ኣካል ኣድረገን ይዘን ይወክለናል የምንለው መንግስት አንኳን ቢኖረን ሳንተኛ ነቅተን ልንጠብቀው የሚገባ ነጻነታችንንና ደሞክራሲኣዊ ድላችንን መሆኑን በሚገባ መርምረን ልንረዳና ልናምንበት ይገባል።

 

በኣጭር ጊዜ ውስጥ በዚህ የፖለቲካ ወለድ ችግር ኑሮኣቸውን ባላቸው ሃብትና ጥሪት ለማሸነፍ ሲጥሩ በማይገባቸው ፖለቲካና በሸፍጥ የሚገኝን ስልጣንና ሃብት ለማስጠበቅ ሲባል የማያልቅ የፖለቲካ ክህደት ከቤት ከንብረታቸው የተፈናቀሉና ቤተሰቦቻቸው በግፍ የተገደሉባቸው ወገኖች ተገቢው ካሳና መልሶ መቋቋም በህግ ሊያገኙ ይገባል።

 

ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን ጭፍጨፋ ለማስቆም ብቻ ሳይሆን የስርዓት ለውጥ ለማምጣት በዓለማቀፍ ፍርድ ቤት የሚያካሂዱት ትግል ወጀሎችን ለፍርድ ከማቅረብና ካሳ ኣንዲከፈላቸው ከማድረግ በተጨማሪ ዘላቂ የስርዓት ለውጥ አስኪመጣ ድረስ በርትተው ሊገፉበት ይገባል።  ጅምላ ፍጅትንና ዘር ማጽዳትን ከኢትዮጵያ ፈጽሞ ኣስኪጠፋ ድረስ የዘር ማጽዳትን ለመከላከል ካገር ውጪ የተቋቋመውን ስብስብ በገንዘብ፣ በዕውቀትና ተግባራዊ ድጋፍ በማድረግ ለንረዳው ይገባል።

 

ሁላችንም በየዕምነታችን ኣገራችንን አንዲታደጋት ፈጣሪኣችንን ኣንለምን!

 

ኢትዮጵያውያን አንበርታ!

አግዚኣብሄር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅልን!

 

Source link

Related posts

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ15 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ለአጣዬ ተፈናቃዮች አስረከበ

admin

የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመግታት ሁሉን አቀፍ ምላሽ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለጹ።

admin

ʺአርፎ ያልተኛበት ተስፋና ድካሙ ፣ ሊፈታ ነው መሰል የቴዎድሮስ ህልሙ”

admin