64.54 F
Washington DC
June 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ በሰላማዊነቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር ገለጹ፡፡

ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ በሰላማዊነቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር ገለጹ፡፡

ባሕር ዳር: ግንቦት 10/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ የምታካሂደው የሕዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ይገባኛል ውዝግብ፣ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የጸጥታ ችግሮች ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ኾና ነው፡፡

መንግሥት የሚያወጣቸው ፖሊሲዎች እና ሕጎች በሕዝብ ተቀባይነትና ተፈጻሚነት ማግኘት እንዲችሉ ምርጫ ማድረጉ አማራጭ እንደሌለው ምሁራን ያነሳሉ፡፡ በዚህም በሀገሪቱ የሚካሄደው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ መከናወን ስለሚገባቸው ተግባራትና እና ሊፈጠሩ በሚችሉ የጸጥታ ስጋቶች ዙሪያ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ጥናት መምህር አበበ አሰፋ ጋር ቆይታ አድርገናል፡፡

በአብዛኛው ከምርጫ በኋላ የሚፈጠሩ ችግሮች በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት የተፈጠሩ ስህተቶች ነጸብራቅ ናቸው ይላሉ መምህር አበበ፡፡

የምርጫ አስፈጻሚ ተቋማት ገለልተኛነት ባልተረጋገጠባቸው እና የመቻቻል ባሕል ባልዳበረባቸው ሀገሮች ከምርጫ በኋላ ውጤቱን አለመቀበልን ተከትሎ ሁከትና ብጥብጥ እንደሚስተዋልም አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ በሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫም በቅድመ ምርጫ እና በምርጫ ወቅት ከሚፈጠሩ ስህተቶች ባለፈ ሀገሪቱ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ውስጣዊ እና ውጫዊ ኀይሎች በምርጫው ላይ እንቅፋት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ እንደስጋት አስቀምጠዋል፡፡ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ውኃ ሙሌት ድርድር ያሰቡትን አሳሪ ሕግ ማስፈጸም ያልተሳካላቸው የታችኛው የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት ምርጫውን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ገልጸውልናል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ እያደገ የመጣውን የቻይናን እና የሩስያን ፍላጎት ለመግታት አሜሪካ እና የአውሮፓ ሀገራት ኢትዮጵያን የመፎካከሪያ ሜዳ ማድረጋቸውን አንስተዋል፡፡ እነዚህ ሀገራት የሚፈልጉትን አሻንጉሊት መንግሥት ለመመስረት ካላቸው ፍላጎት በመነጨ ከውስጣዊ ኀይሎች ጋር በመቀናጀት ምርጫውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያ ላይ ጫና ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

ምርጫው ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ በሰላማዊነቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን፣ የሲቪል እና የሃይማኖት ተቋማት፣ የምርጫ ታዛቢዎች፣ አስፈጻሚዎች እና የጸጥታ አካላት በተደራጀ መንገድ ሊሠሩ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

የመቻቻል ባሕልን ማዳበር፣ በምርጫ ውስጥ ልዩነትን ተቀብሎ አብሮ መኖር ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡ ችግሮች ከተከሰቱም መንግሥት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት የችግሩን ምንጭ መመርመር፣ የተሳታፊ አካላትን ፍላጎት መረዳት እና መለየት እንዲሁም ሐሳባቸውን እንዲገልጹ በማድረግ እንደሚናቸው እና እንደ ግንዛቤያቸው ደረጃ እርምት መውስድ ይገባል ነው ያሉት፡፡

በሕግ እና በጸጥታ ተቋማት ብቻ እርምጃ ከመውሰድ ባለፈ ፖለቲካዊ መፍትሔ ማስቀመጥ፣ በእርቅ እና በውይይት ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኀን ምርጫው ሰላማዊ ኾኖ እንዲጠናቀቅ የተካረሩ አቋሞችን ከማስተናገድ ይልቅ ሥነ ምግባርን አክብረው ሊሠሩ እንደሚገባቸው ነው ያስገነዘቡት፡፡

ማኀበረሰብ አንቂዎችም ከወገንተኝነት ወጥተው ትክክለኛ መረጃ መስጠት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ፓርቲዎች ‹‹ሁሉም ሕዝብ እኔን ይደግፋል፤ እኔ ብቻ ነው የምመረጠው›› ከሚል አስተሳሰብ ተላቅቀው ሕግን እና የሕዝብን ድምጽ ለማክበር ዝግጁ ሊሆኑ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

Source link

Related posts

ምርጫ ቦርድ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳን ነገ ይፋ ሊያደርግ ነው

admin

መቀንጨርን ለመከላከል ተቋማት ተቀናጅተው በአመጋገብ ላይ እየሠሩ እንደሚገኝ የላይጋይንት ወረዳ የሰቆጣ ቃልኪዳን ገለጸ፡፡

admin

በቲቢ በሽታ የመያዝ መጠንን በ90 በመቶና የመሞት መጠንን በ95 በመቶ ለመቀነስ አቅዶ እየሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡

admin