82.22 F
Washington DC
June 21, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ቃልን ማክበር እና መፈጸም የለውጡ አመራር ቁልፍ ተግባር ነው- ዐቢይ አሕመድ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር አንድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተመርቆ ስራ ጀመረ።
ኢትዮጵያን ከልጆቿ፣ከታሪኳ፣ከባህሏ፣ከራሷ እና ከልጆቿ የማስታረቅ ስራ በመስራት ላይ እንገኛለን ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ፡፡
የህዳሴውን ግድብ በመጨረስ ዐይናችንን ከልማት ላይ ሳናነሳ ኢትዮጵያን ልማት ማረጋገጥ ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያን ከተፈጥሮ ጋር ለማስታረቅ ኢትዮጵያዊያን በአርንጓዴ አሻራ እና በገበታ ለሀገር የሚያደርጉትን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውስጥ እና የውጪ ጠላቶችን በመከላከል የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል ጠቅላይ ሚንስርት ዐብይ አህመድ፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘው ተሻገር ፥በፋብሪካው ስራ መጓተት የአማራ ክልል አመራር እና ህዝብ ተስፋ የቆረጠ ቢሆንም ከለውጡ በኋላ በተሰራ ስራ ይህ አመርቂ ውጤት እንደተገኘ ገልጸዋል፡፡
ከ2 ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተሰራው ስራ በርካት የስራ ዕድልን የፈጠረ፣ለአግሮ ኢንዱስትሪው ተመጋጋቢነት ሰርዓት የሚዘረጋ ነው ብለዋል፡፡
ከተረፈ ምርቱ የሚገኘውን ግብዓት ተጠቅሞ በተለያዩ ምርቶች ላይ ባለሀብቶች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል አቶ አገኘው ተሻገር፡፡

 

የስኳር ፕሮጀክቶች በበቂ ጥናት እና ዕውቀት ባለመሰራታቸው ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል ሲሉ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ተናግረዋል፡፡

ካለፍንበት መንገድ ተምረን የስኳር ፕሮጀክቶችን ለማስፋፋት የተፈጥሮ እድሎች ስላሉን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡

የጣና በለስ ቁጥር ሁለት የስኳር ፋብሪካ በለውጥ አመራሩ ቆራጥነት እና የሪፎርም አቅጣጫ በኢንዱስትሪው የተበላሹ ጅምሮችን በአጭር ጊዜ በማስተካከል ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር የሸንኮራ አገዳን ተረፈ ምርት በመጠቀም 45 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚቻል ሲሆን፣ 20 ሜጋዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪውን ወደ በሔራዊ የኤልክትሪክ ቋት መላክ ይችላል ብለዋል አቶ ወዮ ሮባ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ቃልን ማክበር እና መፈጸም የለውጡ አመራር ቁልፍ ተግባር ነው- ዐቢይ አሕመድ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.Source link

Related posts

ከብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

admin

የወሎን ሰላም ለመጠበቅ የሀይማኖት ተቋማት ሚና የጎላ ነው ተባለ

admin

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የሚደግፍ የ650 ቢሊየን ዶላር እንዲመደብ ተወሰነ

admin