65.28 F
Washington DC
June 15, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ እየሰጠ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለጸ።
ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በመራጮች ምዝገባ ሂደት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሔ እየሰጠ መሆኑን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ገለጸ።
ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባን ሂደትን በተመለከተ
ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ ወቅታዊ የምርጫ ሂደትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ቦርዱ በመግለጫውም ከምርጫ
ሂደት መካከል ዋና የሆነውን የመራጮች ምዝገባን እያከናወነ ይገኛል ብሏል፡፡ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው ጣቢያዎች
ቁጥር 43 ሺህ 17 እንደሆኑም ተጠቅሷል።
ምርጫ ቦርዱ በመራጮች ምዝገባ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንም አቅርቧል። የመራጮች ምዝገባ ዘግይቶ መጀመር (በቁሳቁስ
ስርጭት የተነሳ)፣ የመራጮች ምዝገባ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት የተመዝጋቢዎች ቁጥር ዝቅተኛ መሆን፣ የመራጮች ምዝገባ
ከተጀመረ በኋላ የምርጫ ጣቢያዎች እና የተመዝጋቢዎች አለመመጣጠን በተለይ በአዲስ አበባ በጋራ መኖሪያ ቤቶች
የአስፈጻሚዎች ክፍያ መዘግየት፣ በተወሰኑ ቦታዎች (በተለይ በአዲስ አበባ) የአስፈጻሚዎች ኀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት፣
በጸጥታ ችግር የተነሳ የመራጮች ምዝገባ ማድረግ ባልተቻለባቸው ቦታዎች በልዩ ሁኔታ የሚደረግ መሆኑ ያጋጠሙ ችግሮች
ናቸው ብሏል።
በመራጮች ምዝገባ ላይ ላጋጠሙ ችግሮች ቦርዱ የወሰዳቸው የመፍትሔ ርምጃዎችም የመራጮች ምዝገባ ቀናትን ማራዘም፣
የመራጮች ምዝገባ የቁሳቁስ ስርጭትን አስመልክቶ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር ትብብርን ማጠናከር
የመራጭ ምዝገባ መልእክቶችን እና መረጃዎችን ማሰራጨት ሥራን መጨመር (አጭር የስልክ መልእክቶች፣ የተለያዩ ባለድርሻ
አካላት ትብብር፣ የሲቪል ማህበራት ቅስቀሳ)፣ ከፖርቲዎች እና ከዜጎች ( በ778 ነጻ የስልክ መስመር) የሚመጡ ጥቆማዎችን
ከምርጫ ኦፕሬሽን ሥራዎች ጋር በማቀናጀት መፍትሔ መስጠት፣ የጸጥታ ችግር ባለባቸዉ ቦታዎች ልዩ እቅድ እና ዝግጅት
በማድረግ ከየክልሎቹ የጸጥታ ተቋማት ጋር በመተባበር የአስፈጻሚዎች ስልጠና እና የቁሳቁስ ስርጭት በማከናወን የመራጮች
ምዝገባ ከሚያዝያ 29 ጀምሮ እንዲከናወንባቸው ተወስኗል (4ቱ የወለጋ ዞኖች (24 ምርጫ ክልሎች)፣ ካማሽ (4 ምርጫ
ክልሎች) እና አማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን (3 ምርጫ ክልሎች) በልዩ ሁኔታ ምዝገባ እያከናወኑ ይገኛሉ ብሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የመራጮች ምዝገባ በዋናነት ከፍተኛ የሰው ቁጥር ባላቸው የጋራ መኖርያ ቤቶች አካባቢዎች
