68.38 F
Washington DC
June 22, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“በለውጥ እድገት ላይ የሚገኘው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በስፋት በመዳሰስ ተጽኖ ፈጣሪ መሆን አለበት” በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦች ትምህርት ክፍል መምሕር ቢሰጥ አያሌው (ዶ.ር)

“በለውጥ እድገት ላይ የሚገኘው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በስፋት በመዳሰስ ተጽኖ ፈጣሪ መሆን አለበት” በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦች ትምህርት ክፍል መምሕር ቢሰጥ አያሌው (ዶ.ር)

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 26/2013 ዓ.ም (አሚኮ) መገናኛ ብዙኃን ለአንድ ሀገር ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጉልህ ሚና ይጫወታሉ፡፡ በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደት፣ መልካም አስተዳደርን በማስፈን፣ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር፣ ልማትን በማፋጠን እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ለማኅበረሰቡ ማስገንዘብ የመገናኛ ብዙኃን ቀዳሚ ተግባር ነው፡፡

“ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!” በሚል መርሕ በየጊዜው ራሱን እያሻሻለ የመጣው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በስድስት ልዩ ልዩ ቋንቋዎች ቀዳሚ፣ ተዓማኒ እና ተመራጭ የመረጃ ምንጭ በመኾን እየሠራ ይገኛል፡፡ በቅርቡም ይበልጥ ተደራሽ ለመኾን አዳዲስ ማሻሻያዎችን እያደረገ ነው፡፡ ከነዚህ መካከል በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገራት ቋንቋዎች ተደራሽ መኾን፣ ሁለተኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ለመክፈት መዘጋጀት፣ የተቋሙን ብራንድ ማሻሻልና የሬዲዮ ጣቢያ ተደራሽነትን ማሳደግ ይጠቀሳሉ፡፡

የሬዲዮ ተደራሽነትን ለማሳደግ አዳዲስ የሬዲዮ ጣቢያዎችን መገንባትና የማቀባበያ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት ይገኙበታል፡፡ በሂደት ሁሉም የአማራ ክልል ዞኖች የሬዲዮ ባለቤት እንዲኾኑ በተቋሙ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ተይዟል፡፡ በቅርቡ የአማራ ኤፍ ኤም ጎንደር 105.1 የቀጥታ ስርጭት እንዲሁም የአማራ ኤፍ ኤም አዲስ አበባ 103.5 የሙከራ ስርጭት ጀምረዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የአማራ ኤፍ ኤም ደብረማርቆስ 95.1 መደበኛ ስርጭት ጀምሯል፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ሥነ ተግባቦች ትምሕርት ክፍል መምሕር ቢሰጥ አያሌው (ዶ.ር) እንዳሉት አሚኮ ተደራሽነቱን ለማስፋት የጀመረው እንቅስቃሴ በሚዲያውና በማኅበረሰቡ መካከል ጥብቅ ቁርኝት ይፈጥራል፡፡ በማኅበረሱ ውስጥ ያሉ ትክክለኛ ሁነቶችን በቅርበት ለመከታተልም ሰፊ ዕድል ይሰጣል፡፡ ይህም በስትራቴጂያዊ ዕቅዱ ለማሳካት ለታቀዱ ተግባራት ውጤታማነት መሠረት መኾኑን ነው ዶክተር ቢሰጥ የተናገሩት፡፡

በዓለም ላይ በርካታ ማኅበረሰብን በመድረስ ትልቅ ለውጥ በማምጣት ወደር የሌለው ኤፍ ኤም ሬዲዮ ነው ብለዋል፡፡ በኢትዮጵያም ግለሰቦች በእጅ ስልካቸው ሬዲዮ የማድመጥ ልምድ እያደገ መጥቷል፤ ሬዲዮ በሥራ ቦታ፣ በተሸከርካሪዎች ላይ ጭምር ተደራሽ ነው፤ ተደራሽነትን ከማስፋፋት ባለፈ የይዘት መረጣና የዝግጅት ጥራት ተቋሙ እምነት እንዲጣልበት ያደርጋሉ ነው ያሉት ዶክተር ቢሰጥ፡፡ መምህሩ እንዳሉት ለሕዝብ አማራጭ እይታዎችን ማሳወቅ፣ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን መዳሰስ፣ በውጪ ጉዳይ ፖሊሲ፣ በሰላምና በሀገራዊ ልማት ላይ አጀንዳ በመቅረጽ ግንዛቤ መፍጠር ይጠበቃል፡፡

በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ዝቅተኛ መኾኑን በማንሳት አሚኮ ማኀበረሰቡን ያሳተፈ ዝግጅት ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡ ለዚህም የተቋሙን ሠራተኞች አቅም ማሳደግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት፡፡

በሥራ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን ለመሙላት ዘጋቢዎች፣ አዘጋጆችና የተቋሙ የሥራ ኀላፊዎች እንዲሁም ለመገናኛ ብዙኃን ቅርብ የኾኑ ፖለቲከኞች ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ይገባል፡፡ ከዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግ እንደሚገባም መክረዋል፡፡ “በለውጥ እድገት ላይ የሚገኘው ሚዲያው ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን በስፋት በመዳሰስ ተጽኖ ፈጣሪ መሆን አለበት” ነው ያሉት፡፡

ዘጋቢ፡- ደጄኔ በቀለ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወደመ

admin

“ኢትዮጵያን ለማዳን ሁሉም አንድ መሆን ይገባዋል” የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም

admin

ሠራተኞችን ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም አዘዋውሮ ማሠራት የሚያስችል አሠራር ተግባራዊ ሊደረግ ነው

admin