61.54 F
Washington DC
April 18, 2021
Satenaw Ethiopian News/Breaking News
Amharic News

 ለጤናው ዘርፍ ከ21 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ያስፈላጋል- ዶ/ር ሊያ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ የሚከናወኑ ተግባራት ብቻ ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር እንደማያስችሉና የባለድርሻ አካላትን ርብርብ እንደሚጠይቁ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፁ።

ዶክተር ሊያ ይህን ያሉት የጤና ሚኒስቴር በቀጣዮቹ ዓመታት ለትግበራ ያዘጋጀውን የጤናው ዘርፍ የአስር ዓመት መሪ ዕቅድ እና የአምስት ዓመት የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለህዝብ ተውካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና የምክር ቤት አባላት እንዲሁም ለተጠሪ ተቋማት ተወካዮች በቢሾፍቱ ከተማ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

መሪ ዕቅዱ 14 የትኩረት አቅጣጫዎች ፣አምስት የትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች እና አምስት ግቦች  እንዲሁም 76 ጠቋሚዎች እንዳሉት ገልፀው ቁልፍ ጉዳዮች ያሏቸውን ለተሳታፊዎቹ አብራርተዋል።

ከህብረተሰቡ ፍላጎት ማደግና መጨመር ፣ከተላላፊ በሽታዎች መስፋፋት እንዲሁም ወጣቶችን ማዕከል ያደረጉ ተደራሽ የጤና አገልግሎቶችን ከማቅረብ አኳያ ዛሬም ተግዳሮቶች መኖራቸውን ዶክተር ሊያ መጠቆማቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም የትምህርት አለመስፋፋት ፣መሠረተ ልማት በበቂ ሁኔታ አለመዘርጋት ፣በሱስ የሚያዙ ሰዎች መበራከት ፣የተፈናቃዮች ቁጥር መጨመር እና በስርዓተ ፆታ ላይ የሚታዩ ችግሮች ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

የጤናው ዘርፍ በቂ በጀት እንዳለው ተደርጎ የሚነገር የተሳሳተ አስተሳሰብ በአንዳንድ የመንግሥት አካላት ዘንድም መኖሩን የጠቀሱት ዶክተር ሊያ በቀጣይም ጥራት ያላቸውን የጤና አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ስለሚጠይቅ የተከበረው ምክር ቤት አባላትም እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ከ21 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ ለስራው እንደሚያስፈልግ የገለፁት ዶክተር ሊያ ወጪውም በመንግሥትና በአጋር አካላት ድጋፍ የሚሸፍን ነው ብለዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ  የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አመራሮች እንዲሁም  የተወካዮች ምክር ቤት አባላትና የጤና ሚኒስቴር ዳይሬክተሮችና የተጠሪ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!Source link

Related posts

በደቡብ ክልል በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እየቀረበ  ነው -የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

admin

በሲሚንቶ ግብይት የወጣውን የዋጋ ተመን ተግባራዊ ባላደረጉ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

admin

“የኢትዮጵያንና የሳዑዲ አረቢያ ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

admin