51.91 F
Washington DC
May 12, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

መቀንጨርን ለመከላከል ተቋማት ተቀናጅተው በአመጋገብ ላይ እየሠሩ እንደሚገኝ የላይጋይንት ወረዳ የሰቆጣ ቃልኪዳን ገለጸ፡፡መቀንጨርን ለመከላከል ተቋማት ተቀናጅተው በአመጋገብ ላይ እየሠሩ እንደሚገኝ የላይጋይንት ወረዳ የሰቆጣ ቃልኪዳን ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሥርዓተ ምግብ ባለሙያዎች እንደሚሉት መቀንጨር የአስተሳሰብ አድማስን
በመቀነስ የእርስ በርስ አለመግባባትንና የፈጠራ ችሎታን በማዳከም ሀገርን ለድህነት ይዳርጋል፤ የአደጉት ሀገራት ሚስጥርም
ሥርዓተ ምግብ ላይ ትኩረት ሰጥተው በመሥራታቸው እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡
አዕምሮ ልማት ላይ የሠራ ሀገር ተረካቢ ዜጋ በቀላሉ ለመፍጠር ሥርዓተ ምግብ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንደሚገባ ነው
የሥርዓተ ምግብ ባለሙያዎች የሚያስረዱት፡፡ በተለይ ከእርግዝና ጀምሮ ያሉትን አንድ ሺህ ቀናት ሥርዓተ ምግብ ላይ ትኩረት
ሰጥቶ በመሥራት መቀንጨርን መከላከል እንደሚቻል ያስረዳሉ፡፡ በደቡብ ጎንደር ዞን ላይጋይንት ወረዳ መቀንጨርን ለመከላከል
እየተሠራ ያለውን ሥራ አስመልክቶ ነዋሪዎችን እና ባለሙያዎችን አነጋግረናል፡፡
በወረዳው ቀበሌ16 አሚኮ ያነጋገራቸው እህትእሸት አበራ እና ወርቄ አከለ እንዳሉት መቀንጨርን ለመከላከል ከእርግዝና ጀምሮ
ያሉትን አንድ ሺህ ቀናት በጤና ባለሙያዎች በተሰጣቸው የሥርዓተ ምግብ አዘገጃጀት ስልጠና መሰረት የተለያዩ የጓሮ
አትክልቶችን በማልማት እና ዶሮ በማርባት እንቁላል እንደሚጠቀሙ ነግረውናል፡፡ የዶሮ እርባታ እና አትክልት ልማትን አጠናክረው
እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል፡፡
በላይጋይንት ወረዳ የቀበሌ 16 አምባ ማሪያም የጤና ባለሙያዋ ቦሴ ገላው እንደገለጸችው መቀንጨርን ለመከላከል ከእርግዝና
ጀምሮ ያሉትን አንድ ሺህ ቀናት አጥቢዎች እና ነፍሰ ጡር እናቶች ስብጥሩን የጠበቀ የምግብ አዘገጃጀት እንዲተገብሩ
በቀበሌዎች ለሚገኙ ሁሉም ነፍሰ ጡር እናቶች ትምሕርት እየተሰጠ ይገኛል፤ ለዚህ ደግሞ እናቶች ዶሮ እያረቡ ነው፤ አትክልትና
ፍራፍሬም በጓሯቸው እያለሙ ይገኛሉ፡፡ በየወሩም የሥርዓተ ምግብ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ ወቅትም ሁሉም እናቶች
ተቀብለው እየተገበሩ መሆኑን ነግራናለች። በስልጠናው ባለቤቶቻቸው እንዲሳተፉ መደረጉንም ነው የገለጸችው።
የላይጋይንት ወረዳ የሰቆጣ ቃል ኪዳን አስተባባሪ አለዓለም ጉግሳ እንዳሉት የሰቆጣ ቃልኪዳን በአማራ ክልል ተከዜ ተፋሰስ
በሚገኙ 27 ወረዳዎች ላይ መቀንጨርን ለመከላከል እየተሠራ ይገኛል፡፡ ከዚህ ውስጥ በደቡብ ጎንደር ዞን ላይጋይንት፣ እብናት
እና መቀጠዋ ወረዳዎች ይገኙበታል፡፡ መቀንጨርን ለመከላከል 13 ሴክተር መሥሪያ ቤቶች በመቀናጀት በአመጋገብ ላይ
በጥምረት እየሠሩ እንደሚገኝ አስተባባሪው ገልጸዋል። ለዚህም ቀበሌዎች ጭምር መቀንጨርን ለመከላከል በጀት መድበው
እየሠሩ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ሰቆጣ ቃልኪዳን ሥራ ሲጀምር መቀንጨር በሀገር አቀፍ ደረጃ 49 ነጥብ 7 በመቶ ነበር። በዚህ ወቅትም ወደ 45 በመቶ ዝቅ
ማድረግ እንደተቻለ ገልጸዋል።
በወረዳው የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ የዘር ስርጭት መካሄዱንም አመላክተዋል፡፡