የመራጮች ምዝገባ በተለያየ ምክንያት ሲስተጓጎል ነበር ነው ያለው ቦርዱ። ኾኖም ይህንን ለማስተካከል የተለያዩ አማራጮች
እንደተወሰዱ ቦርዱ አስታዉቋል ።
የሶማሌ ክልል የመራጮች ምዝገባን በተመለከተም ለ6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ አቤቱታ
የቀረበበትና በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ለቦርዱ አቤቱታዎችን በማቅረብ (ኦብነግ፣ ነጻነት እና እኩልነት፣ ኢዜማ እና የግል
እጩ ተወዳዳሪ)፣ ሕጋዊ ያልሆነ የምዝገባ ሂደትን
የሚያሳዩ ምስሎች እና ቪዲዎችም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሲታዩ ነበር፤ ቦርዱም በሚዲያ ሞኒተሪንግ ክፍሉ ተሰበስቦ የቀረቡትን
እነዚህን ምስሎች እና ቪዲዮዎች ተመልክቷል ብሏል።
በጋራ እና በተናጠል ለቦርዱ የቀረቡለት አቤቱታዎችም
1. የመራጮች ምዝገባ ካርዶች የማይገባቸው ሰዎች እጅ ገብቷል፣ ከምርጫ ጣቢያ ውጪ ካርዶች ሲታደሉ ነበር።
2. ያልተሞሉ የመራጮች ምዝገባ ካርዶች ለዝቅተኛው መንግሥት እርከን (ቀበሌ ወረዳ ሰራተኞች) እና እጩዎች ተሰጥተዋል።
3. የመራጮች ምዝገባ ሂደቱን የገዥው ፓርቲ የዝቅተኛ እርከን ሠራተኞች ከፍተኛ ጣልቃገብነት ነው የሚሰራው፣ በዚህም
ምክንያት የመራጮች ምዝገባ በቦርዱ ቁጥጥር ስር አይደለም።
4. የምርጫ አስፈጻሚዎች ከመንግሥት አስተዳደር እርከን ሰራተኞች እና እጩዎች ጋር በዝምድና እና በተለያዩ መንገዶች
የተያያዙ በመሆናቸው የገለልተኝነት ጥያቄ አለ።
5. የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ዜጎች እንዳይመዘገቡ ክልከላ ተደርጎባቸዋል።
6. የመራጮች ካርድ የወሰዱ ዜጎች እጅ ተመልሶ ተሰብስቧል።
7. የመራጮች ካርድ ብሉ ቦክስ በምርጫ ጣቢያዎች ሲደርስ በተገቢው መንገድ ሳይታሸግ ነው ፤ ይህም በመካከል እንደተከፈተ
ያሳያል የሚሉ ናቸው።
ለነዚህ አቤቱታዎች ዝርዝር የጽሑፍ አቤቱታ፣ የፎቶ፣ የቪዲዮ እና ሌሎች ማስረጃዎች ይሆናሉ የሚሉ ሰነዶችን አቅርበዋል ነው
ያለው።
አቤቱታዎቹን መሰረት በማድረግ ቦርዱ አቤቱታ ካቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በማእከልም በክልሉም ውስጥ ውይይት
ማከናወኑን አብራርቷል።
በቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ የሚመራ አጣሪ ቡድን ወደ ክልሉ በመላክ ምርጫ ጣቢያዎችን፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን እና ሌሎች
አካላትን እንዳነጋገረ ነው የተገለጸው።
ያቀረቡትን አቤቱታ እና ሰነዶችን በማየት ስብሰባ አከናውኖ የሚከተሉትን ውሳኔዎች መወሰኑን ጠቅሷል፡፡
ቦርዱ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱ ላይ የቀረቡትን ዝርዝር አቤቱታዎች በስፋት መርምሯል፤ በማስረጃነት የቀረቡለትን ከ150 በላይ
የሆኑ ባዶ እና ምዝገባ የተፈፀመባቸው የመራጭ ካርዶችን በመራጮች ምዝገባ ሲስተሙ ላይ ካለው ዳታ ጋር አገናዝቦ
ተመልክቷል፤ የቀረቡ የቪዲዮ ማስረጃዎች(ትርጉም) እና ምስሎችን ከአቤቱታው ጋር ማገናዘቡንም አስታውቋል።
በእነዚህ ሂደቶች ከተመለከታቸው ዝንባሌዎች (trends) በአቤት ባዮቹ የተጠቀሱት ብልሹ አሠራሮች ተፈፅመው ሊሆን
