61.99 F
Washington DC
May 11, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሚሠሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተናገሩ፡፡ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሚሠሩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 10/2013 ዓ.ም (አብመድ) ተዓማኒ፣ ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የረጂም ጊዜ ልምምድን፣
ስልጡን እና ለመብቱ ተሟጋች ማኅበረሰብን እና ጠንካራ ተቋማትን መገንባት ይጠይቃል፡፡ ምርጫ በአንድ ጀንበር ውስጥ
ተጀምሮ የሚጠናቀቅ ሳይሆን ሂደታዊ ነው፡፡ ከሂደቱ እስከ ውጤቱ በሀሳብ የማመን ብቃትን እና ውጤትን በፀጋ የመቀበል ሞራልን
ይጠይቃል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ኀይሎች የተለያየ ጥቅም እና ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና
ሕዝቦች፣ ልሳነ ብዙ ቋንቋዎች፣ መልከ ብዙ ባህሎች እና እምነቶች በመኖራቸው ምክንያት ሁሉንም በእኩልነት እና በፍትሐዊነት
ማስተናገድ የሚችል የዲሞክራሲ ባህል የመገንባት ሂደት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ቁልፍ አጀንዳዎች ናቸው፡፡
ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲ እና እኩልነት የሰፈነባት ሀገር ለመገንባት መሰረታዊ ከሚባሉት አላባዊያን መካከል አንዱ ምርጫ ነው፡፡
በምንም መልኩ አምባገነናዊ ስርዓተ መንግሥትን የማታስተናግድ ሀገር ለመገንባት ደግሞ በነፃ፣ በፍትሐዊ እና በዲሞክራሲያዊ
ምርጫ እና በሕዝብ ይሁንታን ያገኘ መንግሥት የሀገረ መንግሥት ምስረታው የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡
ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በብዙ መልኩ በመራጩ ሕዝብ እና በተመራጮቹ ፓርቲዎች ዘንድ ተስፋ ሰንቋል፡፡ በ2013ቱ ምርጫ
47 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር መዘጋጀታቸውን የገለጸው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው፡፡ ከገዥው ፓርቲ ብልጽግና በመቀጠል
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) እና እናት ፓርቲ ከፍተኛ እጩዎችን በማስመዝገብ ቀጣዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡
ለመሆኑ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች ስለቀጣዩ ምርጫ ምን ይላሉ? አብመድ በስልክ አነጋግሯቸዋል፡፡ ከመጋቢት 29/2012 ዓ.ም
ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ለማግኘት ሂደቶችን ሲያሟላ የነበረው እናት ፓርቲ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲ ሕጋዊ ሰውነት
የተሰጠው ባለፈው ታኅሣሥ መጀመሪያ አካባቢ ነበር፡፡ የእናት ፓርቲ ላዕላይ ምክር ቤት አባል እና የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ
አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ታመነ ሀብቱ (ዶክተር) የፓርቲያቸው ግብ ምርጫውን ማሸነፍ ቢሆንም ምርጫው ሠላማዊ፣ ነፃ እና
ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን አልሞ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት በሆነው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት ያክል የተራዘመው የዘንድሮው ስድስተኛ
ሀገራዊ ምርጫ ምንም እንኳን በጊዜ መጣበብ ምክንያት የመርሃ ግብር መደራረብ ቢኖርም ሠላማዊ እና ፍትሐዊ ምርጫ
እንደሚኖር ፓርቲያቸው እንደሚያምን ዶክተር ሀብቱ ነግረውናል፡፡ በምርጫው አሸናፊዋ ኢትዮጵያ እንድትሆን እና የሕዝብ ፍላጎት
እንዲፈጸምም በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት፡፡
የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ተረቅቆ እና ፀድቆ ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ አምስት ጊዜ ሀገራዊ ምርጫ ተድርጎ ነበር ያሉት የኢትዮጵያ
ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ናቸው፡፡ በአንዱም ምርጫ ግን የሕዝብ የስልጣን
ባለቤትነት አልተረጋገጠበትም ነበር ብለዋል፡፡ ይህም ሀገሪቱን ለዘመናት ለዘለቀ አለመግባባት፣ የኃይል አማራጭ እና
በመጨረሻም ሕዝባዊ እምቢተኝነት ዳርጓት እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ አዲስ ተስፋ ይዞ እንደመጣ አቶ ናትናኤል ገልጸዋል፡፡ ፓርቲዎች የሚወዳደሩት
ቢያሸንፉ ሀገር ለመምራት በመሆኑ በቅድመ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳዎቻቸው አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦቻቸውን ለሕዝብ ይፋ
ማድረግ ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል፡፡ የፓርቲዎች እንቅስቃሴም ሠላማዊ፣ ሕጋዊ እና የሌሎች ፓርቲዎችን መብት ያከበረ
መሆን እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡
መራጩ ሕዝብ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ እንዳለፉት አራተኛ እና አምስተኛ ምርጫዎች ተስፋ ቆርጦ ለአስፈፃሚው አካል ብቻ
የሚተወው እንዳይደለም ገልጸዋል፡፡ ሁለቱም አስተያየት ሰጭዎች ምሁራን እና ማኅበረሰብ አንቂዎችም ለሠላማዊ ምርጫ
ከሕዝቡ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ የሕዝቡ ምርጫ ፓርቲዎች በሚገቡት ቃል ኪዳን ላይ የተመሰረተ፣
በአማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦቻቸው ላይ ያተኮረ እና በቀጣይ ለሚመኟት ኢትዮጵያ ተስፋ ላይ የተመሰረተ መሆን እደሚገባውም
አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article338 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
Next articleለ9 ዓመታት አገልግሎት የሰጠው የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፓሊሲን ለመቀየር እየተሠራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

Source link

Related posts

ምዕራባውያን ፈርተውናል! – አንድነት ይበልጣል ሐዋሳ

admin

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቶኪዮ ኦሎምፒክ ዝግጅትን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

admin

አቶ ደመቀ ከተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ጋር ተወያዩ

admin