55.74 F
Washington DC
April 16, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ሊኖር እንደሚገባ አሚኮ ያነጋገራቸው እናቶች ተናገሩ፡፡

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሠላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የሁሉም ዜጋ የነቃ ተሳትፎ ሊኖር እንደሚገባ አሚኮ ያነጋገራቸው እናቶች ተናገሩ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 01/2013 ዓ.ም (አሚኮ) በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረውን ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በመርሐግብሩ መሠረት የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው፡፡ የምርጫው ሂደት ሠላማዊ እንዲሆን ከምንም በላይ እንደሚመኙ እና ለዚህም ሁሉም የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ አሚኮ ያነጋገራቸው እናቶች ተናግረዋል፡፡

ወይዘሮ ሰውዓለም ማናየ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡፡ ወይዘሮ ሰውዓለም ሀገር በምንም ሁኔታ ሠላሟ ሊታወክ እንደማይገባ ነው የገለጹት፡፡ ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫም የወደፊቱን ሀገራዊ እድገት መልካም እንዲሆን የሚሠራበት እንጂ ስጋት ሊሆን እንደማይገባ ተናግረዋል፡፡

“ውለን ለመግባት፣ ወልደን ለማሳድግ ሠላም ያስፈልጋል፤ ሠላም ስለፈለግነው ብቻ የሚመጣ ጉዳይ ሳይሆን እኛ ኀላፊነታችንን በአግባቡ መወጣት አለብን” ብለዋል፡፡

ወጣቶች በቀላሉ ለግጭትና ለሁከት የመዳረጋቸው እድል የሠፋ መሆኑን የገለጹት ወይዘሮ ሰውዓለም ይህ እንዳይከሰት እናቶች ልጆቻቸውን መምከር እና ማስተማር አለባቸው ብለዋል፡፡ ልጆች ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመጡ ጊዜ ሰጥቶ ማዳመጥ፣ ማወያየት እና ሀሳባቸውን መረዳት ይገባልም ነው ያሉት ወይዘሮ ሰውዓለም፡፡

የሕዝብን አዎንታዊ ተቀባይነት ያገኘ ምርጫ ለማካሄድ በሚደረገው ጥረት እናቶች ሠፊ ተሳትፎ ሊኖራቸው እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ወጣቶች ከምርጫ ባሻገር በማንኛውም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ እንዲሳተፉ እናቶችና መላው የቤተሰብ አባላት ኀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡

ሌለዋ ወይዘሮ ዓይናለም ተሾመ የደብረ ብርሃን ከተማ ነዋሪ ናቸው፡፡ የሠላም እጦት ቅድሚያ ችግር ውስጥ የሚከተው ሴቶች፣ ሕጻናት እና አረጋውያንን እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ እናም መጪው ሀገራዊ ምርጫ የሀገሪቱን መፃዒ ተስፋ የሚወስን በመሆኑ ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡ ለዚህም ወጣቶች የጎላ ሚና እንዳላቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪዋ የወላጆች እገዛ ሊታከልበት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

ወይዘሮ ዓይናለም በግርግር እና በሁከት የሚመሠረት ሀገር እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ “ከግርግርና ሁከት ወጥተን በመነጋገርና በመደማመጥ የምንፈጽመው ተግባር ውጤቱ አስደሳች ይሆናል” ነው ያሉት፡፡ በሀገራዊ ጉዳይ ወጣቶች የመፍትሔ አካል እንዲሆኑ ማሳተፍ እንደሚገባ እና ሁሉም “እኔ ያልኩት ብቻ ይሁን” ከሚል ሀሳብ ወጥቶ ወጣቶችን ለመረዳት ጊዜ መስጠት እንደሚገባ አስተያየት ሠጥተዋል፡፡

ወይዘሮ ዓይናለም ወላጆች ለልጆቻቸው የከፈሉት ዋጋ ሊተመን የማይችል መሆኑን አውቅው ጊዜያቸውን ሀገር ሊገነባ፣ የሰዎችን አመለካከት ሊቀይር በሚችል ሥራ ላይ ሊያተኩሩ እንደሚገባም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ወይዘሮ ሰውመሆን መለሰ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ አስተያየት የሰጡን ሌላዋ እናት ናቸው። የምርጫ ሂደቱ ሠላማዊ እንዲሆን እና ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ምርጫው ሠላማዊ በሆነ መንገድ መካሄዱ ቅድሚያ ተጠቃሚዎቹ እናቶች ናቸው ያሉት ወይዘሮ ሠውመሆን ለዚህም የነቃ ተሳትፎ መደረግ አለበት ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

አጼ ቴወድሮስ ከቋራ እስከ መቅደላ የሠሩትን ታሪክና አካባቢውን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ።

admin

“ሁለተኛው የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠት በአርሶ አደሮች መካከል ሊነሳ የሚችለውን የወሰን ግጭት በማስቀረት ልማትን ያፋጥናል” የአማራ ክልል ገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ቢሮ

admin

አፍሪካ ለዓለም ሰላም መስፍን የድርሻዋን እየተወጣች  ነው- አቶ ደመቀ መኮንን

admin