እንደሚችል ግንዛቤ በመውሰድ፤ ይህ ሁኔታም በሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ የሚፈጥር መሆኑን በመገንዘብ ከፍተኛ የሆነ
የመራጮች ምዝገባ ሂደት የአሠራር መዛባት አቤቱታ የቀረበባቸው በሶማሌ ክልል የሚገኙ የሚከተሉት የምርጫ ክልሎች ላይ
የመራጮች ምዝገባ በጊዜያዊነት አንዲቆም ወስኗል።
እነዚህም የምርጫ ክልል አራቢ (ለክልል ምክር ቤት አውበሬ እና ደንበል ከተማ ምርጫ ክልሎችን የሚያካትት)፣ ምርጫ ክልል
ደግሃመዶ የምርጫ ክልል ጎዴ ( ለክልል ምክር ቤት አዳድሌ፣ ቤርአኖ፣ ደናን፣ ምስራቅ ኢሚ፣ ኤልወይኔ፣ ጎዱ፤ ኃይ ከተማ
የምርጫ ክልሎችን የሚያካትት)፣ የምርጫ ክልል ጂጂጋ 1(ለክልል ምክር ቤት ጂግጂጋ፣ ጂግጂጋ ከተማ፣ ቱሉ ጉድሌ ምርጫ
ክልሎችን የሚያካትት)፣ ምርጫ ክልል ቀብሪደሃር (ለክልል ምክር ቤት ደበወይን፣ ቀብሪደሃር፣ ቀብሪደሃር ከተማ፣ መርሲን፣ ሼኮሽ
እና ሺላሎ ምርጫ ክልሎችን የሚያካትት)፣ ምርጫ ክልል ቀላፎ (ለክልል ምክር ቤት ፊርፊር እና ቀለፎ የምርጫ ክልሎችን
የሚያካትት) ምርጫ ክልል ዋርዴር (ለክልል ምክር ቤት ደራቴሌ እና ዋርዴር ምርጫ ክልሎችን የሚያካትት።)
ቀደም ሲል ከተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች ላይ ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት በጊዜያዊነት ሲቆም አስፈጻሚዎች እና
የሚመለከታቸው የቦርዱ ኦፕሬሽን ሠራተኞች የሚወስዱትን እርምጃ አስመልክቶ መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በመመሪያው መሠረት
ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ከላይ በተጠቀሱት የምርጫ ክልሎች ላይ ያለውን የመራጮች ምዝገባ ሂደት የሚያጣራ ቡድን ቦርዱ የሚያቋቁም ሲሆን በዚህም
የማጣራት ሂደት ውስጥ የአቤቱታ አቅራቢ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የቦርዱ ሠራተኞች እና ገለልተኛ ባለሞያዎች የማጣራት ሂደቱን
እንዴት ሊያከናውኑት እንደሚገባ የሚመራ የቴክኒክ ዝርዝር መመሪያን አዘጋጅቶ ወደተግባር የሚገባ ይሆናል ብሏል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m


Previous articleየወቅቱ የዝናብ ሁኔታ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ውኃ ሙሌት ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የዘርፉ ምሁር ገለጹ፡፡


Source link

Related posts

ኢትዮጵያ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የሆነ በአባይ ውሃ የመጠቀም መብቷን የሚያቅብ ማናቸውም ዓይነት ስምምነት አትፈርምም – የውሃ፣መሰኖ እና ኢነርጂ ሚንስቴር

admin

በሀሰተኛ ሰነድ ተጠቅሞ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ የነበረ ገጀራ ተያዘ

admin

በክልሉ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር ወጣቶች ሕዝቡን ከጥቃት መጠበቅ እንደሚገባቸው በአማራ ክልል የተለያዩ አደረጃጀቶች ገለጹ፡፡

admin