የላይጋይንት ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አበበ ላቀው መቀንጨርን ለመከላከል የጓሮ አትክልት እና ፍራፍሬ ማልማት
በትኩረት እየተሠራ መሆኑን ገልጸውልናል፡፡
በወረዳው አስር ቀበሌዎች የሚገኙ እናቶች የጓሮ አትክልት እንዲያለሙና የእንስሳት ተዋጽኦ እንዲጠቀሙ በማድረግ የሥርዓተ
ምግብ መንደር መፍጠር መቻሉን ነግረውናል። ሌሎች እናቶችም በቤታቸው እንዲተገብሩት በአርሶአደር ማሰልጠኛ እና በጤና
ጣቢያዎች የምግብ አዘገጃጀት የልምድ ልውውጥ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የሥርዓተ ምግብ ሥራውን ዘላቂነት ለማረጋገጥ
ቀበሌዎች በጀት በመመደብ ዘር ማግኘት ለማይችሉ እናቶች ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ጤና መምሪያ የሥርዓተ ምግብ ባለሙያ ዘወርቅ መንበር እንደነገሩን ደግሞ በዞኑ በ15 ወረዳዎች መቀንጨር
መከላከል ላይ እየተሠራ ይገኛል፡፡ ላይጋይንት ወረዳ ደግሞ ለሥርዓተ ምግብ በጀት በመመደብ መቀንጨርን በመከላከል ሥራ
የተሻለ መሆኑን አንስተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ በወረዳው የሥርዓተ ምግብ መንደር በመመስረት የጓሮ አትክልት፣ ፍራፍሬ
በማልማት እና ዶሮ በማርባት እንዲጠቀሙ እየተሠራ ነው፡፡ ተሞክሮውንም ወደ እብናት፣ ሊቦ ከምከም፣ መቀጠዋ ወረዳዎች
ማሳፋት መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ባለሙያው እንዳሉት መቀንጨር ምግብ በማጣት ብቻ የሚከሰት ሳይሆን የአመጋገብ ሥርዓትን ካለማወቅ የሚከሰት ነው፡፡
“መቀንጨር ሰዎች በሥራቸው ውጤታማ እንዳይኾኑ ያደርጋል” ብለዋል ባለሙያው፡፡ ችግሩን ለመከላከል ነፍሰጡር እናቶች
ሲመገቡ ከነበረው ሁለት ተጨማሪ ምግብ ሊያገኙ ይገባል፤ ከወለዱ በኋላ ደግሞ ከስድስት የምግብ አይነቶች በ24 ሰዓት
ውስጥ ቢያንስ አራቱን መመገብ አለባቸው፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ የቤተሰብ እና የአካባቢውን ማኀበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ
ተቀዳሚ ሥራ ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡
እ.አ.አ በ2019 የተጠናው ጥናት እንደሚያሳየው መቀንጨር በሀገር ደረጃ 37 በመቶ ፤ በአማራ ክልል ደግሞ 41 ነጥብ 3 በመቶ
ነው፡፡ በኢትዮጵያ 16 በመቶ ተማሪዎች በመቀንጨር ምክንያት ይደግማሉ፡፡
በመቀንጨር ችግር ኢትዮጵያ በዓመት 55 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ታጣለች፡፡
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“ኢትዮጵያ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት በኩል እንዲካሄድ የያዘችው አቋም ለሕብረቱ ያላትን ክብርና እውቅና የሚያሳይና የሚደነቅ ነው” መሀመድ አል አሩሲ አክቲቪስትና የፖለቲካ ተንታኝ

Source link

Related posts

በ169 ታዳጊዎች ላይ ሊፈፀም የነበረ ያለ እድሜ ጋብቻ እንዲቋረጥ ተደረገ

admin

ጠ/ሚ ዐቢይ በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለአፍሪካ ህብረት ሰላምና የደህንነት ምክር ቤት ማብራሪያ ሰጥተዋል

admin

የተፈራው አልቀረም ሙሉ ነጋ(ዶ/ር)  ዳግማዊ ስብሃት ነጋን ሆነው መጥተዋል!?! (ታምሩ ገዳ)

admin