68.25 F
Washington DC
May 13, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

“ሕወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሐሳብ መቅረቡ በሀገር ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ ሚና ይኖረዋል” የሕግ ባለሙያ“ሕወሓት እና ሸኔ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሐሳብ መቅረቡ በሀገር ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ ሚና
ይኖረዋል” የሕግ ባለሙያ
ባሕር ዳር: ሚያዝያ 23/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሽብር ወንጀል በዓለም አቀፍ ደረጃ አደገኛ ከሚባሉ የወንጀል አይነቶች ተርታ
ይመደባል፡፡ የሃይማኖትን፣ የፖለቲካ እና የርዕዮተ ዓለም ፍላጎትን ለማራመድ ሕዝብን ማስገደድ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት
ማድረስ፣ ሰውን ማገት፣ በንብረትና በተፈጥሮ ሀብት ወይንም በአካባቢ እንዲሁም በታሪካዊ ቅርሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረስ፣
ማኅበራዊ ተቋማት አገልግሎት እንዳይሰጡ ማስተጓጎል የሽብር ወንጀል መሆኑን የሕግ ባለሙያው አቶ ኪያ ጸጋዬ ተናግረዋል፡፡
የሽብር ወንጀል ማኅበረሰቡ ደኅንነት እንዳይሰማው እና ከፍተኛ የስነልቦና ጫና የማሳደር ዓላማ አለው ብለዋል፡፡
አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጸመውም በተደራጀ እና ትስስር ባለው ቡድን ነው፤ አመራሮች እና አባላት ያሉት ሲሆን እንደ አልቃይዳ፣
ቦኮሀራም፣ አይ ኤስ አይ ኤስ የመሳሰሉት የሽብር ቡድኖች ለዚህ ሁነኛ ምሳሌ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሽብር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ 1176/2012 ለወንጀሉ የሰጠው ትርጓሜ ከአለማቀፍ
ድንጋጌዎች ጋር የሚገናኝ ነው፡፡ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የውሳኔ ሃሳብ የቀረበባቸው ሕወሓት እና ሸኔ የተባሉ ቡድኖችም
በአዋጅ ቁጥር 1176/2012 እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከለከሉ ተግባራትን እንደፈጸሙ አመላክተዋል፡፡ በተለይም ብሔራዊ
ደኅንነትን አደጋ ላይ መጣል፣ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ማገት፣ የመንግሥት ባለስልጣናትን መግደል፣ መንገዶችን መዝጋት፣
ሰላማዊ ተጓዦችን መግደል፣ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ማስተጓጎልና ሰላማዊ ሰዎች የደኅንነት ስጋት እንዲያድርባቸው
የሚያደርጉ ወንጀሎችን መፈጸማቸው ቡድኖቹ በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ የሚያስችላቸው ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያውያን ሰላም ላይ ጫና መፍጠራቸው እና ሀገሪቱ እንዳትረጋጋ በማድረግ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ
ጫና ማድረሳቸውን አብራርተዋል፡፡
መንግሥት በተለመደው የሕግ አግባብ ጉዳዩን ለማዬት በሆደሰፊነት ቢመለከትም የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅምና ብሔራዊ
ደኅነትን የሚገዳደሩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠላቸውን አንስተዋል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ቡድኖች በሽብርተኝነት እንዲፈረጁ
በተለየ አግባብ መመልከት ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
እንደ ሕግ ባለሙያው ማብራሪያ እነዚህ አካላት ድጋፍ ከሌላቸው ብዙ ርቀት መሄድ ስለማይችሉ ቡድኖቹን በሽብርተኝነት
እንዲፈረጁ ማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ድጋፍ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የፍረጃው ዋና ዓላማም የድጋፍ ምንጫቸውን በማስቀረት የተጠናከረ ርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡
ማኅበረሰቡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የነዚህ ቡድኖች ዓላማ አስፈጻሚ እንዳይሆን ፍረጃው በአስገዳጅነት የሚከለክል መሆኑንም
ገልጸዋል፡፡ በዋናነት የመንግሥት መዋቅር እና የጸጥታ አካላት ይህንን ተገንዝበው የሚያከናውኑትን ተግባር በዚህ መልኩ የተቃኘ
እንዲሆን ዕድል ይፈጥራል፡፡ በሀገር ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን በመቀነስ ረገድም ሚና ይኖረዋል ብለዋል የታሪክ ባለሙያው፡፡
ሽብርተኝነት እንደየሀገሩ የሚለያይ ቢሆንም ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጡ ስምምነቶች አሉ የሚሉት
ባለሙያው ከነዚህ መካከል አጎራባች ሀገራት ሰላማዊ ግንኙነት በመፍጠር የሽብር ቡድኖች መሰረት እንዳይኖራቸው በጥምረት
መሥራት ተጠቃሽ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
እነዚህ ቡድኖችንም ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራትና ከዓለምአቀፍ ተቋማት ጋር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ለማጥፋት ጠንክራ
መሥራት ይጠበቅባታል ብለዋል፡፡
ሽብርተኝነትን መከላከል መንግሥትን የመደገፍና ያለመደገፍ ጉዳይ ሳይሆን የሀገርን ህልውና ማስቀጠል በመሆኑ እያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊ ሽብርተኝነት በጋራ መከላከል ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
Previous article“የአማራ ሕዝብ ጠላቶች የቱንም ያህል ቢበረቱ አሸናፊ መሆን ግን አይችሉም።” አቶ አብርሃም አለኸኝ

Source link

Related posts

በአማራ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን በአጣየ አካባቢ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈታ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡

admin

በኖርዲክ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉበት የሕዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃግብር በመጪው ቅዳሜ ይካሄዳል፡፡

admin

የአድዋን ድል ስናከብር የተሸረሸረውን አንድነትና ኢትዮጵያዊ እሴት ለመመለስ ቃል እየገባን መሆን አለበት – ዶክተር ሙሉ ነጋ

admin