71.73 F
Washington DC
June 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“መካሪ የሌለው ንጉስ ያለአንድ አመት አይነግስ” – ከወይራው እርገጤ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

“መካሪ የሌለው ንጉስ ያለአንድ አመት አይነግስ” “

መካሪ የሌለው ንጉስ ያለአንድ አመት አይነግስ” ይላል ብሂሉ፡፡ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጣበት ጊዜ ህዝቡ በወያኔ 27 አመት የግፍ አገዛዝ የተንገፈገፈ ስለነበረ ንቅል ብሎ ወጥቶ ሙሉ ድጋፉን ሰጥቶት ነበረ፡፡አለምም ጉድ እስከሚል ድረስ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ነጻነት የናፈቀው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አስደማሚ ድጋፎችን በማሳየት የድጋፍ ስሜቱን ገልጾለት ነበረ፡፡በኦሮሙማ አክራሪወች ከተጠመዘዘው የኦሮሞ ክልል በስተቀር፡፡ ይህ የሆነ ሀቅ ነው፡፡

የሆነው ሁሉ ሆነና ትንሽ ቆይቶ አብይ አህመድ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዝብ የጣለበትን እምነት ትቶ ወደ ኦሮሙማ አሮንቃ ተወተፈ፡፡ አብይ አህመድ ለዚህ ድርጊቱና ብሎም አሁን ላለበት ውድቀቱ ምክንያቱን ራሱ የሚያውቀው ሲሆን ታሪክም እውነቱን ወደፊት ይፋ ያወጣዋል፡፡ እኛም በበኩላችን አሁን ላለንበት የውድቀትና የውርደት ጊዜ እንዴት እዚህ ደረጃ ደረስን ብለን ብዙ መላምቶችን ልንሰጥ እንችላለን፡፡ ምሳሌ፦ አብይ በስልጣን እያለ ይህ ሁሉ ዘግናኝ ጉድ የተፈጸመው ሰውየው በኦሮሙማ ታጥሮና ተገድዶ ምንም ማድረግ ስላልቻለ ነው፡ ወይንም ከአቅሙ በላይ ችግሮቹ አፋጥጠው ይዘዉት ስለነበረ ነው ፡ ወይንም ሰውየው ቀድሞውንም ቢሆን ለኦሮሞ የበላይነት እንጅ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል የሚሰራ ሰው አልነበረም ሌላም ሌላም …ወዘተ ብለን የየራሳችንን ግምት ልንሰጥ እንችላለን ፡፡ ህዝቡ የአብይ አህመድን ያኔ የተናገራቸውን የማታለያ ቃሎች ሰምቶና ሰውየውንም አምኖ ‘አሁን ገና የእድሜ ልክ መሪ አገኘን ’ ብሎ ተስፋ እንዳልጣለበት ሁሉ ሰውየው “እርፍና ነው” ብሎ ያመነ ቢሆንም የህዝቡ ተስፋ እንድሟጠጥና እምነቱ እንዲጠፋ የሚያደርጉ አያሌ የጅልና የድድብና ስራወችን ሰራ፡፡ ህዝብን በጠራራ ጸሀይ አስጨፈጨፈ፡፡ የንጹሀንን አስከሬን በዘር ቆጠረ፡፡አገርን አስወርሮ ውርደትን አስከተለ፡፡ እርሱ መሪ በነበረባቸው በእነዚህ 3 አመታት ውስጥ የተሰሩት አይን ያወጡ የዘረኛነት አሰራሮች፡ የሚያሳዝኑ ማፈናቀሎች፡ ገሀድ የወጡ ዘረፋወች፡ የሚዘገንኑ ግዲያወች ሰቅጣጭ ጭፍጨፋወችና የዘር ማጽዳቶች አገሪቱ በታሪኳ አጋጥሟት አያውቅም፡፡ በሰው በላው የወያኔ ጊዜም ቢሆን እንደዚህ ያለ ጉድ በዚህ ደረጃ አልታየም አልተሰማም፡፡ ለዚህም ነው በአብይ አመራር ጊዜ የተሰሩት ወንጀሎችና ግፎች ከስህተቶች የመነጩ ሊሆኑ የማይችሉት፡፡አብይ በጦሩና በደህንነቱ ክፍል ያደራጃቸውን የኦሮሙማ ሰንሰለቶች ወደጎን አቆይተን በሲቪሉ ብቻ ከመደባቸው መደዴወች ውስጥ ሽመልስ አብዲሳንና ታዬ ደንደአን ለይተን ብንመለከት ከእውቀት የጸዱት እነዚህ ሁለቱ ከአፋቸውም ከድርጊታቸውም የሚወጣውን የጥጋብ ቅርሻት ማገናዘቡ ብቻውን ሰውየው የገባበትን አሮንቃ የትየለሌነት ለማወቅ አያዳግትም፡፡

