55.89 F
Washington DC
April 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኃይል በመዝለቅ ምንጊዜም ቢሆን የሚቆጫትን ስህተት መስራቷን ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ አስታወቁ።

ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በኃይል በመዝለቅ ምንጊዜም ቢሆን የሚቆጫትን ስህተት መስራቷን ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ አስታወቁ።

ባሕር ዳር፡ ጥር 16/2013 ዓ.ም (አብመድ) በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህርና የዓባይ ውኃ ጉዳይ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እና ዘላቂ ጥቅሟን የሚያሳጣት እንደሆነ አመላክተዋል።

ፕሮፌሰር ያእቆብ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ ሱዳን በመንግስትነት ሳትቋቋም በፊት በኢትዮጵያ እና በቅኝ ገዥዎች መካከል የተጀመረ ነው።

ችግሩን ለመፍታት የጋራ ኮሚሽን ተቋቁሞ የተለያዩ ልዑካን እና ኤክስፐርቶች ሐሳብ እየተለዋወጡ እንደሆነ አመልክተው፣ ውይይቱ ድንበሩ የት ይሁን የሚለውን ሳይቋጩ ሱዳን የኢትዮጵያን መሬት በኃይል ወስዳ የእኔ ነው ማለት ተቀባይነት የለውም ብለዋል። የሰራችው ስህተት ምንግዜም ቢሆን የሚቆጫት እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

ከብዙ አቅጣጫ ሲታይ እና ሲመዘን ሱዳን ዛሬ የድንበር ጉዳይ የምታነሳበት ወቅት እንዳልሆነ ያመለከቱት ፕሮፌሰሩ፤ የድንበር ጉዳይ ቢነሳ እንኳ ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት አለኝ ብላ በጉልበት ለመውሰድ የምትንቀሳቀስበትም ጊዜ አይደለም ብለዋል፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ረጅም ድንበር የምትጋራ፣ የሀገራቱ ህዝቦችም ለረጅም ጊዜ በሰላም አብረው የኖሩ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ይህ እውነታ በተጨባጭ ባለበት ሁኔታ እንደ አለመታደል ሆኖ የሱዳን መንግስት ለራሱ እና ለህዝቡ በማይጠቅም መንገድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

የሱዳን መሪዎች የአካባቢውን ሰላም፣ ልማት እና ጸጥታ በሚጎዳ መንገድ መራመድ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ የጠቆሙት ፕርፌሰሩ፣ አሁን ግን እጅግ በጣም ተለዋዋጭ በሆነና ለሱዳን ህዝብ በማይጠቅም፣ አካባቢውን ወደ ውዝግብ በሚወስድ መንገድ ውስጥ መግባቱን አመልክተዋል፡፡

ሱዳን ላይ የመጡ መንግስታት ብሄራዊ ጥቅማቸውን ከማስከበር ይልቅ የሶስተኝ ወገን አጀንዳ ይዞ የመንቀሳቀስ ሁኔታ ያሳያሉ ያሉት ፕሮፌሰር ያእቆብ፣ ሁኔታው በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ በሀገራቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ጉርብትና ወንድማማችነት የሚመጥን አይደለም ብለዋል።

በህዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ሱዳን ወጥ የሆነ አቋም እንደሌላት፣ አቋሟ በየጊዜው የሚለዋወጥ መሆኑን የጠቆሙት ፕርፌሰሩ፣ አሁን እየሄደችበት ያለው መንገድና የያዘችው አቋም የሱዳንን ብሄራዊ ጥቅም የሚጉዳ ፣ ዘላቂ ጥቅሟንም የሚያሳጣ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

ሱዳን የያዘችው አቋም ኢትዮጵያን ሊጎዳ የሚችል የአካባቢውን ልማትና ጸጥታ የሚያስ ተጓጉልና የሚያውክ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ የሶስተኛ ወገን ተለጣፊና ተላላኪ እንዲሁም ጠበቃ ሆና በዚህ መልኩ መቅረቧም የሚያስገርም እንደሆነ አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሱዳን ጎረቤቷ መሆኗን የሀገራቱ ህዝቦች ወደፊቱም ቢሆን ተጋግዘውና ተረዳድተው የሚኖሩ መሆናቸውን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ሱዳን በግድብም፣ በተቀረው የውኃ ልማት ሆነ በድንበር ጉዳዩ የኢትዮጵያን ጥቅም የማትጎዳ ከሆነ አሁንም ከሱዳን ጋር መልካም ጉርብትናን ለመፍጠር እንደምትፈልግ አስታውቀዋል፡፡

ትርጉም ያለው መርህ ያላቸው ሀገሮች ብሄራዊ ጥቅማቸውን እና ማንነታቸውን የሚጋፋ ነገሮችን እንደማይፈልጉ ሁሉ ኢትዮጵያውያንም ሉዓላዊነታቸውን በማስከበር በኩል ቀዳሚነት ያላቸው ናቸው፡፡ ወዳጅነትም፣ ትብብር ሆነ መተማመን ሊመሰረት የሚችለው ይህንኑ መርህ መሰረት አድርጎ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሱዳን አሁን ከያዘችው አቋም እንደምትመለስ ተስፋ ታደርጋለች፡፡ ካልተመለሰች ደግሞ ጥቅሟን ሳታስነካ ሱዳን ውሳኔዋን እስክታስተካክል ድረስ የራሷን ዳር ድንበር አስከብራ በግዛቷ ውስጥ የሚገኘውን ብሄራዊ ጥቅሟን ታስከብራለች።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንደምታጠናቅቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን የማዳከም ቋሚ ስትራቴጂ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች እንዳሉ ኢትዮጵያ ጠንቅቃ ታውቃለች፡፡ ሱዳንም የነዚህ ኃይሎች መሳሪያ ሆና ብዙ ጊዜ እንደማትዘልቅ ያመለከቱት ፕሮፌሰር ያእቆብ ከአዲስ ዘመን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሱዳንን ብሄራዊ ጥቅም የሚያከብር እና ሱዳንን የሚያስከብር አስተዳደር እንደሚመጣ ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ከ750 በላይ የቀድሞ የሕወሃት ልዩ ሃይል፣ ፖሊስና ሚሊሻ አባላት ከተሐድሶ ስልጠና በኋላ ወደየ አካባቢያቸው ሊመለሱ ነው

admin

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ እና ሌሎች ኃላፊዎች ከመምህራን ጋር ውይይት አካሄዱ

admin

አቶ ደመቀ ሩስያ ለወሰደችው መርህን መሰረት ያደረገ አቋም ምስጋና አቀረቡ

admin