ህዝቡ አብይ አህመድን ጠብቆት የነበረው ከዘረኝነት በጸዳ መልኩ አገሪቱን ከማጥ አውጥቶ ወደ ዲሞክራሲ ይመራታል፡ ወያኔ በህዝብ ውስጥ የዘራውን የዘረኝነት መርዝና ወደ እርስ በርስ የመጠፋፋት ጎድና ዘግቶ ሁሉም የአገሪቱ ህዝብ በእኩልነትና በአንድነት የሚኖርበት ስርአት በአዝጋሚ መልኩ ቢሆንም ወደዚያው ይወስደናል የሚል ነበር፡፡ የህዝቡም ቀጣይ ተስፋ የነበረው አብይ በዚህ አድራጎቱ ለብዙ ዘመናት አገር በማስተዳደሩ ስራ ቀጥሎ እንደተወደደና እንደተከበረ ይኖራል የሚል ጽኑ እምነት ነበር፡፡ ይህ ህዝባዊ እምነት አሁን ላይ አፈር ድሜ በልቷል፡፤ ሊመለስም ከቶውንም አይችልም፡፡ በግፍ የተጨፈጨፉ የብዙ ንጹሀን ስወች ደም ይጮሀል፡፡ የቀሪው ህዝብም ልቡ ደምቷልም፡፡ሸፍቷልም፡፡ እምነቱም ተሟጥጦ አልቋል፡፡ አገሪቱም በሁሉም አቅጣጫ አየደማች ነው፡፤ ተደፍራለችም፡፡ ተወራለችም፡፡ ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ኢትዮጵያ ከእንግዲህ ወዲያ በአብይ አህመድ ስር ሆና ነገሮች ሊሻሻሉ የሚችሉበት ደረጃ አይኖርም፡፡ይህ አልፏል፡፡ አብይ አህመድ በለመደው የማታለል፡ ወይንም በጦርና በጭፍጨፋ ስልት አለበለዚያም በሁለቱም ጥምረት አገዛዙን ለማስቀጠል ቢሞክርና የሚቀሩት ትንሽ የስልጣን ጊዜያት የሚኖሩት ቢሆን በእነዚሁ ጊዜያት ውስጥም ቢሆን ችግሮቹ ከመባባስ በስተቀር መፍትሄ ሊያገኙ ፈጽሞ አይችሉም፡፡ይህንን ማድረጊያው  ጊዜው አልፏልና ፡፡

ስለዚህ አሁን ላይ አገሪቱንም ጨርሶ ከሚያጠፋ የእርስ በእርስ ጦርነት (Full Scale Civil War) ሊያወጣት የሚችል፡ አብይ አህመድን ራሱንም በህግ ተጠያቂ ከመሆን ባሻገር ሊያድነው የሚችል አንድ እድል ብቻ ቀርቶታል፡፡ይህ እድልም ከሁሉ በፊት ከቅን ልብ የሚመነጭ መሆንን ይጠይቃል፡፡ አብይ የመጨረሻው አማራጭ ከቅን ልብ በመነጨና በይቅርታ መንፈስ ሊመራ የሚገባው ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን ያካተተ ብሄራዊ የአንድነትና የጋራ ህዝባዊ ዲሞክራቲክ ኮንፈረንሰ በአስቸኳይ መጥራትና ከዚህ ኮንፈረንስ የሚወጣ ውስኔን በተግበር ላይ ማዋል ብቻ ነው፡፡ ይህንን ሳያደርግ ቀርቶ አሁንም ምርጫ እያለ የሚያፌዝ ከሆነ ውጤቱ የሚሆነው ሁሉንም የሚበላ ሰደድ እሳት ላይ ቤንዚን ማርከፍከፍ ነው፡፡

ኦሮሙማ አሁን የሚያደርገው የአማራን ህዝብ የመጨፍጨፋ ስራ በዚያው የሚቆም የሚመስላቸው ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ካሉ ተሳስተዋልና ከአሁኑ መንቃትና የአማራን ለተረኞች የአልገዛም ባይነት አመጽን መቀላቀል አለባቸው፡፤ ጅቡ ኦሮሙማ ማንንም አይምርምና፡፡ ስለሆነም የአማራው ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር ለኢትዮጵያ መዳን በስፋት መስራት አለበት፡፡ አማራው በቀጥታ በኦሮሙማም ሆነ በሆድ አደሩ የአማራ ብልጽግና አማካይነት ከሚደረግበት የግፍ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት የሚያደርገውን ወሳኝ ትግል ወደላቀ ደረጃ ማሳደግ አለበት፡፡በጸረ ወያኔ ትግሉ ወቅት እንዳሳየው ብቃት ሁሉ ዛሬም ትግሉን በተሻለ የአደረጃጀት መልኩ የአማራው ብቸኛ አለኝታ በሆነው አብን – አማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ዙሪያ በመሰባሰብ ተጋድሎውን በተቀነባበረ አሰራር ጫፍ እስከጫፍ በማቀጣጠል አስተማማኝ ነጻነት እስከሚያገኝ ድረስ ያለማቋረጥ ተጋድሎውን መቀጠል አለበት፡፡

Source link

Related posts

“የተለያዩ የመሠረተ ልማት የሌለባቸው አካባቢዎች ቢገጥሙም ከኅብረተሰቡ ስለማይበልጡ ሳንታክት ልናገለግል ይገባል” የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ የህክምና ዶክተሮች

admin

በቀን ብርሃን ኢትዮጵያዊ፤ በጨለማ ኦሮሙማ – ከፈለቀ አለሙ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin

ኢትዮጵያዊ አንድነት በእኩልነት – ጆቢር ሔይኢ ከሁስተን ቴክሳስ | Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider

admin